ረቡዕ 20 ዲሴምበር 2017

ቡና መጠጣት ረጅም እድሜ ለመኖር፣ካንሰርና የልብ ህመምን ለመከላከል ያግዛል- ጥናት

ቡና አዘዉትሮ መጠጣት ረጅም እድሜ ለመኖር  እንዲሁም ካንሰር እና ከልብ ጋር የተያያዘ በሽታን ይከላከላል ሲል አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
ቡና በዓለም ላይ በጣም ከተለመዱ አነቃቂ መጠጦች አንዱ ሲሆን በየቀኑ በዓለም ውስጥ በግምት 2ነጥብ 25 ቢሊዮን ኩባያዎች ይጠጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በኢትዮጵያም ቢሆን ቡና  የሚጠጡ ሰዎች ብዛት ቀላል አይደለም፡፡
ለረጅም ዓመት መኖር ከፈለጉ በቀን ሶስት ሲኒ ቡና መጠጣት በቂ ሊሆን ይችላል ።የምንጠጣው ቡና ለበሽታዎች የመጋለጥ እድልን በመቀነስ እና ለሞት እንዳይዳረጉ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ሲሉ የለንደን ኢምፔርያል ኮሌጅ ተመራማሪዎች ያደረጉት ጥናት አመላክቷል፡፡
ተመራማሪዎቹ ባደረጉት ጥናት ቡና አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች ቡና ከማይጠጡ ሰዎች ጋር ሲነፃፀሩ ረዘም ላለ እድሜ የመኖር እድላቸው ሰፊ መሆኑን ደርሰውበታል፡፡ይህም  በቀን ውስጥ ሦስት ሲኒ ወይም ኩባያ ቡና በአመጋገብዎ ማካተት የጤና ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል በኢምፔርያል ኮሌጅ ሃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢሊዮ ሪቦሊ፡፡  
በአስር የአውሮፓ ሀገሮች ማለትም ብሪታንያ፣ፈረንሳይ፣ ዴንማርክ እና ጣሊያን ከአምስት ሺ ሃያ አንድ እንዲሁም ሶስት መቶ ሰላሳ ከ35 እድሜ በላይ የሆኑት ሰዎች ላይ ጥናቱ ተደርጓል፡፡
በተደረገው ጥናት በቀን እስከ 3 ሲኒ ወይም ኩባያ ቡና የሚጠጡ ሰዎች ከማይጠጡት ሰዎች ጋር ሲነፃፀሩ ረዘም ላለ ግዜ የመኖርና ለሞት ከሚያጋልጡ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ እንደሆነ አሳይቷል፡፡
አለም አቀፉ ኤጀንሲ ፎር ካንሰር የተሰኘው ድርጅት እንዲሁም የኢምፔርያል ኮሌጅ ተመራማሪዎች ቡና የሞት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ የመቀነስ ኃይሉ እንዲሁም በተለይ ሞትን ከሚያስከትሉ በሽታዎች ፡ከደም ዝውውር እና  የምግብ አፈጫጨት ሥርዓቱ ላይ የተስተካከለ እንዲሆን በማድረግ ድርሻው ትልቅ ነው ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች የቡና ፍጆታ እና በጤና  ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ቢያስቀምጡም አወዛጋቢ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአሜሪካም ሆነ በጃፓን ውስጥ  የተደረጉ ትላልቅ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ቡና መጠጣት  ጤና ላይ ተመጣጣኝ ተፅዕኖ እንዳለው ነው ያመለከቱት፡፡   
ቡና በአውሮፓውያን ማህበረሰብ ዘንድ እንደየ ሀገራቱ የተለያየ አፈላል ይዘጋጃል፡፡ ለምሳሌ ጣልያኖች ኢስፕሪስ ቡናን ያዘወትራሉ፡፡ እንግሊዛውያን ደግሞ ካፑቺኖ የተሰኘውን ቡና በወተት ይጠጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ ቡናን ከአመጋገብ ስአታችን ጋር ማዘውተር  ጠቀሜታው  ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
"ቡና መጠጣት ከተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር ተያያዥነት እንዳለውና የበሽታን  የመከላከል  ምላሽ እንደሚሰጥ ተመልክተናል. "ይህ በአሜሪካ እና ጃፓን ውስጥ ከተደረጉ ጥናቶች ጋር ሲነፃፀር በተወሰነ መልኩ ወጥነት ቢጎድለውም ቡና መጠጣት የጤና ጥቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ ግን ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ዶክተር ጎርተር ተናግረዋል፡፡" (ምንጭ:ሲኤንኤን)

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ