ረቡዕ 20 ዲሴምበር 2017

ነፍሰ ጡሮች ጣፋጭ መጠጦችን መውሰድ እንደሌለባቸው የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ተናገሩ

የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ብዙ እናቶች በተለይም ነፍሰ ጡሮች ጣፋጭ መጠጦችን እንዳይወስዱ መክሯል፡፡
ተመራማሪዎቹ  እንደሚሉት ነፍሰ ጡሮች በብዛት ጣፋጭ መጠጦችን የሚወስዱ ከሆነ እናቶች የሚወለዱት ህፃናት ለአስም በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋነው ፡፡ ይህንንም በጥናት ማረጋገጡን ነው ዩኒቨርሲቲው ያስታወቀው፡፡
በጥናቱ መሠረት በየቀኑ በአማካይ ሁለት ጠርሙስ የስኳርነት ባህሪ ያላቸው ጣፋጭ መጠጦችን የሚጠጡ ነፍሰ ጡር እናቶች ልጆቻቸው ከ7 እስከ 9 ዓመት የዕድሜ ክልል ሲደርሱ ለአስማ በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነዉ፡፡ በመቶኛ ሲሰላ 60 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት ለአስም በሽታ ይጋለጣሉ፡፡
ጣፋጭ መጠጦችን መጠቀም፣ ስኳር የበዛበት ምግብ መመገብ የሰውነትን  ክብደት  እንደሚጨምር አጥኚዎቹ አስታዉቀዋል፡፡
የክብደት መጨመር ደግሞ ብዙ ጊዜ በነፍሰጡር እናቶች ከተከሰተ ለረጅም ጊዜ በልጆቻቸው ጤና ላይ እክል እንዲገጥም ሊያደርግ እንደሚችል ተመራማሪዎች ገልጸዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ  በአንድ  ሺህ ስልሳ ስምንት እናቶች እና ህጻናት ላይ የረዥም ጊዜ ጥናት ማካሄዳቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡
ነፍሰ ጡር ሴቶች በየቀኑ ምንያህል ስኳርና ሌሎች ጣፋጭ መጠጦችን፣ ፍራፍሬዎችና ጭማቂዎችን እንደሚጠቀሙ ተጠይቀዋል፡፡ ለጥናቱ አጋዥ የሆኑ መጠይቆችም በተከታታይ በጥናቱ ቀርበውላቸዋል፡፡
የጥናቱ ውጤት እንደሚያመለክተው በአማካይ በጥናቱ ከተካተቱ አምስት ህፃናት መካከል አንዱ የአስም በሽታ ሰለባ ሆኗል፡፡ በእርግዝና ወቅት በቀን ሁለት ጠርሙስ ጣፋጭ መጠጦች ከሚጠጡ እናቶች የሚወለዱ ህፃናት ምንም ጣፋጭ መጠጥ ከማይጠጡ እናቶች ጋር ሲነፃፀር 63 በመቶ ለአስም በሽታ ይጋለጣሉ፡፡
ጥናቱ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት በእርግዝና ወራት በምትወስዳቸዉ መጠጦች ምክንያት የጤና መታወክ እንደሚያጋጥማት ተመራማሪዎቹ መረዳታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ህፃናት በለጋ ዕድሜያቸው የሚሞቱበትን ምክንያት ያመለካተ በመሆኑም ጠቀሜታው የጎላ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች መግለፃቸውን ዩ ፒ አይ ድረ ገፅ አስነብቧል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ