ማክሰኞ 24 ኤፕሪል 2018

ሞሃመድ ሳላህ የ2017-2018 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ምርጡ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የ2017-18 የእንግሊዝ ፕሪሚየር  ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
የ25 ዓመቱ ሞሃመድ ሳላህ ተፎካካሪዎቹን ኬቨን ዴብሩየን፤ ሊሮይ ሳኔ፤ ዲቬዲ ሲልቫ፤ ሃሪ ኬንን እና   ዲቬድ ድሂሃን በመብለጥ ነው አሸናፊነቱን ያረጋገጠው፡፡
“በቼልሲ ክለብ እያለሁ ያለኝን ችሎታ ማሳየት አልቻልኩም ነበር፤ በተጫዎቾች መመረጤ ክብር ተሰምቶል በጣም ደስተኛ ነኝ” በማለት ሳላህ አስተያቱን ሰጥቷል፡፡
የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በበኩላቸው የሳላህ አሰልጠኝ በመሆናቸው እጅጉን ደስተኛ እንደሆኑና  ይህን ሽልማት ማሸነፉ የማይታመን ክብር ነው በማለት ለሳላህ ያላቸውን አድናቆት ተናግረዋል፡፡
ሳላ ፕሪምየር ሊግ በ31 ጨዋታዎች 33 ግቦች በማስቆጠር የፕሪሚየር ሊጉን የምን ጊዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰኑን ከአላን ሼረር ፣ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሉዊስ ሱዋሬዝ ጋር ክብረወሰኑን ተጋርቷል፡፡
የማንችስተር የሲቲው  ሊሮይ ሳኔ ደግሞ የፕሪምየር ሊግ ወጣት ተጫዋች በመባል የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በሴቶቹ ደግሞ የቼልሲዋ ፍራንክ ኪርቢ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብላ የተሸለመች ሲሆ የብሪስቶል ሲቲዋ ላውረን ሄምፕም እንዲሁ በሴቶች ወጣት ተጫዋችን ሽልማት አግኝታለች፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲ

ረቡዕ 18 ኤፕሪል 2018

ምክር ቤቱ ነገ አዲስ አፈጉባኤ ይመርጣል፤ የካቢኒ አባላት ሹመትንም ያፀድቃል

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ አዲስ የምክር ቤቱን አፈጉባኤ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸውን እጩ የካቢኒ አባላት ሹመትን ተቀብሎ ያፀድቃል ተብሎም ነው የሚጠባቀው።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅንም ተመልክቶ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ



አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
ድምፃዊ ታምራት በድንገተኛ አደጋ ህይዎቱ ማለፉ ታውቋል።
ታምራት ደስታ አንለያይም፣ ሃኪሜ ነሽ፣ ከዛ ሰፈር፣ ካንች አይበልጥ፣ ሊጀማምረኝ ነው እና ሌሎችም ስራዎቹ በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጆች ናቸው።
ድምፃዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።
 ለቤተሰቦቹና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።