በመዲናዋ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም የተጀመረው የአሮጌ የውሃ መስመሮችን በፕላስቲክ ቧንቧ ቅየራ ስራ እስካሁን 65 ኪሎ ሜትር ዝርጋታ መከናወኑን የአዲሰ አበባ ከተማ የውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን አስታወቀ።
የመስመር ቅየራው በአሮጌ የብረት መስመሮች ምክንያት የሚስተዋለውን የውሃ ጥራትን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ዘለቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአዲስ አባባ መንገዶች ባለስልጣን የክረምት መንገድ ቁፋሮ ክልከላ እና በ42 የጥቃቅን ማህበራት ስልጠና ምክንያት ዘግይቶ ተጀምሯል።
በዚህም አሮጌ የብረት የውሃ መስመሮችን የመቀየር ስራ በአሁን ወቅት ከ100 ኪሎ ሜትር ውስጥ 65 ኪሎ ሜትር ተከናውኗል።
ቀሪው 35 ኪሎ ሜትር ዝርጋታ በቀጣይ አንድ ወር ይጠናቀቃል ብለዋል።
እንደ አቶ ፍቃዱ ገለጻም ባለስልጣኑ በቀጣይም በአጠቃላይ 263 ኪሎ ሜትር ቀሪ አሮጌ መስመሮችን በፕላስቲክ የመቀየር ስራ እንደሚያከናውን አመላክተዋል።።
በታሪክ አዱኛ

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ