ዓርብ 3 ኦገስት 2018

#በሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው


አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው።

መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ያሰረከበባቸው ተጠርጣሪዎች አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው።

የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት አቃቤ ህግ ብርሃኑ ወንድምአገኘሁና አቃቤ ህግ ካሳሁን አውራሪስ የተጠርጣሪዎቹ ጉዳይ እየታየበት ያለበትን የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት የተረከቡትን የምርመራ መዝገብ የድምፅ ቅጂ፣ የምስልና ዝርዝር ጉዳዮች ምርመራ የያዘ በመሆኑ፥ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ይሰጠን ሲሉ ጠይቀዋል።

ተጠጣሪዎች በበኩላቸው ምርመራው ከተጠናቀቀ ለአቃቤ ህግ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጠው አይግባም፤ የዋስትና መብታችን ይጠበቅ፤ በማረፊያ ቤት የሚያጋጥመንም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይቁም ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጠው አቃቤ ህግ በበኩሉ የሁለት ዜጎች ህይወት ያለፈበት እና በበርካቶች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰበት እንዲሁም ድርጊቱ ተቀነባብሮ የተፈፀመ በመሆኑ በምስክሮች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ ዋስትና ሊፈቀድ አይገባም ሲል ተቃውሟል።
ሰብዓዊ መብታቸውን በተመለከተ ምላሽ የሰጠው መርማሪ ፖሊስ፥ በየቀኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚገናኙና ባረፉበት አካባቢ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በየቀኑ የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃ ስላለ ይህንን የቪዲዮ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን ብሏል።

ድርጊታቸው የተቋም ስምን ማጥፋት ነው፤ ካልሆነ ግን ጉዳዮን የሚከታተል ገለልተኛ አካል ሊመደብ ይችላል ሲል ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ሁለቱንም ወገን ካደመጠ በኋላ አቃቤ ህግ የጠየቀውን የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሰርዓት አንቀፅ 109 ንፁስ ቁጥር 1 መሰረት ክስ መመስረቻ የ15 ቀን ጊዜ ፈቅዳል።

ተጠርጣሪዎችም በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ያዘዘ ሲሆን፥ ሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ ግን የሚመለከተው ኃላፊ በቀጣይ ቀጠሮ ቀርቦ እንዲያስረዳ አዟል።

የአቃቤ ህግ ክስን ለማየት ለነሃሴ 16 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ይዟል።

ቀሪ ተጠርጣሪ የሆኑት የብሄራዊ መረጃ ደህንነት መምሪያ አዛዝ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ ሶስት ተጠርጣሪዎች የምርመራ መዝገብ ጉዳይ የፊታችን ረቡዕ በችሎቱ የሚቀርብ ሲሆን፥ የስራ ክፍተት በመፍጠር የተጠረጠሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የነበሩት ግርማ ካሳን ጨምሮ ዘጠኝ የፌደራል ፖሊስ አባላትን በተመለከተ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠው ቀጠሮ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሚታይ ይሆናል።

በታሪክ አዱኛ
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

እሑድ 15 ጁላይ 2018

Ethiopia: ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዶ/ር አብይ የክብር ካባ ተበረከተላቸው!!

ፕረዚደንት ኢሰያስ ኣፈወርቂ ኣብ ቤተ መንግስቲ ኢትዮጲያ ናይ ቀለቤት ህያብ ተበርኪትሉ

አዲስ ነገር አርቲስቶቻችን ስለ ኢትዮ ኤርትራ ወዳጅነት እና ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ/What's new Specaial ...

Ethiopia: ዶ/ር አብይ እና ኢሳያስ አፈወርቄ ዛሬ የተደረገላቸዉ የቁርስ ግብዣ በሀዋሳ

Ethiopia: ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ያደረጉት ታሪካዊው የአማርኛ ንግግር !!

ሐሙስ 12 ጁላይ 2018

Ethio Man - Nkidn Do | ንኺድን'ዶ - New Tigrigna Music 2018 (Official Video)

በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ እያሽቆለቆለ መጥቷል

 በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ የዶላር የምንዛሬ ዋጋ ከሰሞኑ እያሽቆለቆለ መጥቷል።
በአሁኑ ወቅትም በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ ያለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ወደ ባንኮች ተመን እየተጠጋ መሆኑ ተሰምቷል።
የሀገሪቱ አምራች ኢንዱስትሪ የሚጠበቅበትን የውጭ ምንዛሬ ማምጣት ተስኖት አለመረጋጋቱም ተጨምሮበት የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ከፍተኛ የሚባል ደረጃም ላይ መድረሱ የሚታወስ ነው።
ዘላቂ መፍትሄ አይሁን እንጂ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 2 ቢሊየን ዶላርን በኢትዮጵያ ለሚደረግ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 1 ቢሊዮን ዶላር ለውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለማቃለል ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንደምታስቀምጥ ተናገረች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ባሳለፍነው አርብ ሰኔ 2010 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥ ሰሞኑን በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ የዶላር ምንዛሬ ዋጋ በተወሰነ ደረጃ ቀንሷል ማለታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፥ “አዳዲስ ዶላሮች እየገቡ ስለሆነ በጥቁር ገበያ ዶላር የያዛችሁ ሰዎች በአፋጣኝ በባንክ ገበያ የማትለውጡት ከሆነ እናንተንም ችግር ውስጥ ስለሚያስገባ ብታስቡበት” በሚል መልክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። 
ይህንን ተከትሎም የአሜሪካን ግምጃ ቤት ተሰብስቦ የወለድ ምጣኔ ከፍ አለ ወይስ ዝቅ አለ በሚል የሚተራመሰውን ገበያ ዓይነት ኢትዮጵያ ውስጥም በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ታይቷል። 
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አንድ የአሜሪካን ዶላር ቀድሞ ሲሸጥበት ከነበረው 36 ብር በጣም መቀነሱም ተነግሯል።
በአሁኑ ወቅትም አንድ የአሜሪካ ዶላር በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ ከ28 ብር እስከ 30 ብር ድረስ ወርዶ ወደ ባንኮች ተመን እየተጠጋ መሆኑ ተሰምቷል።
አሁን ግን የህገወጡ ዶላር ምንዛሬ በእጅጉ ወርዶ ከህጋዊው ምንዛሬ 1  ብር ልዩነት ላይ ደርሷል።
በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የዶላር የምንዛሬ ዋጋ በዚህ ደረጃ የወረደበት ምክንያት ግልጽ እንዳልሆነላቸው በመግለጽ፤ በአሁኑ ወቅት ዶላርን የመግዛት ፍላጎታቸው እንደቀነሰ ነው የሚናገሩት።
የጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ ሁኔታን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እና ባለሙያዎች ደግሞ በጥቁር የውጭ ምንዛሬ ገበያ እንዲዳከም ምክንያት የሆነው በሀገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥ ነው ይላሉ።
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ረቡዕ 11 ጁላይ 2018

#የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 100 ቀናት

የ42 ዓመቱ ጎልማሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመቶ ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መንበረ ሥልጣኑን ተረከቡ። በበዓለ ሲመታቸው ዕለት ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ዘልቀው ገቡ። “ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነትና ይቅርታ” የሚሉት መልዕክቶቻቸው የሕዝብን ልብ ገዝተው ላቸዋል። 
“ማንነታችን እንዳይለያይ ሆኖ የተሰናሰለ፣ እንዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደ፣ የተዋደደ እና የተዋሃደ ነው። ኢትዮጵያ ከፖለቲካ አመለካከት በላይ ነች። ኢትዮጵያውያን ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ እንሆናለን” በማለት ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊነት ያነሷቸው ሀሳቦቻቸው ከልጅ እስከ አዋቂ፤ ከደጋፊ እስከ ተቃዋሚ ሁሉንም የገዙ መልዕክቶች ነበሩ። ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ባለፉት መቶ ቀናት ያከናወኗቸው ሥራዎች በምሁራን እንዴት ይታያሉ? በቀጣይስ ምን መሥራት አለባቸው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በትረ ሥልጣኑን ሲረከቡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ግጭቶች ነበሩ። አገሪቱም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ነበረች። የመጀመሪያ ሥራቸውም ያደረጉት መረጋጋት ማስፈን ነው። የችግሮች መፍቻ ስልታቸው ደግሞ ከወትሮው የተለየ ነበር። የፀጥታ ኃይል ከመላክ ይልቅ መቃቃር፣ መጠራጠርና ግጭቶችን ለማስወገድ በየክልሉ በመዞር ስለ አንድነት፣ ፍቅር፣ ይቅርታና ሠላም መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሌት ተቀን በሚባል ደረጃ በጅግጅጋ፣ አምቦ፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ሀዋሳ፣ ባሌ፣ ደንቢዶሎ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወልቂጤና አፋር ከተሞች ፀብ እንዲጠፋ ሠላም እንዲወርድ መተማመን እንዲፈጠር ሰብከዋል። በዚህም አሁንም ያልተጠናቀቁ የቤት ሥራዎች ቢኖሩም አገሪቱ ከነበረችበት የሠላም እጦት እያገገመች ነው። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ተላቃለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህን ለመፍታት ብዙ መልፋታቸውንና እንደተሳካላቸው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለኃይማኖት፤ በአገሪቱ የነበረው ግጭት የአፈና ውጤት መሆኑን ያነሳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሩት ዴሞክራሲን የማስፋት አካሄድ የሚቀጥል ከሆነና የሕግ የበላይነት እየሰፈነ ከሄደ ችግሩ እየተፈታ ይሄዳል። ዶክተር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በአገሪቱ ያለውን የሠላም ችግር በመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርከተዋል። ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራትም ችግሩን ሙሉ በሙሉ መፍታት እንደሚገባቸውም ያሳስባሉ።
ሌላው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትኩረት የተሰጠው የኢኮኖሚው ጉዳይ ነው። የመንግሥት ትላልቅ ድርጅቶችን በከፊልና በሙሉ ወደ ግል ማዘዋወር፣ የ2011 በጀት ዓመት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ላይ ትኩረት ማድረጉ በጉልህ የሚታዩ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ናቸው።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር ባልደረባ የሆኑት የኢኮኖሚ ምሁሩ ዶክተር አሰፋ አድማሴ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የመንግሥት ግዙፍ ድርጅቶችን በከፊልና ሙሉ ለሙሉ ወደ ግል ለማዘዋወር የተላለፈው ውሣኔ ትክክለኛ ነው ይላሉ።
ዶክተር አሰፋ እንደሚሉት፤ የ2011 በጀት ከሌሎች ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ዕድገቱ መጠነኛ ነው። ይህም ብድርን ለመቀነስ ያለመ ነው። የተመደበው በጀት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ላይ ማተኮሩ ገንዘብና ጊዜ እየበሉና በኢኮኖሚው ላይ ጫና ያሳደሩትን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ ያግዘዋል።
ከጎረቤት አገራት ጋር የተጀመሩ ጠንካራ ግንኙነቶችም በወደብ፣ በአየርና በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች በጋራ ለማደግና ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ይረዳሉ። ከዚህ ባለፈም ለፀጥታ የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ ባለፉት ሦስት ወራት ከአንድ መሪ የሚጠበቅ በቂ የኢኮኖሚ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ያስቀመጡትን አቅጣጫ የመፈፀም ኃላፊነት የዜጎችና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እንዲሁም የውጭ ባለሀብቶች ነው ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ መቶ ቀናት እስረኞችን በይቅርታ መፍታት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያከናወኑ ኃላፊዎችን በሌላ መተካት፣ የምህረት አዋጁ እንዲወጣና ሌሎች ሕጎችን ለማሻሻል ጥናት የሚያደርግ ኮሚቴ ማቋቋም በጉልህነት የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው።
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ ረዳት ፕሮፌሰር መኮንን ፍስሃ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገር ውስጥ በተለያየ ምክንያት የታሰሩ ዜጎችን በመፍታት እንዲሁም በውጭ ታስረው የነበሩ ዜጎችን በማስፈታት ባለፉት ሦስት ወራት የለውጥ ኃይል መሆናቸውን አሳይተዋል። ችግር ያለበትን የፍትህ ሥርዓት መስመር ለማስያዝም እንደሞከሩ በማንሳት ጥሩ የለውጥ ጅምሮች መደረጋቸውን ይናገራሉ።
ረዳት ፕሮፌሰር መኮንን፤ ሆኖም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተወሰዱ እርምጃዎች አብዛኞቹ ትክክል ቢሆኑም፤ በሽብር፣ በሰው መግደልና በሙስና የተጠረጠሩና የተፈረደባቸው ሰዎቸ መፈታታቸው ተገቢ አልነበረም። የሚወሰኑ አንዳንድ ውሣኔዎች ግልፅነት ይጎላቸው ነበር። እንደ ሰንደቅ ዓለማ ያሉና ሌሎች ሕጎች አልተከበሩም። አንዳንድ ውሣኔዎችም የሕግ መሰረት ሳይኖራቸው ተወስነዋል። ከመስቀለኛ መንግድ ወደ ሌላ መስቀኛል መንገድ እንዳንገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥንቃቄና በትብብር መሥራት እንዳለባቸው በማንሳት ጅምሩን ከዳር ማድረስ እንደሚገባቸው ሃሳብ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመቶ ቀናት ውስጥ ትኩረት ሰጥተው ካከናወኗቸው ጉዳዮች ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር ሌላው ተጠቃሽ ጉዳይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ሦስት ወራት ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ዩጋንዳና ኤርትራ ከመካከለኛው ምስራቅ ደግሞ ሳኡዲ አረቢያና ዩናይትድ አረብ ኢሜሬቶችን ጎብኝተዋል። ኢትዮጵያ ከአገራቱ ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲኖራት መሥራታቸው ሌላው ስኬት ነበር።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሲሳይ አስምሬ፤ ዶክተር አብይ በዲፕሎማሲው መስክ ባለፉት ሦስት ወራት በአፍሪካ ታይቶ የማይታወቅ ስኬት አምጥተዋል። ለዓመታት በጦርነት ተፋጠው የኖሩትን ኢትዮጵያና ኤርትራንም ወደ ሠላምና አንድነት በማምጣት ስኬታማ ሆነዋል። በዲፕሎማሲ ሥራቸው በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም ተቀባይነት እያገኙ ነው። የጀመሩትን የዲፕሎማሲ ሥራ ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ የቀጣናውን አገራት በኢኮኖሚ አንድ ከማድረግ ባለፈ ፖለቲካዊ ውህደትን ዕውን ለማድረግ መንገድ ይጠርጋሉ። እስካሁን ባለው የዲፕሎማሲ ሥራቸው ይህን ያስተካክሉ የሚባል ነገር የለም፤ የጀመሩትን ከፍፃሜ ለማድረስ መሥራት ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ወራት ስኬታማ ሥራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
ዶክተር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጁት አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኦነግ እና ኦብነግ ከአሸባሪነት መሰረዛቸው በበጎ የሚታይ ተግባር ነው። በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት መጥተው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ጥሪ አድርገዋል። እንደ ኢሳትና የኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ መገናኛ ብዙሃንና የሚዲያ መሪዎቹ ላይ የነበረውን የፍርድ ቤት ክስም እንዲቋረጥ አድርገዋል። ይህን ተከትሎ ወደ አገር ቤት የገቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ለመግባትም የተዘጋጁ አሉ።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲው መምህር ሲሳይ፤ በአሸባሪነት የተፈረጁ ከሽብር መሰረዛቸው፣ በተለያየ ምክንያት የታሰሩት መፈታታቸው፣ መገናኛ ብዙሃን በነፃነት እንዲዘግቡ መደረጉ፣ ዜጎችና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን በነፃ መግለፃቸው፣ ሕጎችን ለማስተካከል ሥራዎች መጀመራቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ሦስት ወራት ያከናወኗቸው ስኬታማ ሥራዎች ናቸው። የተጀመሩት ሥራዎች መልካም የሚባሉ ሲሆን፤ ፓርቲዎች ሕገ መንግሥቱን አክብረው በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ፣ የአገሪቱ የዴሞክራሲ ባህል የማዳበርና ጠንካራ ተቋማትን የመፍጠር ጉዳይ በቀጣይ ትልቅ የቤት ሥራቸው ማድረግ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

ዜና ሐተታ
አጎናፍር ገዛኸኝ

ሰኞ 9 ጁላይ 2018

#የዓለም ባንክ የአፍሪካ ጎዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ነገ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

የዓለም ባንክ የአፍሪካ ጎዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፌዝ ጋኒም ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ በነገው ዕለት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅትም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ ጋርም ይወያያሉ፡፡
በውይይታቸው ወቅትም ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ግስጋሴና በአዲሱ የማሻሻያ ፖሊሲዎች ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ባንክ መካከል ስላለው የስራ ግንኙነትም ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

                                                                                                            አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2010 (ኤፍቢሲ)
туристический онлайн-справочник
Лучшие Андроид планшетአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የዓለም ባንክ የአፍሪካ ጎዳዮች ምክትል ፕ

TEDDY AFRO live - Fiyorina (Flashback)

TEDDY AFRO - Dahlak Live (Throwback)

Sisay Demoz Amarebish Zare አማረብሽ ዛሬ New Ethiopian Music Dedicated ...

ERi-TV, Eritrea: Speeches by President Isaias Afwerki

ማክሰኞ 24 ኤፕሪል 2018

ሞሃመድ ሳላህ የ2017-2018 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ምርጡ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የ2017-18 የእንግሊዝ ፕሪሚየር  ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
የ25 ዓመቱ ሞሃመድ ሳላህ ተፎካካሪዎቹን ኬቨን ዴብሩየን፤ ሊሮይ ሳኔ፤ ዲቬዲ ሲልቫ፤ ሃሪ ኬንን እና   ዲቬድ ድሂሃን በመብለጥ ነው አሸናፊነቱን ያረጋገጠው፡፡
“በቼልሲ ክለብ እያለሁ ያለኝን ችሎታ ማሳየት አልቻልኩም ነበር፤ በተጫዎቾች መመረጤ ክብር ተሰምቶል በጣም ደስተኛ ነኝ” በማለት ሳላህ አስተያቱን ሰጥቷል፡፡
የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በበኩላቸው የሳላህ አሰልጠኝ በመሆናቸው እጅጉን ደስተኛ እንደሆኑና  ይህን ሽልማት ማሸነፉ የማይታመን ክብር ነው በማለት ለሳላህ ያላቸውን አድናቆት ተናግረዋል፡፡
ሳላ ፕሪምየር ሊግ በ31 ጨዋታዎች 33 ግቦች በማስቆጠር የፕሪሚየር ሊጉን የምን ጊዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰኑን ከአላን ሼረር ፣ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሉዊስ ሱዋሬዝ ጋር ክብረወሰኑን ተጋርቷል፡፡
የማንችስተር የሲቲው  ሊሮይ ሳኔ ደግሞ የፕሪምየር ሊግ ወጣት ተጫዋች በመባል የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በሴቶቹ ደግሞ የቼልሲዋ ፍራንክ ኪርቢ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብላ የተሸለመች ሲሆ የብሪስቶል ሲቲዋ ላውረን ሄምፕም እንዲሁ በሴቶች ወጣት ተጫዋችን ሽልማት አግኝታለች፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲ

ረቡዕ 18 ኤፕሪል 2018

ምክር ቤቱ ነገ አዲስ አፈጉባኤ ይመርጣል፤ የካቢኒ አባላት ሹመትንም ያፀድቃል

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ አዲስ የምክር ቤቱን አፈጉባኤ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸውን እጩ የካቢኒ አባላት ሹመትን ተቀብሎ ያፀድቃል ተብሎም ነው የሚጠባቀው።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅንም ተመልክቶ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ



አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
ድምፃዊ ታምራት በድንገተኛ አደጋ ህይዎቱ ማለፉ ታውቋል።
ታምራት ደስታ አንለያይም፣ ሃኪሜ ነሽ፣ ከዛ ሰፈር፣ ካንች አይበልጥ፣ ሊጀማምረኝ ነው እና ሌሎችም ስራዎቹ በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጆች ናቸው።
ድምፃዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር።
 ለቤተሰቦቹና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

ማክሰኞ 27 ማርች 2018

ሰበር­_ዜና: ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

ለቀናት ስብሰባውን ሲያካሂድ የቆየው የኢህአዴግ ምክር ቤት ዶክተር አብይ አህመድን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከግንባሩ ሊቀመንበርነት ለመነሳት ያስገቡትን መልቀቂያ መቀበሉን ተከትሎ ነው ምክር ቤቱ ምርጫ በማካሄድ ተተኪ የመረጠው። ምክር ቤቱ አቶ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉም ወስኗል።
                                                      ዶክተር አብይ አህመድ ማን ናቸው?

የትውልድ ስፍራ፦ ጅማ ዞን
የትምህርት ዝግጅት፦ የመጀመሪያ ዲግሪ በኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ፣ ሁለተኛ ዲግሪ በትራንፎርሜሽናል ሊደርሺፕ እና ቼንጅ፣ ማስተርስ ኢን ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን እና በክሪፕቶ ግራፊ እንዲሁም የዶክትሬት ትምህርታቸውን በ“ፒስ ኤንድ ሴክዩሪቲ” አግኝተዋል።
የስራ ልምድ፦ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ እስከ ሌፍተናንት ኮሎኔል ድረስ በተለያዩ ስፍራዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል፣ የፌደራል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የልህቀት ማእከል ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፣ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ውስጥም በምክትል ዳይሬክተርነት አገልግለዋል። በተጨማሪም የኢፌዴሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመሆኑ አገልግለዋል።
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት እና ቤቶች ቢሮ ሃላፊ በመሆን ሰርተዋል።
ዶክተር አብይ አህመድ የኢህአዴግ አባል ድርጅት የሆነው ኦህዴድ ሊቀመንበር ናቸው።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

ረቡዕ 14 ማርች 2018

ከ4 ወራት በፊት ባለቤቱ በሞት የተለየበት ታማኝ ውሻ እስከአሁን ድረስ ከሆስፒታሉ በራፍ አልተንቀሳቀሰም

ከ4 ወራት በፊት ባለቤቱ በህመም ምክንያት በሞት የተለየበት ታማኝ ውሻ እስከአሁን ድረስ ከሆስፒታሉ በራፍ ባለ መንቀሳቀሱ የአለም መገናኛ ብዙሃን መወያያ ርእስ ሆነዋል።
የውሻው ባለቤት በጠና በመታመሙ ምክንያት ነበር ከሚኖርበት አከባቢ ወደ ብራዚል ሳኦ ፓሎ ሆስፒታል በአንቡላንስ የተወሰደው።
በዚህም ውሻው ይህ ሲያውቅ የአንቡላንሱን መንገድ በሩጫ ተከትሎ ሆስፒታሉ ድረስ መምጣቱ ሰራተኞች ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ የ59 አመት እድሜ የውሻው ባለቤት ህመሙ ከባድ ስለነበር የህክምና እርዳታ ሲያገኝበት ከነበረ ሆስፒታል ሳይወጣ ከአራት ወራት በፊት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ውሻው ግን ይህን አላምን በማለቱ ለባለቤቱ ጤና እየተመኘ እስከአሁን ድረስ ከሆስፒታሉ በራፍ ሳይንቀሳቀስ ባለቤቱ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ነው ተብሏል።

 ምንጭ፦www.odditycentral.com(ኤፍ.ቢ.ሲ)

ለሴት ልጃቸው የወንድ ስም የሰጡት ወላጆች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ቤተሰቦች ስም ለማውጣት ብዙ ክርክሮች ያደርጋሉ ያለው ሚረር በፈረንሳይ ግን ከዚህ በተለየ ለሴት ልጃቸው የወንድ ስም በማውጣታቸው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነግሯል።
ለህፃኗ ልጅ ቤተሰቦቿ “ሊያም” የሚል ስም ቢያወጡላትም ፍርድ ቤቱ ለሴት ልጅ የሚሆን ስም አይደለም ብሎ ማገዱ ነው የተነገረው።
 የልጅቱ ስም የህፃናትን ፍላጎት የሚፃረር እና በማህበራዊ ግንኙነት ላይ ትፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ስሙን ሊያግደው እንደሚገባ አቃቤ ህጎች ተናግረዋል።
በተጨማሪም ስሙ ፆታዊ የሆኑ ብዠታዎችን ይፈጥራል ተብሏል።
ጉዳዩን የሚከታተለው ፍርድ ቤት የህፃኗ ቤተሰቦች አዲስ ስም እንዲያወጡ ማዘዙም ተገልጿል። 
ሆኖም የህፃኗ ቤተሰቦች ልጃቸው ባውጡላት ስም እንድትጠራ እንደሚፈልጉና ለዚህም የህግ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የተናገሩ ሲሆን፥ የህፃኗን ጥምቀት( baptism) ማራዘማቸው ታውቋል።
በልጃቸው ስም ምክንያት ፍርድ ቤት የቆሙት ወላጆች ጉዳይ ለልጆች ስም ማውጣት ላይ ጥብቅ ስርዓት አላት በምትባለው ፈረንሳይ ያልተለመደ መሆኑ ተነግሯል።
ከዚህ በፊት በፈረንሳይ ኑታላ፣ ስትሮዎበሪ እና ማንሃታ የተሰኙ ስሞች ለልጆች ማውጣት መከልከሉ ይታወሳል።
ምንጭ፦ ሚረር(ኤፍ.ቢ.ሲ)

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከኃላፊነት አነሱ

 የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን ከኃላፊነት አነሱ። በሬክስ ቲለርሰን ቦታም የሲ አይ ኤ ዳይሬክተር ማይክ ፔምፖንን ተክተዋል ነው የተባለው። 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰንን በትዊተር ገፃቸው ያመሰገኑት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፔምፖ መልካም ስራዎችን ይሰራሉ ሲሉ ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የኤክሶንሞቢል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ሬክስ ቲለርሰን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ከአንድ ዓመት በፊት ነበር።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሆኑት የማይክ ፔምፖ የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተርነት ስፍራ ላይም የመጀመሪያዋ ሴት የሆኑትን ጊና ሀስፔልን በእጩነት አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ ስቴፈን ሀውኪንግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለ

የዓለማችን ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ ስቴፈን ሀውኪንግ በ76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ።  እንደ ቤተሰቦቹ ገለፃ፥ ስቴፈን ሀውኪንግ ዛሬ ማለዳ ላይ በቤታቸው እያሉ አርፈዋል።“በጣም የምንወደው አባታችን ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል” ሲሉም የስቴፈን ሀውኪንግ ልጆች ተናግረዋል። የፌዚክስ ሊቅ የሆኑት እንግሊዛዊው ስቴፈን ሀውኪንግ “ብላክ ሆልስ” እና “ሪላቲቪቲ” በሚባሉ የፊዚክስ ስራዎቻቸው የሚታወቁ ሲሆን፥ “ብሪፍ ሂስትሪ ኦፍ ታይም” የሚለውን ጨምሮ በርከት ያሉ የሳይንስ መጻህፍቶችንም ጽፈዋል።
ስቴፈን የ22 ዓመት ወጣት እያሉ ባጋጠማቸው የነርቭ ህመም ያለ ድጋፍ ሰጪ መሳሪያ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ ሳይችሉ ቆይተዋል።
ስቴፈን ሀውኪንክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥር 8 1942 ላይ ነበር በእንግሊዟ ኦክስፎርድ የተወለዱት።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1959 በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በተፈጥሮ ሳይንስ ያጠኑት ሀውኪንግ፥ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ ከካንብሪጅ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል;። 
በፈረንጆቹ 1963 “ሞቶር ኔውሮን” በተባለ የነርቭ በሽታ የተጠቁት ስቴፈን በወቅቱም ከዚህ በኋላ በህይወት የሚኖሩት 2 ዓመት ብቻ ነው ተብለው ነበር።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1988 ያሳተሙት “ብሪፍ ሂስትሪ ኦፍ ታይም” የሚለው መጽሃፋቸውም በዓለም ዙሪያ በ10 ሚሊየን ኮፒ መሸጡ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ሰኞ 19 ፌብሩዋሪ 2018

ህጉን ተፈጻሚ ለማድረግ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል

አገሪቱ ሲጋራ ማጨስ መቆጣጠርን አስመልክቶ የትንባሆያጸደቀቻቸውን አለም አቀፍ ኮንቬንሽን እንዲሁም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ የወጣውን የማስፈጸሚያ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስፋት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ የህግ ክፍል ዳይሬክተር ወይዘሮ አብረኸት ግደይ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተ ናገሩት፤ ትምባሆን መጠቀም እንደ አገር ጎጂ በመሆኑ ምርቱ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል። አገሪቱ ያጸደቀችውን ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ወደ ተግባር ለመቀየርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አወጅ ቁጥር 822/2006 ተፈጻሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት ተሰጥቶታል።
የቁጥጥር ስራው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብቻ ተሰርቶ ውጤታማ እንደማይሆን ዳይሬክተሯ ጠቅሰው፤ የሚመለከታቸው የዘርፍ መስሪያ ቤቶችና የክልል መንግስታት በተለይም የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ ህጉን ተፈጻሚ ማድረግ ዋና ስራ ቢሆንም ከዚህ ጎን ለጎን ግን የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማዳበር ስራ መሰራት አለበት፤ አመዛኙ ስራም መከናወን የሚገባው በዚህ ደረጃ ነው፡፡
የትግራይ ክልል ከዚህ አንጻር ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው፤ ክልሉ በምርጥ ተሞክሮው የአለም ጤና ድርጅት ጭምር የመሰከረለት መሆኑን ገልጸዋል፤ ክልሉ ለእዚህ ውጤት የበቃው የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋቱና በስራው ላይም ተሳትፎ እንዲያደርግ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱ መሆኑን አስረድተዋል።
በዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በዓመት ሰባት ሚሊዮን ህዝብ ከማጨስ ጋር በተያያዘ ህይወቱን ያጣል።

በአዲስ አበባ 13 የግል ትምህርት ቤቶች ያልተገባ ክፍያ በመቀበላቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው


በአዲስ አበባ የሚገኙ 13 የግል ትምህርት ቤቶች ያልተገባ ክፍያን ከተማሪ ወላጆችን ከማስከፈል ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው የትምህርት ተቋማት ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ያሉ መሆናቸውን በአዲስ አበባ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት እና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ አሳውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ብሩክነሽ አርጋው እንዳሉት ተቋማቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በሚል ተጨማሪ ክፍያ ከወላጆች በመውሰዳቸው ነው።
በተደረገ ክትትል እና ፍተሻም ተቋማቱ ለመማሪያ ቁሳቁስ በሚል ከወላጆች የተቀበሉትን ገንዘብ እና ተጨማሪ የመማሪያ ቁሳቁሶችም ለወላጆች እንዲመለሱ መደረጉን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
ሌሎች ተቋማት ላይም ይህን መሰል ድርጊት እንዳይፈፅሙ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።
እነዚህ ተቋማትም በድጋሚ ይህን ተግባር የሚደግሙት ከሆነ እርምጃ የሚወሰድባቸው እንደሚሆንም ኤጀንሲው ገልጿል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ተቋማት የውጭ ፍተሻ ስራ ትናንት በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፥ የፍተሻ ስራው ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ባሉ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ነው የሚሰጠው።
ኤጀንሲው እስካሁን ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ተያይዞ ችግር አለባቸው ለተባሉ 99 የመንግስትና 5 የግል የትምህርት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
እነዚህ ተቋማት ከነበሩበት ደረጃ የማይሻሻሉና ያሉባቸውን ችግሮች የማይቀርፉ ከሆነም እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።

 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዙፋን ካሳሁን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2010

ሐሙስ 15 ፌብሩዋሪ 2018

https://youtu.be/CCcXpWRSx1o

ሰበር ዜና... ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

አዲስ አበባ የካቲት 8/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢህአዴግ ሊቀመነበርነትና ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በአገሪቱ የተፈጠረው አሳሳቢ ሁኔታ እልባት እንዲያገኝ የመፍትሄው አካል ለመሆን ነው ብለዋል።
ከስልጣን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ ድርጅታቸው ደኢህዴን የተቀበለው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል።


ረቡዕ 14 ፌብሩዋሪ 2018

ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች

 ታዋቂ ፈላስፋዎችን፣ ሳይንቲስቶችን እና ለዓለም ስልጣኔ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ ሰዎችን እናስተዋውቃችኋለን። እስቲ ልጆች የዓለም ስልጣኔ እዚህ እንዲደርስ ትልቅ ድርሻ አላቸው የምትሏቸውና ከዚህ ቀደም እናንተ ከምታው ቋቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን አስታውሱ። ሊደነቁ ይገባል አይደል? መልካም ልጆች ሁሉም ሰው በእኩል ደረጃ ለዓለም መሰልጠን እና 
አቅማችን ከተጠቀምንበት አዲስ ነገር ለመሥራት እና ለመፍጠር እኛ የሰው ልጆች ከሌላው የዓለም ፍጡር በተለየ መንገድ ልዩ ስጦታ ታድለናል። ታዲያ እናንተ ምን አሰባችሁ? አዲስ እና ጠቃሚ ነገር ለአገራችሁ ብሎም ለዓለም ህዝብ ለመሥራት ተዘጋጃችሁ? መልካም ጥሩ ምሳሌ እንዲሆናችሁ ለዛሬ የኬሚስትሪ ሊቅ የሆነውን እና ለዓለም ስልጣኔ የራሱን ድርሻ ስለተወጣው ሊውስ ፓስተር እንነግራችኋለን።
1. እ.አ.አ በ18 22 ተወልዶ እስከ 1895 የኖረው የኬሚስትሪ ምሁር እና ማይክሮ ባይሎጂስቱ ሊውስ ፓስተር የምግብ መመረዝን የሚፈውስ «አንቲ ዶትን» ጨምሮ በርካታ በሽታዎችን የሚያድኑ መድሀኒቶችን ለዓለም አበርክቷል።
2. ይህ እውቅ ሳይንቲስት ወተትን ፓስቾራይዝድ እንዲሆን እና ለቲቢ በሽታ የሚያጋልጠውን «ቱውበ ርክሎስስ» ለማስወገድ እንዲጠቅም የማድረግ ዘዴን አስተዋውቋል። ይህ ሰው ጀርም ከማንኛውም ቁስ ጋር በሚደረግ ንክኪ እንዴት ሊፈጠር እንደ ሚችልም ባደረገው ምርምር መሰረት ድንገት የማይፈጠር እና በሂደት በንክኪ የሚመጣ መሆኑን አረጋግጧል።
3. በምሥራቅ ፍራንስ በ«ዶል» ከተማ የተወለደው ሊውስ ፓስተር በዋናነት ስለ ጀርም አፈጣጠር ጥናት አድርጓል። ይህ ሰው በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ በመባል ህመም ላይ ሰፊ ጥናት በማድረግ መድሀኒት መፍጠር ችሏል።
4. ሊውስ በህይወቱ ጠንካራ ሠራተኛ ለመሆን ይተጋ ነበር። አብዛኛውን ጊዜውንም በምርምር በላቦራቶሪው ውስጥ ያሳልፍ ነበር። በዚህም የበርካታ በሽታዎችን መድሃኒት ለማግኘት ችሏል። በተለያየ ጊዜ ትምህርቱን ቢከታተልም በ1847 ግን በምርምር ሥራ የዶክትሬት ዲግሪውን ማግኘት ችሏል። አጋሮቹም ሁል ጊዜ ስለሥራ ጥሩነት ያወራቸው ነበር።
ልጆች ዛሬ ስለ ሊውስ ፓስተር በጥቂቱ አውርተናችኋል። ከዚህ ሰው የሥራ ክቡርነትን፣ የሰው ልጆች ላይ ችግር ሆነው የቆዩ በሽታዎችን የሚያድን መዳህኒት ለማግኘት የተደረገ ጥረት እና ስኬትን እንደተማራችሁበት አንጠራጠርም። ስለዚህ በህክምናው ዘርፍ ላይ ለመሰማራት እና ልክ እንደ ሊውስ ፓስተር አስተዋፅኦ ለማድረግ የምትፈልጉ ጥሩ ትምህርት እንደም ትወስዱበት አንጠራጠርም። 
 


ምንጭ፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ  ማህበራዊ አምድ

ዓርብ 2 ፌብሩዋሪ 2018

61 የሀገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዳቸው ተሰረዘ



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 77ኛ ዓመት ቁጥር 145 ባወጣው ማስታወቂያ የሀገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በቢሮው በስራና ሠራተኛ ማገናኘት አግልግሎት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አውጥተው ይሰሩ የነበሩ ቢሆንም የዕድሳት ጊዜያቸውን በወቅቱ ባለመፈፀማቸው ምክንያት በአዋጅ ቅጥር 632/2001 አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 1/መ/መሠረት ከጥር 01 ቀን  2010 ዓ.ም ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃዳቸውን ሰርዟል፡፡ 











ሐሙስ 25 ጃንዋሪ 2018

ከ200 ሺህ የተጣሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች የተሰራው የዓለማችን ትልቁ ቲ ሸርት

መቀመጫውን ህንድ ሙንባይ ያደረገው ፕላስቲንዲያ ኩባንያ ግን የአካባቢ ስጋት የሆነውን ፕላስቲክ ለመልካም አላማ ለማዋል በማሰብ ከተጣሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ቲ ሸርት ሰርቷል። 
ኩባንያው ቲ ሸርቱን ለመስራት 200 ሺህ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ከሰበሰበ በኋላ አንድ ላይ በመፍጨት ወደ ክርነት ቀይሯቸው ነው 4 ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ልብስ የሰራው።
ቲሸርቱን አንድ ላይ ለመስፋትም 15 የዓለም አቀፉ ኪንትን አልባሳት አምራች ልብስ ሰፊዎች እና 60 በጎ ፍቃደኞች እንደተሳተፉበት ነው የተነገረው።
የዓለም ድንቃ ድንቅ ስራዎችን የሚመዘግበው ጊነስ ወርልድ ሪከርድስም ቲሸርቱን ለመለካት ቡድኑን ወደ ስፍራው የላከ ሲሆን፥ ቡድኑ ቲሸርቱን ዘርግቶ የሚለካበትን ባዶ እና ሰፊ ስፍራ ለማፈላለግ እና ለክቶ ለማጠናቀቅ 45 ቀን እንደፈጀበት ነው የተነገረው።
በዚህም አረንጓዴ እና ነጭ ቀለም ያለው ቲሸርት 96 ነጥብ 86 ሜትር ቁመት እና 69 ነጥብ 77 ሜትር ስፋት እንዳለው የተለካ ሲሆን፥ በተሳካ መልኩም የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር ችሏል ነው የተባለው።
ህንዱ ፕላስቲንዲያ ኩባንያ ክብረ ወሰኑን በእጁ እንዳስገባ ካረጋገጠ በኋላም በመደበኛ መጠኖች የተሰሩ 10 ሺህ ቲ ሸርቶችን በአካባቢው ለሚገኙ ችግረኛ ህጻናት አከፋፍሏል።
ክብረ ወሰኑ ከዚህ ቀደም በብራዚል በተሰራው እና 93 ነጥብ 2 ሜትር ቁመት እና 62 ነጥብ 73 ሜትር ስፋት ባለው ቲሸርት ነበር ተይዞ የነበረው።

ረቡዕ 17 ጃንዋሪ 2018

ብራዚላዊው ኮከብ ሮናልዲንሆ ከእግር ኳስ ጨዋታ ራሱን አገለለ

ብራዚላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ርናልዲንሆ የእግር ኳስ ጨዋታን በይፋ ማቆሙ ተገለፀ። ከሀገሩ ብራዚል ጋር የዓለም ዋንጫን ያነሳው ሮናልዲንሆ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2015 ወዲህ የእግር ኳስ ጨዋታ አድርጎ አያውቅም።
የ37 ዓመቱ ሮናልዲንሆ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2002 የዓለም ዋንጫን ያነሳው የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ውስጥ ቁልፍ ሚና ነበረው።
እንዲሁም በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2006 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ከባርሴሎና ጋር ያነሳ ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 2005 ደግሞ የዓለም ኮከብ ተጫዋች ተብሎ በባላድኦር ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የፈረንጆቹ 2004፣ 2005 የፊፋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እና በፈረንጆቹ 2006 የአውሮፓ ክለቦች የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ጨምሮ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል።
ወንድሙ እና መኪሉ የሆነው ሮቤርቶ አሲስ፥ ሮናልዲንሆ የእግር ኳስ ጨዋታን ሙሉ በሙሉ ማቆሙን በትናንትናው እለት አረጋግጧል።
ለእግር ኳሱ ኮከብ በብራዚል፣ በአውሮፓ እና በእሲያ የመሸኛ ስነ ስርዓት ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያለው ወኪሉ፥ ከብራዚል ብሄራዊ ቡድን ጋር በመሆንም ልዩ የሆነ ነገር ለማዘጋጀት አስበናል ብሏል።
ሮናልዲኒሆ የእግር ኳስ ጨዋታን በብራዚሉ ጀርሚዮ የጀመረ ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 2011 ወደ ፈረንሳዩ ፒ.ኤስ.ጂ በዝውውር እስኪሄድ ድረስም በጀርሚዮ ሲጫወት ቆይቷል።
በስፔኑ ባርሴሎና ለ5 ዓመታት በነበረው ቆይታም 2 የላሊጋ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻለ ሲሆን፥ ወደ ጣሊያኑ ኤ.ሲ ሚላን በማቅናትም የፈረንጆቹ 2010-11 የሴሪ አ ዋንጫን ማንሳት ችሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ (ኤፍ.ቢ.ሲ) 

ሐሙስ 11 ጃንዋሪ 2018

ዓለም አቀፉ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

 ዓለም አቀፉ የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አውደ ርዕይ በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።    
የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር አውደ ርዕዩን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
አውደ ርዕዩ 'ሆርቲ ፍሎራ ኤክስፖ 2018' በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።             
በአውደ ርዕዩ ላይ ለመሳተፍ 120 የአገር ውስጥና የውጭ አምራቾች፣ ግብዓት አቅራቢዎች፣ አማካሪዎች፣ ገዥዎችና ባለድርሻ አካላት መመዘገባቸው ተገልጿል።
ለሦስት ቀናት ከሚካሄደው ከዚህ መርሀ ግብር ጎን ለጎን የቢዝነስ ስብሰባዎች፣ የሚመለከታቸው አካላት የሚሳተፉበት አውደ ጥናቶችና የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻ ልማት ሥራዎች ይጎበኛሉ ተብሏል።         
የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ እንደገለጹት፤ ኢንዱስትሪው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ በፍጥነት እያደገ መጥቷል።   
ኢትዮጵያ አበባን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጸው፤ በአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ያለውን እምቅ አቅም ወደ ወጪ ንግድ በመቀየር የሚጠበቀው ገቢ እንዲገኝ ማኅበሩ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እየሰራ ነው ብለዋል። 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በርካታ የውጭ መዳረሻዎች ያሉት በመሆኑ፤ ለማምረት ምቹ የሆነ የአየር ንብረት መኖሩ፣ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አገልግሎት መጀመሩ ለሚጓጓዘው አትክልትና ፍራፍሬ "ትልቅ እመርታ ነው" ብለዋል። 
ከአውስትራልያ፣ ከጃፓን፣ ከአሜሪካ፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአፍሪካ አገሮች በአጠቃላይ ከ40 አገራት በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች በአውደ ርዕዩ ላይ እንደሚሳተፉ አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል።  
የአውደ ርዕዩ መካሄድ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ከማሳየት ባለፈ አገሪቷ በመስኩ ተሰማርተው የሚገኙ ኩባንያዎች ልምድ እንዲቀስሙ እድል እንደሚፈጥርም ጠቅሰዋል።     
ከዚህ ባለፈ በመንግሥት የተለዩ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ቦታዎች ለዓለም አቀፉ ተዋንያኖች ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።    
የተለያዩ አበባዎች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች፣ ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀርቡ ጠቅሰው፤ ክልሎችም በመስኩ ያላቸውን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በስፋት ያስተዋውቃሉ።    
የኃይል መቆራረጥ፣ አንዳንድ አሰራሮች መጓተት፣ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዳንሆን እየደረገ በመሆኑን ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
አውደ ርዕዩ ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን፤ ከየካቲት 7 እስከ 9 ቀን 2010 ዓ.ም እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል።    
sourse : ENA

በመዲናዋ የኩላሊት ህክምናን በአንድ ቦታ የሚሰጥ ማዕከል ሊቋቋም ነው

 በአዲስ አበባ ሁሉንም የኩላሊት ህክምናዎች በአንድ ቦታ ለመስጠት የሚያስችል ማዕከል ሊያቋቁም መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በመላው ዓለም ግማሽ ቢሊዮን ህዝብ ጽኑ የኩላሊት ህመምተኞች ሲሆኑ፥ ከዚህ ውስጥ 78 በመቶ ያህሉ በታዳጊ አገራት እንደሚገኙ የዓለም የጤና ድርጅት ከአንድ ዓመት በፊት ያወጣው መረጃ ያስረዳል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የኩላሊት ህመም ከ15 ዓመት በፊት ከነበረበት 25ኛ ደረጃ ገዳይ በሽታነት ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት 15ኛው ገዳይ ህመም ሆኗል።
በኢትዮጵያ በየዓመቱ የኩላሊት ህክምና የሚያስፈልጋቸው ህሙማን ቁጥር 60 ሺህ መድረሱን የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር መረጃ ያመለክታል።
በሚኒስቴሩ የክሊኒካል አገልግሎት ተወካይ ዳይሬክተር ዶክተር ይበልጣል መኮንን እንደገለጹት፥ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል።
በዚህም ህክምናውን ለሚፈልጉ ዜጎች የተሟላ የኩላሊት ህክምናዎችን ያካተተ ማዕከል ለማቋቋም የሰው ሀይል የማደራጀት፣ በጀት የማዘጋጀትና ሌሎች የዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው።
በ14 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚገነባው ይህ ማዕከል በኢትዮጵያ እና በኳታር መንግስት ድጋፍ በአዲስ አበባ ሚኒሊክ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ እንዲቋቋም መወሰኑን ዶክተር ይበልጣል ገልጸዋል።
ማዕከሉ የኩላሊት እጥበት፣ ንቅለ ተከላ፣ የኩላሊት ህክምና ማሰልጠኛ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያካተተ እንደሚሆንም አብራርተዋል።
በተጨማሪም 50 የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ ማዕከላትን በዩንቨርሲቲ ሆስፒታሎች እና በሌሎች ተቋማት በማቋቋም በሁሉም ክልሎች ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።
በኬሚካሎች እና በምግብ መመረዝ ምክንያት ለሚፈጠሩ ህመሞች ህክምና የሚሰጡ ማዕከላትንም በክልሎች ለማስፋፋት መታቀዱን ጠቅሰዋል።
የደም ግፊት፣ የስኳር ህመም፣ መመረዝና ኢንፌክሽኖች ለጽኑ የኩላሊት ህመም መንስኤዎች ሲሆኑ፥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አትክልቶችን እና ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ አልኮል እና ሌሎች እፆችን አለመውሰድ ከህመሙ መከላከያ መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ። 


ምንጭ፦ (ኤፍ.ቢ.ሲ)ኢዜአ

ረቡዕ 10 ጃንዋሪ 2018

ሶስቴ ለመደገስ አቅም የለኝም ያለው ሰው በአንድ የሰርግ ስነ ሰርዓት ሶስት ሚስቶችን አግብቷል

 ሶስት ሚስቶችን ለማግባት ሲሰናዳ የኖረው ሰው የተለያዩ ሰርጎችን የመደገስ አቅም የለኝም በሚል በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ሶስት ሚስቶችን አግብቷል። የ50 ዓመት ዕድሜ ያለው ኡጋንዳዊው መሃመድ ሰማንዳ፥ በፈፀመመው ተግባር የአፍሪካን መገናኛ ብዙሃን ቀልብ ስቧል ነው የተባለው። 
ሰማንዳ ሶስቱን ሴቶች ለማግባት ቢፈልግም፥ ለእያንዳንዷ ሴት በተለያዩ ጊዜያት ሰርግ የመደገስ አቅም የለኝም ሲል ተናግሯል።
ሰማንዳ በኡጋንዳ ዋኪሶ ግዛት ነዋሪ ሲሆን፥ ምግብ በመሸጥ የሚተዳደር ነው። የ50 ዓመቱ ሰው ያገባቸው ሶስቱም ሴቶች ምንም ዓይነት ቅናት እንደሌለባቸው የገለፀ ሲሆን፥ ኑሯቸውን ለመደገፍ ጠንክሮ እንደሚሰራ ነው የተናገረው።

ምንጭ፦ (ኤፍ.ቢ.ሲ) www.odditycentral.com

ማክሰኞ 2 ጃንዋሪ 2018

በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች እየተሠሩ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአ ንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ አራት ዕቃ ጫኝ  ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ውል ገብቶ እያሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የአየር መንገዱ የካርጎ ከፍል ዋና ሃላፊ  አቶ ፍጹም አባዲ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ  በብድር በተገኘ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ  እያንዳንዳቸው በአንድ ጊዜ 103 ቶን ዕቃ የመጫን አቅም ያላቸው አራት  አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ውል ፈጽሟል፡፡
አራቱ ቦይግ 777 ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች ከአፍሪካ፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ ባንኮችና አበዳሪ ድርጅቶች በተገኘ ብድር የሚገዙ  መሆናቸውን  ጠቅሰው፤ የአውሮፕላኖቹ  ግንባታ ተጠናቆ ቅብ ደረጃ በመድረሳቸው ከመ ጪው ዓመት መስከረም 2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ብለዋል፡፡
የደንበኞችን ፋላጎትና የካርጎ አገልግሎቱን ለማጣጣም አየር መንገዱ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተው፤ አዳዲሶቹ  አውሮፕላኖችም የአገሪቱን የወጪና የገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡
አዲሶቹ አውሮፕላኖች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ የአየር መንገዱን የዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች ቁጥር ወደ 12 እንደሚያሳድገው ጠቁመው፤ አየር መንገዱ ከሚያጓጉዛቸው ዕቃዎች መካከል በዋነኝነት የአበባ ምርትን ጨምሮ የግብርና ምርቶች፣ ጨርቃጨርቅና የተለያዩ  የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችና የመኪና መለዋወጫዎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል አየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ በዓመት 350 ሺ ቶን  ዕቃ  የሚያስተናግዱ መጋዝኖች እንዳሉት ገልጸው  በ150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በዓመት 600 ሺ ቶን ዕቃዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው መጋዘን አስገንብቶ ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ ይህም  የካርጎ አገልግሎቱን የተሻለ እንደሚያደርገው ነው የገለጹት፡፡
በአሁኑ ጊዜ አየር መንገዱ ከ100 ቶን በላይ አቅም ያላቸው ዘመናዊ ስድስት ቦይግ 777 የሚባሉ አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን፤ በጥቅሉ የስምንት ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖች ባለቤት ነው፡፡ በእነዚህም አውሮፕላኖች ወደ 44 መዳረሻዎች በመብረር በዓመት 400ሺ ቶን ዕቃዎችን ያጓጉዛል፡፡
አዲስ ዘመን (ጌትነት ምህረቴ)

የመሊ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ወደ መደበኛ ምርት ገባ

 በሙከራ ምርት ላይ የቆየው የመሊ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ መደበኛ ምርት ጀመረ።
ፋብሪካው የሚገኝበት በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን በአስገደ ፅምብላ ወረዳ ሲሆን፥ በ1999 ዓ.ም በውጭ አገር አማካሪ ድርጅት ተጠንቶ በ2004 ዓ.ም ህጋዊ የስራ ፈቃድ ማግኘቱን ተነግሯል።
የትእምት እህት ኩባንያ በሆነው ኢዛና ማዕድን ልማት ኩባንያ ስር የሚገኘው መሊ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ፥ በአሁኑ ወቅት በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ኪሎ ግራም ወርቅ እያመረተ መሆኑን የፋብሪካው ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ፀጋይ አሰፋ ገልፀዋል።
ፋብሪካው በቀጣይ አቅሙን በማሳደግ እስከ 4 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም በቀን ለማምረት እቅድ መያዙንም ዋና ስራ አስከያጁ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በፋብሪካው ከ200 በላይ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩም ተጠቁሟል።
የፋብሪካው ምክትል ስራ አስከያጅ እና የጂኦሎጂ ባለሙያ አቶ ወንድወሰን አረጋኸይ፥ ወርቅ ባለበት ቦታ 600 ሜትር ስፋት ያለው ቁፋሮ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት መደረጉን ገልፀዋል።
ከዚህም እስከ አሁን ስድስት ሜትር አካባቢ ተቆፍሮ ወርቅ በማንጠር ላይ ነው ሲሉ አቶ ወንድወሰን ተናግረዋል።
ፋብሪካው በ2010 ዓ.ም ለሀገሪቱ ከ40 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

መንገደኞች ለግል መገልገያ ብቻ የሚጠቀሙባቸውን እቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ ከታክስ ነጻ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ መመሪያ ይፋ ሆነ

መንገደኞች ለግል መገልገያ ብቻ የሚጠቀሙባቸውን እቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ ከታክስ ነጻ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ መመሪያ ይፋ ሆነ። ለንግድ የማይዉሉ ወደ አገር ዉስጥ የሚገቡ የግል መገልገያ እቃዎችን ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው እንዲገቡ የወጣውን መመሪያ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፤ በጉምሩክ አዋጁ ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ መላካቸውን በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የህግ አገልግሎት ዳይሬክሩ አቶ ቦቹ ስንታየሁ ገልጸዋል።
መመሪያው በአየርም ሆነ በየብስ ከውጭ አገር የሚመጡ መንገደኞች፣ ተመላሽ ኢትዮጵያውያንና በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችም በመመሪያው ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው የተባለው።
መመሪያው ከታህሳስ 6 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የፀና መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ መንገደኞችም የኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት ህትመት እና ኮፒ አገልግሎት እቃዎችን፣ የሙዚቃ ማጫወቻ እና ተዛማጅ መሳሪያዎች፣ ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚዉሉ የማብሰያ እና መሰል እቃዎችን በነጻ እንዲገቡ ፈቅዷል።
በተጨማሪም ሌሎችም በ26 አይነት የተመደቡ 351 መገልገያ የእቃ አይነቶች ላይ የሚገቡበትን ብዛትና መጠን መመሪያው አካቷል።
ለምግብነት የሚያገለግሉ እቃዎች እስከ 20 ኪሎ በጉዟቸው ወቅት እንዲያስገቡና እንዲያስወጡ ሲፈቀድ፥ ሁለት ሞባይል ቀፎዎችና ኤክስተርናል ሃርድዲስክ እንደዚሁም ቴሌቪዥን ከነስታንዱ፣ መገልገያ ካሜራ፣ ላፕቶፕ ኮምፒተር አንዳንድ ይዞ እንዲሁም፥ አምስት ፍላሽ ዲስኮች ማስገባት እንደሚቻልም በመመሪያው ተካቷል።
በመመሪያው ያልተካተቱ ሌሎች እቃዎች ሲመጡም በልዩ ሁኔታ በባለስለጣኑ ዉሳኔ እንደሚሰጥባቸው ነው የተነገረው።
በዚህም ወጥ በሆነ የታሪፍ ምጣኔ የማይስተናገዱ እቃዎችም ባለመብቱ ሊገለገልበት ከሚችለው መጠን በላይ በተደጋጋሚ ሲያስገባ፣ ለንግድ የሚዉሉ መገለገያ እቃዎችን ሲያስገባና ለንግድ የማይዉሉ ተብለው ከተቀመጠው መመሪያ ዉጭ የሆኑ ዕቃዎችን የሚያስገባ ከሆነ ዕገዳ ይጣልበታል።
ዳይሬክተሩ ለመገልገያ ተብለው የሚገቡ እቃዎችን ለንግድ ስራ ማዋል እንደማይቻል ገልጸዋል።
 (ኤፍ. ቢ. ሲ.)