ጎግል የተባለው መረጃ መረብ ከአሜሪካ የአእምሮ ህክምና ተቋም ጋር በመተባበር የጀመረው ይህ አዲስ ፕሮጀክት የሙከራ ስራውን በአሜሪካ ብቻ የተወሰነ ቢሆንም እንደውጤቱ ወደ የተለያዩ የአለም ሀገራት የሚሰራጭ ይሆናል፡፡
በዚህም መሰረት አንድ ተጠቃሚ ከጭንቀት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለመፈለግ ጎግልን በሚከፍትበት ወቅት ተጠቃሚው ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ችግሮች ካሉበት በራሱ እንዲያረጋግጥ ጎግል ጥያቄ የሚቀርብለት ይሆናል፡፡
የአሜሪካ የአእምሮ ህክምና ተቋም እንዳለው ይህ አሰራር የጭንቀት ችግር ያለባቸውም ሆኑ የሌለባቸው ሰዎች በየጊዜው ሃኪም ቤት የሚመላለሱበትን ጊዜ የሚቆጥብ እና ሁኔታቸውን ለማወቅ ለማግኘት ግዴታ ሀኪም ቤት ድረስ መሄድ የለባቸውም፡፡
ስለ ፕሮጀክቱ አሰራር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው አላማው በህክምና ማዕከላት የሚሰጠውን ሙሉ አገልግሎት ለመሸፈን ሳይሆን ችግሩ በመጀመሪያ የህመም ደረጃው ላይ ለማስቆም ወይም ጉዳቱን ለመቀነስ እንዲያስችል ነው፡፡
በአገልግሎቱ ለመጠቀምም “የጭንቀት ችግር እንደሌለቦት ያረጋግጡ” የሚል ጥያቄ የሚመጣ ሲሆን ይህም ተጠቃሚው ያለበትን የጭንቀት ደረጃ በማሳየት ምን አይነት እርዳታ እንደሚያስፈልገው ያሳውቀናል፡፡ ስለዚህ ጭንቀታቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች በፍጥነት ህክምና እንዲያገኙ ይጠቁማቸዋል፡፡
ይህ ፒ ኤች ኪው ናይን የተሰኘው ፈጠራ አእምሮን ሊፈትኑ የሚችሉ ነገር ግን ቀላል የሆኑ 9 ጥያቄዎችን ብቻ በመጠየቅ የመላሹን የጭንቀት መጠን ያሳውቃል፡፡ ሙከራ ላይ በመሆኑ አሁን አገልግሎቱን የሚያገኙት በስልክ ብቻ ነው፡፡ በአሜሪካ በየአመቱ ከ3 ሚሊዮን በላይ ህዝቦች በጭንቀት በሽት ይጠቃሉ፡፡( ምንጭ:ቢቢሲ)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ