በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተዘጋጀ አንድ የሙዚቃ ድግስ ላይ የሴቶችን የመዋኛ ልብስ ተጠቅሞ በስፍራው ከነበሩ ሰዎች ሰዎች ኪስ በመበርበር 53 ስልኮችን የሰረቀው ግለሰብ በሶስት ዓመት እስር ተቀጥቷል።
ወጣቱ ሮማኒያዊ ሲሆን አሊን ማሪን ይባላል፤ የ22 ዓመት ወጣት ነው።
ማሪን በበርሚንግሃም በተዘጋጀ አንድ የሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቁር እና ሃምራዊ ቀለም ያለው ከሰውነት ጋር ጥብቅ የሚል እና ሲያስፈልግ የሚለጠጥ የሴቶች የመዋኛ ልብስ ከውስጥ እና ጥንድ ጂንስ ሱሪ ለብሶ ታድሟል።
በዚህ መልኩ በሙዚቃ ድግሱ ሰዎች በጣም ተጠጋግተው በሚጨፍሩበት አካባቢ ይጠጋል።
ይህን ያደረገውም በርካታ ሰዎች እየተገፋፉ ስለሚጨፍሩ እና ከፍተኛ ድምፅ ስላለ ከታዳሚያኑ ኪስ እየገባ ለመስረቅ እንዲያመቸው ነው።
በዚህም መሰረት ስልኮችን ከሚጨፍሩት ሰዎች ኪስ ያምንም ስጋት እያወጣ ከውስጥ በለበሰው የሴቶች የመዋኛ ልብስ ማስቀመጥ ጀመረ።
በዚህ ጊዜ በአጠቃላይ በሰውነቱ ውስጥ 53 ስልኮችን የያዘ ሲሆን፥ ይህም ህይወት ያለው ሳጥን አስመስሎታል።
ዓላማውን ያሳካው ወጣቱ ማሪን ከሙዚቃ ድግሱ ለመውጣት ሲያስብ ድንገት በዙሪያው የነበሩ የደህንነት ሰዎች ዓይን ውስጥ ገባ።
በተጨናነቀው የህዝብ ብዛት ውስጥ የፀጥታ ስራን እየተከታተሉ የሚገኙት የደህንነት ሰዎች፥ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ዝርፊያ መከናወኑን መረጃው ስላላቸው በማሪን ላይ ክትትል ማድረግ ጀመሩ።
ማሪን በሙዚቃ ድግሱ በርካታ ሰዎች ከተጨናነቁበት ቦታ ለመራቅ ጥረት ሲያደርግ በደህንነት ሰዎች እጅ ገባ።
ስልኮችንም በመኪና ማቆሚያ አቅራቢያ ለማስቀመጥ ሲሞክር ነው የታየዘው።
የበርሚንግሃም ከተማ ፖሊስ መኮንን ጁሊያ ስላተር እንደተናገሩት፥ ማሪን ያካሄደው የኪስ ስርቆት በተጠና እና በታቀደ ሁኔታ የተፈፀመ ነው።
በርካታ ስልኮች በሙዚቃ ድግሱ ከታደሙ ሰዎች ንብረታቸውን በጥንቃቄ ያስቀምጥልናል ብለው ካሰቡት የፊት የጅንስ ኪስ ነው የተሰረቁት።
ሰዎቹ ስልካቸውን ማንም ሊነካው የማይችል ቦታ ላይ አስቀምጥናል ብለው በነፃነት በሚጨፍሩበት ጊዜ መዝናናቱ ሁሉን ነገር ስልሚያስረሳቸው ማሪን በቀላሉ ስልኩን ለመስረቅ አመች ሆኖለታል ይላሉ የፖሊስ መኮንኑ።
ስርቆቱ ከተፈፀመ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላም የበርሚንግሃም ንጉሳዊ ፍርድ ቤት የዙፋን ችሎት በያዝነው ሳምንት በማሪን ላይ የሶስት ዓመት የእስር ቅጣት በይኖበታል።
ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ)ኦዲቲ ሴንትራል

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ