ረቡዕ 28 ኦክቶበር 2020

HELEN & LWAM Ethiopian Amharic music reggae cover (2020) የአማርኛ ሬጌ ሙዚቃ

ዳዊት በቀለ Dawit Bekele New Ethiopian Amharic music Cover አዲስ ከቨር (2020)

ሜሮን መከተ Meron Mekete Dinget Salasebew Amharic cover Ethiopian Music (2020)

ፀደይ ገፃዲቅ ምርጥ ከቨር ካህኔ Tsedey GTsadik Amharic Cover New Ethiopian Music

ሜሮን መከተ Meron Mekete Ethiopian music 90's cover (2020)

ከቨር ESMIZ MAN Cover Music (New Ethiopian Music 2020)

ረቡዕ 29 ጁላይ 2020

#የሄፒታይተስ በሽታ ስርጭት ሰፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን መጠብቅ አለበት- የጤና ሚኒስቴር


ሄፒታይተስ (የጉበት በሽታ) እንደ ሌሎች በሽታ አጀንዳ ሆኖ ብዙ ባይሰራበትን ስርጭቱ ሰፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ራሱን ከዚህ ቫይረስ ሊጠብቅ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ አሳሰቡ።

ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ዱጉማ  ዛሬ አለም አቀፍ የሄፓታይተስ ቀን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሄፓታይተስ በሽታ አሁን ላይ ከአለም በገዳይነቱ በ2ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በመሆኑም መንግስት ከመቼውም በላይ  በሄፒታይተስ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው መሆኑንም አስታውቅዋል።

በዚህም ቫይረሱን ለመከላከል ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ተጋላጭ ለሆኑ ከ675 ሺህ በላይ የጤና ባለሙያዎች ክትባት መሰጠቱ ተጠቁሟል።

ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ በመደበኛ የክትባት መርሃግብር ተካቶ ለህጻናት እየተሰጠ ነውም ተብሏል። 

ዛሬ አለም አቀፍ የሄፓታይተስ ቀን በአለም ለ10ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ7ኛ ጊዜ “ከጉበት በሽታን ነጻ የሆነን ነገን እንፍጠር”  በሚል መሪ ቃል እናቶች እና ህጻናት በጉብት በሽታ እንዳይያዙ በሚደረግ ጥረት ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል ተብሏል። 

በአለም በየአመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች በሄፓታይተስ በሽታ እንደሚሞቱ መረጃዎች ያመካክታሉ። 

በሃኢትዮጵያም  በሽታው በስፋት ከተሰራጨባቸው ሀገራት ስትመደብ በ2017 በተሰራ ጥናት 9 ነጥብ 4 በመቶ በሄፓታይተስ ቢ እንዲሁም 3 ነጥብ 1 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ሄፓታይተስ ሲ እንዳለባቸው ይገመታል።

በሀይማኖት እያሱ

ሐሙስ 4 ጁን 2020

ተጨማሪ 150 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 5141 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 150    ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1636  መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠ ሰዎች ከ 3   እስከ 72   ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ  94   ወንድና  56  ሴት ሲሆኑ፤  147 ኢትዮጵያውያንና ሶስቱ  የውጭ ዜጎች መሆናቸው ታውቋል ::

ማክሰኞ 2 ጁን 2020

#ሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል ጀመረ

ሁለት ወራት ማዕከሉን የማደራጀት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን ገልጸዋል።

ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።

ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።

በማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማንና ለጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ጠቅሰዋል።

በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ነርሶችና ዶክተሮች ሥልጠና ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት የማዕከሉ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ ህሙማንን መቀበል መጀመሩን ነው ዶክተር እስማኤል መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።