ዓርብ 29 ዲሴምበር 2017

በፍሎሪዳ የተደረገው የባህር ውስጥ ሰርግ ብዙዎችን አስደምሟል

ከአራት ዓመት በፊት በመምህር እና አስተማሪነት የተገናኙት ጥንዶች በፍሎሪዳ አካባቢ በባህር ውስጥ ያደረጉት ሰርግ የብዙዎችን ቀልብ መሳቡ ተነግሯል።
የብሪታንያ መከላከያ ሀይል አባል የሆነው የ31 ዓመቱ ቶማስ ሞልድ እና የአሜሪካ ዜግነት ያላት አስተማሪው ሳንድራ ሀይድ፥ ከአራት ዓመት በፊት የውሃ የመጥለቅ ስልጠና ነበር በፍቅር ያገናኛቸው። ጥንዶቹ አራት አመት የቆየው የፍቅር ቆይታ በትዳር እንዲጣመሩ ምክንያት መሆኑን ተነግሯል።
ስለሆነም በፍሎሪዳ ሞላሰስ በሚባል ትልቅ የባህር ጠረፍ አካባቢ በሚገኘው የተቀደሰ ስፍራ የሰርግ ስነ ሰርዓታቸውን በባህር ውስጥ አካሂደዋል።
እነዚህ ባልና ሚስት በባህር ውስጥ አበባ ሲቀባበሉ እና የሰርጋቸው ስነ ስርዓት ሲፈፅሙ ከመካከላቸው አንድ ሰው ብቻ ነው የነበረው።
በዚህም በሰርጋቸው የተነሱት ፎቶግራፍ በግዛቲቱ የቱሪዝም የፌስ ቡክ ገፅ እንዲለጠፍ መደረጉን ተነግሯል።

ምንጭ፦(ኤፍ.ቢ.ሲ) www.upi.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ