ሰኞ 19 ፌብሩዋሪ 2018

ህጉን ተፈጻሚ ለማድረግ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል

አገሪቱ ሲጋራ ማጨስ መቆጣጠርን አስመልክቶ የትንባሆያጸደቀቻቸውን አለም አቀፍ ኮንቬንሽን እንዲሁም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ የወጣውን የማስፈጸሚያ አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስፋት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ የህግ ክፍል ዳይሬክተር ወይዘሮ አብረኸት ግደይ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተ ናገሩት፤ ትምባሆን መጠቀም እንደ አገር ጎጂ በመሆኑ ምርቱ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል። አገሪቱ ያጸደቀችውን ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ወደ ተግባር ለመቀየርና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አወጅ ቁጥር 822/2006 ተፈጻሚ ለማድረግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት ተሰጥቶታል።
የቁጥጥር ስራው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብቻ ተሰርቶ ውጤታማ እንደማይሆን ዳይሬክተሯ ጠቅሰው፤ የሚመለከታቸው የዘርፍ መስሪያ ቤቶችና የክልል መንግስታት በተለይም የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ ህጉን ተፈጻሚ ማድረግ ዋና ስራ ቢሆንም ከዚህ ጎን ለጎን ግን የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማዳበር ስራ መሰራት አለበት፤ አመዛኙ ስራም መከናወን የሚገባው በዚህ ደረጃ ነው፡፡
የትግራይ ክልል ከዚህ አንጻር ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው፤ ክልሉ በምርጥ ተሞክሮው የአለም ጤና ድርጅት ጭምር የመሰከረለት መሆኑን ገልጸዋል፤ ክልሉ ለእዚህ ውጤት የበቃው የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋቱና በስራው ላይም ተሳትፎ እንዲያደርግ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱ መሆኑን አስረድተዋል።
በዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መሰረት በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በዓመት ሰባት ሚሊዮን ህዝብ ከማጨስ ጋር በተያያዘ ህይወቱን ያጣል።

በአዲስ አበባ 13 የግል ትምህርት ቤቶች ያልተገባ ክፍያ በመቀበላቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው


በአዲስ አበባ የሚገኙ 13 የግል ትምህርት ቤቶች ያልተገባ ክፍያን ከተማሪ ወላጆችን ከማስከፈል ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው የትምህርት ተቋማት ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ያሉ መሆናቸውን በአዲስ አበባ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት እና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ አሳውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ብሩክነሽ አርጋው እንዳሉት ተቋማቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በሚል ተጨማሪ ክፍያ ከወላጆች በመውሰዳቸው ነው።
በተደረገ ክትትል እና ፍተሻም ተቋማቱ ለመማሪያ ቁሳቁስ በሚል ከወላጆች የተቀበሉትን ገንዘብ እና ተጨማሪ የመማሪያ ቁሳቁሶችም ለወላጆች እንዲመለሱ መደረጉን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
ሌሎች ተቋማት ላይም ይህን መሰል ድርጊት እንዳይፈፅሙ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።
እነዚህ ተቋማትም በድጋሚ ይህን ተግባር የሚደግሙት ከሆነ እርምጃ የሚወሰድባቸው እንደሚሆንም ኤጀንሲው ገልጿል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ተቋማት የውጭ ፍተሻ ስራ ትናንት በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፥ የፍተሻ ስራው ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ባሉ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ነው የሚሰጠው።
ኤጀንሲው እስካሁን ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ተያይዞ ችግር አለባቸው ለተባሉ 99 የመንግስትና 5 የግል የትምህርት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
እነዚህ ተቋማት ከነበሩበት ደረጃ የማይሻሻሉና ያሉባቸውን ችግሮች የማይቀርፉ ከሆነም እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።

 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዙፋን ካሳሁን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2010

ሐሙስ 15 ፌብሩዋሪ 2018

https://youtu.be/CCcXpWRSx1o

ሰበር ዜና... ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

አዲስ አበባ የካቲት 8/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢህአዴግ ሊቀመነበርነትና ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በአገሪቱ የተፈጠረው አሳሳቢ ሁኔታ እልባት እንዲያገኝ የመፍትሄው አካል ለመሆን ነው ብለዋል።
ከስልጣን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ ድርጅታቸው ደኢህዴን የተቀበለው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ታውቋል።


ረቡዕ 14 ፌብሩዋሪ 2018

ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች

 ታዋቂ ፈላስፋዎችን፣ ሳይንቲስቶችን እና ለዓለም ስልጣኔ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ ሰዎችን እናስተዋውቃችኋለን። እስቲ ልጆች የዓለም ስልጣኔ እዚህ እንዲደርስ ትልቅ ድርሻ አላቸው የምትሏቸውና ከዚህ ቀደም እናንተ ከምታው ቋቸው ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን አስታውሱ። ሊደነቁ ይገባል አይደል? መልካም ልጆች ሁሉም ሰው በእኩል ደረጃ ለዓለም መሰልጠን እና 
አቅማችን ከተጠቀምንበት አዲስ ነገር ለመሥራት እና ለመፍጠር እኛ የሰው ልጆች ከሌላው የዓለም ፍጡር በተለየ መንገድ ልዩ ስጦታ ታድለናል። ታዲያ እናንተ ምን አሰባችሁ? አዲስ እና ጠቃሚ ነገር ለአገራችሁ ብሎም ለዓለም ህዝብ ለመሥራት ተዘጋጃችሁ? መልካም ጥሩ ምሳሌ እንዲሆናችሁ ለዛሬ የኬሚስትሪ ሊቅ የሆነውን እና ለዓለም ስልጣኔ የራሱን ድርሻ ስለተወጣው ሊውስ ፓስተር እንነግራችኋለን።
1. እ.አ.አ በ18 22 ተወልዶ እስከ 1895 የኖረው የኬሚስትሪ ምሁር እና ማይክሮ ባይሎጂስቱ ሊውስ ፓስተር የምግብ መመረዝን የሚፈውስ «አንቲ ዶትን» ጨምሮ በርካታ በሽታዎችን የሚያድኑ መድሀኒቶችን ለዓለም አበርክቷል።
2. ይህ እውቅ ሳይንቲስት ወተትን ፓስቾራይዝድ እንዲሆን እና ለቲቢ በሽታ የሚያጋልጠውን «ቱውበ ርክሎስስ» ለማስወገድ እንዲጠቅም የማድረግ ዘዴን አስተዋውቋል። ይህ ሰው ጀርም ከማንኛውም ቁስ ጋር በሚደረግ ንክኪ እንዴት ሊፈጠር እንደ ሚችልም ባደረገው ምርምር መሰረት ድንገት የማይፈጠር እና በሂደት በንክኪ የሚመጣ መሆኑን አረጋግጧል።
3. በምሥራቅ ፍራንስ በ«ዶል» ከተማ የተወለደው ሊውስ ፓስተር በዋናነት ስለ ጀርም አፈጣጠር ጥናት አድርጓል። ይህ ሰው በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ በመባል ህመም ላይ ሰፊ ጥናት በማድረግ መድሀኒት መፍጠር ችሏል።
4. ሊውስ በህይወቱ ጠንካራ ሠራተኛ ለመሆን ይተጋ ነበር። አብዛኛውን ጊዜውንም በምርምር በላቦራቶሪው ውስጥ ያሳልፍ ነበር። በዚህም የበርካታ በሽታዎችን መድሃኒት ለማግኘት ችሏል። በተለያየ ጊዜ ትምህርቱን ቢከታተልም በ1847 ግን በምርምር ሥራ የዶክትሬት ዲግሪውን ማግኘት ችሏል። አጋሮቹም ሁል ጊዜ ስለሥራ ጥሩነት ያወራቸው ነበር።
ልጆች ዛሬ ስለ ሊውስ ፓስተር በጥቂቱ አውርተናችኋል። ከዚህ ሰው የሥራ ክቡርነትን፣ የሰው ልጆች ላይ ችግር ሆነው የቆዩ በሽታዎችን የሚያድን መዳህኒት ለማግኘት የተደረገ ጥረት እና ስኬትን እንደተማራችሁበት አንጠራጠርም። ስለዚህ በህክምናው ዘርፍ ላይ ለመሰማራት እና ልክ እንደ ሊውስ ፓስተር አስተዋፅኦ ለማድረግ የምትፈልጉ ጥሩ ትምህርት እንደም ትወስዱበት አንጠራጠርም። 
 


ምንጭ፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ  ማህበራዊ አምድ

ዓርብ 2 ፌብሩዋሪ 2018

61 የሀገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዳቸው ተሰረዘ



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 77ኛ ዓመት ቁጥር 145 ባወጣው ማስታወቂያ የሀገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በቢሮው በስራና ሠራተኛ ማገናኘት አግልግሎት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አውጥተው ይሰሩ የነበሩ ቢሆንም የዕድሳት ጊዜያቸውን በወቅቱ ባለመፈፀማቸው ምክንያት በአዋጅ ቅጥር 632/2001 አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 1/መ/መሠረት ከጥር 01 ቀን  2010 ዓ.ም ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃዳቸውን ሰርዟል፡፡