---------*
እቴ
ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን ረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
.
.
... እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።
.
.
እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሽውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን
.
---//------
.
.
2. ክልክል ነው!!!
------------*
ማጨስ ክልክል ነው
ማፏጨት ክልክል ነው
መሽናት ክልክል ነው
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው"፤
የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡
-----//-------
.
.
3. አንሺና ጣይ
-------------*
ደመወዙን ቢጥል
አንስተው ጠጡበት
ባርኔጣውን ቢጥል
ወስደው ደመቁበት
ከዘራውን ቢጥል
ተመረኮዙበት
በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ
በጣለው ሲያጌጡ
በጣለው ሲያተርፉ
ራሱን ሲጥል ግን
አይተውት አለፉ
-----//----
.
.
4. ኢትዮጵያዊ ነኝ!
-------------------*
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደ አክሱም ግንብ እንደቦሃ አለት
የመከራ አለት ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
ከዋርካ ባጥር ከንቧይ ተልቄ
ከፀሃይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ከምድረ በዳ ውሃ አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በፍኝ ጠልቄ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
ልክ እንደ ቻይናው የትም ሳልረባ
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ
በመጠን ኖሬ አፈር ምገባ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
ግትር ጠላቴን ባጭር አንካሴ
እራስ ምታቴን በዳማከሴ ነቅዬ ምጥል
አገር በነገር የማብጠለጥል
ነገር በነገር የማብጠረጥር
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
እንደ ማህረብ ቤቴን በኪሴ
እንደ ንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤው የምዞር ከቦታ ቦታ
በሰበብ ኬላ የማልረታ
ኢ..ት..ዮ..ጵ..ያ..ዊ.... ነኝ!
----//-------
© በዕውቀቱ ስዩም
ዓርብ 27 ሜይ 2016
1.ይስጥሽ
ረቡዕ 11 ሜይ 2016
ዛሬ 03/09/08 በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ
ዛሬ 03/09/08 በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በቀበሌ 16 በሚገኝው በልማድ ፖሊስ ካምፕ በሚባለው ቦታ ለከተማችን ሁለተኛው ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ሙሉ በሙሉ ወጪው በዳሽን ቢራ አ.ማ የሚገነባው ሜዳ የመሰረት ድንጋይ በከንቲባችን በአቶ ተቀባ በዳሽን ቢራ አ.ማ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ መክብብ እንዲሁም የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች እንግሊዛዊው ማርቲን ሬይሞንድ ኬውን በተገኙበት የተቀመጠ ሲሆን በጎንደር መስቀል አደባባይ በተካሄደው ፐሮገራም ለአገሪቱ እግር ኳስ እድገት መሠረት የሆኑትን የታዳጊ የእግር ኳስ ተጫዋቾችንና አሰልጣኞችን ማበረታታት የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ ሲሆን ማሪቲን ኬውን በቆይታው በአዲስ አበባና በጎንደር የልማት ስራዎችን ይጎበኛል።ከዳሽን ቢራና ከፋሲል ከነማ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተዋወቃል።
ከፕሮጀክት እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ጨዋታ ያደረገ ሲሆን ፣ ኳሶችንና ፒፕስ በስጦታ የበረከተ ሲሆን ከሰአት ደግሞ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ለመጎብኝት ሂድዋል ኬውን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከሚሰለጥኑ ታዳጊ ወጣቶች ጋርም የእግር ኳስ ጨዋታ ያደርጋል።
እንዲሁም ከአሰልጣኞችና ከሌሎች የስፖርት ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ ያካሂዳል።
የአርባ ዘጠኝ ዓመቱ ማርቲን ኬውን በአርሰናል፣ በሬዲንግ፣ በኤቨርተን እና በአስቶን ቪላ ክለቦች ተጫውቷል።ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚጣው የእንግሊዙ የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ከዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር በእግር ኳስ ላይ በጋራ ለመስራት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ነው። እንዲሁም ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ቤት ለተቃጠለባችወ ለችግረኞች ዳሽን ቢራ አ.ማ የ 600000 ብር ድጋፍ ለከንቲባው አበርክተዋል ፡፡ አንተነህ መሀሪ የዳሽን ቢራ ስፖርት ክለብ ህዝብ ግንኙነት
«ልብ ብለው ያንብቡ»
Enku TV
የዚህን ቻይናዊ ታሪክ ስሰማ ሁሌም እንደ አዲስ እደነቃለሁ።
ጃክ ማ (Jack Ma) ይባላል።
☞ለሶስት ጊዜ ያክል ኮሌጅ ውስጥ ውጤት አልመጣለትም
☞30 ግዜ ለስራ አመልክቶ አልተሳካልለትም
☞KFC ቻይና ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍት ከእሱ ጋር 24 ሰዎች ለስራ ተወዳድረው እሱ ብቻ እድሉን አጣ
☞ለፖሊስነት አመልክቶ እሱ ብቻ ተቀባይነት አጣ
☞አሜሪካ ለሚገኘው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ለመቀጠል ጠይቆ he was rejected በህይወቱ ውስጥ በጣም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዶዋል ግን ተስፋ ቆርጦ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም።
በ1994 ስለ ኢንተርኔት ሰማ። በ1995 ከትውልድ አገሩ ቻይና ወደ አሜሪካ ባጋጣሚ ያቀናል በዚህም ጊዜ በጓደኛው እርዳታ ስለ ኢንተርኔ ምንነት ማወቅ ቻለ።
ኢንተርኔትን እንዳወቀ መጀመርያ የፈለገው ቃል "beer" የሚል ነበር። በዚህም ስለ ቢራ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ አገሮች ያገኝ ቢሆንም ከአገሩ ቻይና ግን ምንም አይነት መረጃ ማግኝት አልቻለም።
በዚህም ተበሳጨና ስለ ቻይና አጠቃላይ መረጃ መፈለግ ተያያዘ አሁንም ውጤቱ 0 ነበር። በዚህም ቁጭት ከጓደኛው ጋር ሆኖ ሰለ ቻይና መረጃ የሚሰጥ ድህረ ገጽ ፈጠሩ፡፡
ድህረ ገጽ በተከፈተ በአምስት ሰዓት ውስጥ ከተለያዩ ቻይናዊያን የአብረን እንስራና እንተዋወቅ ጥያቄዎች ቀረቡለት።
በዚህም ኢንተርኔት አዋጭ ስራ እንደ ሆነ ተገነዘበ፡፡ እንደዚህ እያለ የአለማችንን ግዙፍ የe-commerce ተቋም የሆነውን ALIBABA GROUP ለማቋቋም በቃ፡፡
አሁን የ 23.6 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ተቀማጭ አለው። ማክ የአለማችን ቱጃር ከሚባሉት ባለሃብቶች ተርታ ስሙን አስመዝግቧል።
ወዳጄ በማንኛውም ሁኔታ በምንም ምክንያት ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ሌላ ብሩህ እና መልካም ቀን ነው። ወዳጄ አንድ ነገር ላይ ችክ አትበል አማራጮችን ተጠቀም አመራጮችን ተመልከት አማራጮችን ፍጠር፡፡ አንድ ነገር ፈልገኸው ወዳንተ ብቻ እስኪመጣ አትጠብቅ አንተም በምትችለው አቅም ተጠጋው፡፡ ምክር አይደለም ወዳጄ የምታውቀውን ነገር ላስታውስህ ብዬ ነው።
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
ሰኞ 9 ሜይ 2016
ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ በዳንኤል ክብረት
ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡
እነ እገሌ ካሉ፣ እነ እገሌ ቦታውን ከያዙ፣ እነ እገሌ እዚያ ላይ ከወጡ፣ በቃ አይሳካልኝም አትበል፡፡ ሌስተርን ያየ እንዲህ አይልም፡፡ ለወትሮው የእንግሊዝ እግር ኳስ ማንቸስተር ዮናይትድና ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሴናልና ቼልሲ በእግራቸው ርግጥ፣ በእጃቸው ጭብጥ አድርገው የሚዘውሩት ይመስል ነበር፡፡ መቼም ዋንጫውን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ እንጂ ሌላው ይቀምሰዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ‹ሙሴ በሩቁ ከነዓንን አያት እንጂ አልወረሳትም› እንደሚባለው ሌሎቹ ቡድኖች ዋንጫውን በሩቁ ከማየት አልፈው ይወርሱታል ብሎ ማን ያስብ ነበር፡፡
ወዳጄ በዚህ ዓለም ላይ የማይነጠቅ የተጨበጠ፣ የማይንሸራተት የተረገጠ የለም፡፡ nothing for granted ይሉ የለም ስታድየሙን ሞልተው የሚጨፍሩት እንግሊዞች፡፡ የጨበጥክበት እጅህ፣ የረገጥክበት እግርህ አንድ ቀን ይዝላል፡፡ የትናንት አይበገሬነትህ፣ የትናንት ጀግንነትህ፣ የትናንት ክብርህ፣ የትናንት አሸናፊነትህ፣ የትናንት ተፈሪነትህ በዛሬ ጥረት ካልታገዘ ታሪክና ቅርስ እንጂ ድልና ውጤት አይኖርህም፡፡ አታያቸውም እንዴ እነ ማንቸስተር ዩናይትድና እነ ማንቸስተር ሲቲ ከአራቱ ውስጥ ለመግባት መከራቸው ሲያዩ? አታያቸውም እንዴ እነ አርሴናል ከቀበሮ አምልጦ ዛፍ ላይ እንደወጣ ዶሮ ካሁን አሁን ከአራቱ ወረድን እያሉ ሲጨነቁ? አላየኸውም እንዴ ስንት ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የኖረው አስቶንቪላ ተሰናብቶ ከሊጉ ሲወርድ፡፡
ዓለም እንደዚህ ናት፡፡ ድል በታሪክ ቢሆን ኖሮ ከሊቨርፑል በላይ ማን ዋንጫ ይወስድ ነበር፡፡ ምን እዚያ ወሰደህ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ዋንጫ የጠነሰስን፣ የአፍሪካን እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንስ የመሠረትን አልነበርንምን? ከብዙዎቹ ቀድመን ኳስ ተጫውተን፣ ከብዙዎቹ ቀድመን ዋንጫ አልበላንምን? ከብዙዎቹስ በፊት የአፍሪካን የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አልመራንምን? ዛሬ ግን የት ነን? ትዝታ ሆነናል፡፡ ዋንጫ እንደ መንግሥተ ሰማያት፣ ድልም እንደ ሰማይ ርቆናል፡፡
ሊቃውንቱ ‹ድል ማለት ጥረትና ዕድል የሚገናኙባት አጋጣሚ ናት› ይላሉ፡፡ አንተ ትታገላለህ፣ ትጥራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትወጣለህ፣ ትወርዳለህ፤ እንዲህ ባለማቋረጥ ስትታገል አንድ ቀን የአንተ የጥረትህ መንገድ ከዕድል መንገድ ጋር ይገናኝና ታቋርጠዋለህ፡፡ ያኔ አይወድቅም የተባለው ወድቆ፣ አይሸነፍም የተባለው ተሸንፎ፣ አይነቀነቅም የተባለው ተነቅንቆ፣ አይፈርስም የተባለው ፈርሶ፣ አይነካም የተባለው ተነክቶ ቦታውን ሲለቅ ታየዋለህ፡፡
አንተ ካልጣርክና ካልታገልክ፣ ካልሠራህና ካልሞከርክ ግን በዕድል ብቻ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ዛሬ አላሸነፍክም? ተስፋ አትቁረጥ ቢያንስ የማሸነፍ ሞራልና የማሸነፍ ተስፋ አለህና፡፡ የሚሸነፍ ትግል የለም፡፡ የሚሸነፍ ሰው እንጂ፡፡ ትግል ትግልን ይወልዳል፣ ጥረት ጥረትን ይተካል፣ ሙከራ ሙከራን ያመጣል፡፡ ዛሬ አንድ አካፋ አፈር ከተራራው ላይ ስታነሣ ተራራውን አልናድከው ይሆናል፡፡ በርግጠኝነት ግን የተራራውን መልክ ቀይረህዋል፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች፣ ወይም አንተ ራስህ እንኳን የተራራው መልክ መቀየሩን ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ተራራው ራሱ ግን ያውቀዋል፡፡ የመሬት መሸርሸር የሚባለው ግማሽ ተራራ ተሸርሽሮ አይደለምኮ፡፡ ውኃ እያሳሳቀ አፈሩን በየጊዜው ሲወስደው ነው፡፡
ምናልባትም ምንም አታመጣም ብለው ሰዎች ይነግሩህ ይሆናል፡፡ ሌስተርን ተመልከቱ በላቸው፡፡ ሌስተር የት ነበረ፡፡ አምና ቼልሲ ዋንጫውን ሲወስድ፣ ማንቸስተር ሲቲ ሁለተኛ ሆኖ ሲጨርስ አርሴናልና ማንቸስተር ዩናይትድ ሦስትና አራተኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ፣ ሌስተር የት ነበር? እስከ ሰባት፣ እስከ ዐሥር ደረጃ ብትፈልገው ታገኘዋለህን? ፈጽሞ፡፡ ሌስተር ከወራጅ ቀጠናው በአራት ደረጃ ርቆ፣ ከወራጁ ከሁልሲቲ በ7 ነጥብ ብቻ በልጦ 14ኛ ደረጃ ላይ ነበረልህ፡፡
ዘመን መሰላል ነው፡፡ የወጣው ሲወርድ፣ የወረደው ሲወጣ ይገናኙበታል፡፡ በአንድ ዓመት ልዩነት የቸልሲን ቦታ ሌስተር፣ የሌስተርንም ቦታ ቼልሲ ይዞ አየነው፡፡ እንዳያርግ ስንፈራው የነበረው ቼልሲ እንዳይወርድ ተሳቀቅንለት፡፡ ‹የናቁት ይውርሳል› እንደተባለው አራቱን ኃያላን ገፍቶ ሌስተር መጣና እንደ ሽሮ ቅቤ በአናት ተቀመጠ፡፡ ‹ይሞታል ያሉት ተርፎ፣ ይቀብራል ያሉት ሞተ› ሲባል አልሰማህም?
እናም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ግፋ፣ ጣር፣ ታገል፣ ሥራ፣ ሞክር፣ ድፈር፤ ድል ይጠራቀማል፡፡ አንድ ቀን ከላይ ያየሃቸው ኃያላን እንደ ቼልሲ ደክመው፣ እንደ አርሴናል አርጅተው፣ እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀልብ ርቋቸው፣ እንደ ሲቲ ነገር ዓለሙ ዞሮባቸው ታገኛቸዋለህ፡፡ ያኔ እንደሌስተር ገፋ ገፋ አድርገህ ከላይ ቁጢጥ ነው፡፡ ሰውን መናቅ እንጂ በሰው መናቅ አይጎዳም፡፡ ሰውን መናቅ ትዕቢትን ወልዶ ስንፍናን ያመጣል፡፡ በሰው መናቅ ግን እልህን ወልዶ ትግልን ይፈጥራል፡፡ እናም አሸናፊነትህ የሚወሰነው ሰዎች ባንተ ላይ ባላቸው አመለካከት አይደለም፤ አንተ በሌሎች ላይ ባለህ አመለካከት እንጂ፡፡ እንዴት ያዩኛል? ብለህ አትጨነቅ፡፡ እንዴት አያቸዋለሁ? ብለህ ግን አስብ፡፡ እያሸነፍክ ስትመጣ የማያዩህ ሁሉ ያኔ ያዩሃል፣ የጠሉህ ያኔ ይወዱሃል፣ የናቁህ ያኔ ያደንቁሃል፡፡ የበለጠ ወደ ማይክራፎኑ በተጠጋህ ቁጥር የበለጠ ድምጽህ ይሰማል፡፡
እንዲያውም ሲንቁህ መልካም ነው፡፡ ጫና አይበዛብህም፤ ጠላት አይበዛብህም፤ ተገዳዳሪ አይበዛብህም፤ ጉልበትህን ለሥራህና ለዓላማህ ብቻ እንድታውለው ጊዜ ታገኛለህ፡፡ ሰዎች ዓይናቸውን ቼልሲ ላይ ያርጉልህ፣ ማንቸስተር ላይ ይጣሉልህ፣ ሲቲ ላይ ያኑሩልህ፣ አርሴናል ላይ ያትኩሩልህ፡፡ አንተ ዝም ብለህ ሥራና እንደ ሌስተር እየገፋህ ና፡፡ መንደርህ ትንሽ ናት? ስምህን የሚያውቀው የለም? ገንዘብህ ጥቂት ነው? የተሰጠህ ግምት አነስተኛ ነው? ባንተ የሚተማመኑ የሉም ወይም ጥቂት ናቸው? እነዚህ ሁሉ ካልለወጡህ ልትለውጣቸው ትችላለህ፡፡
እንደ ንሥር ታድሰህ፣ እንደ እባብ አፈር ልሰህ፣ እንደ ከራድዮን ራስህን ለውጠህ እስካልመጣህ ድረስ እንደ ቼልሲ ትናንት ዋንጫ በልተህ ዛሬ መውረድህ የማይቀር ነው፡፡ ወደላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው፡፡ ጊዜ ይለወጣል፣ ሐሳብ ይለወጣል፣ ወዳጅ ይለወጣል፣ አሠራር ይለወጣል፣ እሴቶች ይለወጣሉ፡፡ አንተም ትናንት የሠራኸውን ብቻ እየዘፈንክ፣ የትናንቱንም ታሪክ ብቻ እየተረክህ፣ ‹ትናንት እንዲህ ያደረግኩት እኔ ነኝ› ብለህ እየፎከርክ መኖር አደገኛው አኗኗር ነው፡፡ ‹ሆ› ብለው ያወጡህ ‹ውይ› ብለው እንዳያወርዱህ፣ ‹ጀግና› ብለው የሰቀሉህ፣ ‹ፈሪ› ብለው እንዳይጥሉህ፤ ‹ጉሮ ወሸባዬ› የዘፈኑልህ፣ ‹ዋይ ዋይ የት ትሄዳለህ› እንዳይሉህ፣ ‹ያለ አንተ› ያሉህ ‹ካንተ በቀር› እንዳይሉህ፡፡ የኮሩብህ እንዳያፍሩብህ፣ ‹እዩኝ እዩኝ› ብለህ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› እንዳትል ከፈለግክ መንገዱ አንድ ብቻ ነው፡፡ የትናንቱን ለታሪክ ተወውና ለዛሬው የሚያስፈልግህንና የሚገባህን ሥራ ሥራ፡፡ ከታሪክ ተማር እንጂ ታሪክ ላይ አትተኛ፡፡
አታይም እዚህ ሀገር እንኳን የሊቨርፑል ዘመን አልፏል፡፡ ዛሬ በሃምሳዎቹና በስድሳዎቹ ውስጥ ያሉ የኳስ አፍቃሪዎች በዘመናቸው የሊቨርፑል ደጋፊዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የእነርሱ ልጆች እንኳን ሊቨርፑልን አይደግፉም፡፡ ያማ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መጥቶ፡፡ ዘመን ተቀይሮ፤ ደጋፊም ተደጋፊም ተቀይሮ፡፡ አዲስ ጀግና መጥቶ፣ አዲስ ተከታይ አፍርቶ፡፡ ያም ዘመን አለፈ፡፡ የነማንቸስተርና የነአርሴናልም ዘመን መጣ፡፡ እርሱም ሊያልፍ ነው መሰል፣ ደግሞ የነ ሌስተርና የነ ቶተንሐም ዘመን መጣ፡፡
‹በቃ ጨርሻለሁ› ወይም ‹በቃ ተጨርሻለሁ› አትበል፡፡ ‹አለቀ›ም ‹አለቀልኝ›ም አትበል፡፡ ካንተ በፊት ሌሎች ነበሩ፡፡ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፡፡ ‹ታግለን ጨርሰናል› ያሉ እንደ ቼልሲ ቦታ እየለቀቁ፣ ‹ገና ይቀረናል› የሚሉ ታጋዮች እንደ ሌስተር ቦታውን እየተረከቡ ይሄዳሉ፡፡ ሕይወት ሌስተርና ቼልሲ ናት፡፡
እሑድ 8 ሜይ 2016
ሸገር ደርቢ
በኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ የምንግዜ የአዲስ አበባ ከተማ ተቀናቃኞቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በዛሬው ዕለት በአደስ አበባ እስታዲየም በ10:00 ሰዓት ጨዋታው ይካሄዳል ። የስታዲየሙ ድባብ እንዲሚከተለው ነው።
ዓርብ 6 ሜይ 2016
የፊፋ የሚያዚያ ወር የአገራት ደረጃ ይፋ ተደርጓል::
በዚህም መሰረት አርጀንቲና፣ቤልጄም እና ቺሊ ከ 1~3 ደረጃውን ሲይዙ
4- ኮሎምቢያ
5-ጀርመን
6-ስፔን
7-ብራዚል
8- ፓርቹጋል
9-ኡራጋይ
10-እንግሊዝ እስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
ከአፍሪካ ደግሞ
33-አልጄሪያ
34-አይቮሪኮስት
38-ጋና ሲሆኑ
ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስናቀና ደግሞ
72-ዩጋንዳ
87-ሩዋንዳ
116-ኬንያ
122-ብሩንዲ
123-ኢትዮጵያ ተቀምጠዋል::
ኢትዮጵያ ከአለም 123ኛ ከ አፍሪካ 38ኛ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 5ኛ ላይ ተቀምጣለች
ቅናት
By Bersufkad Zena@DireTube
---------------------------------------
ቅናት የምንፈልገውን ሰው አጣዋለሁ ብሎ ከመስጋት
የሚመነጭ ስሜት ነው፡፡ቅናት ነገሮችን ከራስ አንጻር ብቻ
በማየት የሚከሰት ነገርም ነው፡፡ ቅናት ደረጃዎች ያሉት
ሲሆን በአለባበስና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ አስተያየት
ከመሥጠት ጀመሮ የአጋራችንን ሁለንተናዊ ነገር
ለመቆጣጠር እስከመሄድ የሚደርስ ነው፡፡ የጥናት
ውጤቶች እንደሚያሳዩት ቅናት ሀይለ ስሜታዊ፣አካላዊ
፣ስነባህሪያዊ እነዲሁም ማህበራዊ አሉታዊ ተጽእኖዎችን
በሰዎች ላይ ያሳድራል፡፡
--
የቅናት ምክንያቶች
ሰዎችን ለቅናት የሚዳርጉ ብዙ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን
እነዚህ ምክንያቶች ካስተዳደግና ከምንኖርበት
ማህበረሰብ ባህል ጋር ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ
ግንኙነት አላቸው፡፡ከተለያዩ የጥናት ውጤቶች
ያገኘኋቸውን እና በእኛ ሐገር ነባራዊ ሁኔታ ያስኬዳሉ
ያልኳቸውን የቅናት ምክንያቶች ከዚህ እንደሚከተለው
አቀርብላችኋለው::
---
1.አጋርን የማጣት ስጋት እና ከመጠን ያለፈ ፍራቻ
የመጣንበት መንገድ ወይንም ከሰዎች ልምድ በመነሳት
እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡
እንዲሁም ለራሳችን የምንሰጠው ቦታ የወረደ ከሆነ ሌላ
ሰው ትልቅ ቦታ ይሰጠናል ብለን ለማሰብ እንቸገራለን
በዚህም ቅናት ውስጥ የመግባት እድል ይኖረናል፡፡የጥናት
ውጤቶች እንደሚያሳዩት የትዳር አጋራችንን ልናጣ
እንደምንችል በመጠኑ መፍራት ፍቅርን የማጠናከር አቅም
አለው ፡፡ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ፍራቻ ለቅናት ይዳርጋል
እንዲሁም የምንወደውን ሰው ሊያሳጣንም ይችላል፡፡
---
2.ሰዎችን እንደቁስ መቁጠር
ሰዎች አስበውና ወደውን እንደመረጡን የማይሰማን ከሆነ
እንዲሁም በየትኛውም ጊዜ የሆነ ሰው ተነስቶ ሊቀማን
ይችላል ብለን የምናስብ ከሆነ የመቅናት እድል ይኖረናል፡:
---
3.ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ጥገኛ መሆን
ጥገኝነት በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል የግዴታ ቁሳዊ
ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡አነድ ሰውን ያጣን ጊዜ የኛ መኖር
እንደሚቆም የምናስብ ከሆነ ያንን ሰው ላለማጣት
እንጥራለን ሁሉም ሰው እሱን የሚቀማን ይመስለናል
በዚህም በቀላሉ በቅናት እንጠቃለን፡፡
----
4.ከአስተዳደጋችን እና ከምንኖርበት ማህበረሰብ ባህል
ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምክንያቶች
እነዚህ ምክንያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በወላጅ እና
በአሳዳጊ መሀከል ጥሩ ያልሆነ ግኝኙነት ከነበር፣
ከህጻንነታችን ጀምሮ ምንም ነገር የመስራት ችሎታ
እየተነገረን ካዳግን…..ወዘተ
----
ቅናትን ለመቀነስ ምን ማድረግ እንችላለን?
ቅናት ሰዎችን ለበሽታ ፣ለጭንቀት እንዲሁም ለተለያዩ
ማህበራዊ ቀውስ የሚዳርግ ነገር ነው፡፡ቅናትን ሙሉ
ለሙሉ ማጥፋት ባይቻልም ቢያንስ ለመቀነስ የሚረዱ
ዘዴዎች አሉ፡፡ ቅናት ለበትን ሰው ከዚህ ስሜት እነዲላቀቅ
ወይም ቅናትን ለመቀነስ የሚረዱ እና ከተለያዩ የጥናት
ውጤቶች ላይ ያገኘኋቸውን ዘዴዎች ከዚህ በታች
እናያቸዋለን እቀርባለሁ
--
1.ቅናት ችግር መሆኑን ማመን
አንዳንድ ሰዎች ቅናትን ጥሩ እንደሆነና ሰውን ከመውደድ
አንጻር የሚደረጉት እንደሆነ ያስባሉ በዚህም ለተለያዩ
ችግሮች ይዳረጋሉ፡፡ ከዚህ ይልቅ ቅናት ትልቅ ችግር
መሆኑን በመረዳት መፍትሄ መፈለግ ጠቃሚ ነው፡፡
--
2.እራሳችንን እና የፍቅር ሂይወታችንን መገምገም
በጣም የተረጋጋና ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ውስጥ
እየኖርን የቅናት ስሜት የሚሰማን ከሆነ እራሳችንን
መገምገም እና ከባለሞያ ጋር መመካከር ያስፈልጋል፡፡
--
3.በሰከነ መንገድ ለመነጋገር መሞከር
ያልተፈጠረ ነገርን ተፈጥሯል ብለን እራሳችንን ከመጉዳት
በፊት በተረጋጋ ሁኔታ አስበንበት ግልጽ የሆነ ውይይት
የማድረግ ባህልን ብናዳብረ ቢያንስ በቅናት ምክንያት
ሊደርስብን የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንችላለን፡፡
---
4.እራሳችን ላይ መስራት
ቅናት በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል ለምሳሌ ለራሳችን
ዝቅተኛ ቦታ መስጠት አንዱ የቅናት ምክንያት ነው፡፡
እንደዚህ እይነት ምክንያቶችን በመለየት እና እራሳችን ላይ
በመስራት በራስ መተማመናችንን በመጨመር ፣ ለራሳችን
ከፍተኛ ግምት በመስጠት ………ወዘተ ቅናትን መቀነስ
እንችላለን፡፡
---
5.ለሚቀናበት ሰው
አጋራችን እነደሚቀናብን ካወቅን አጋራችንን መርዳት
ይጠበቅብናል፡፡ ለአጋራችን ሁሌም ከጎናቸው እንደሆንን
እና ፍቅራችንን የምንገልጽ ከሆነ የአጋራችንን ቅናት
የመቀነስ አቅም ይኖረናል፡፡የጥናት ውጤቶች
እንደሚያሳዩት እንደዚህ የሚያደረጉ ሰዎች የተረጋጋ
የፍቅር ህይወት ይኖራቸዋል፡፡
---
6.ከባለሞያ ጋር መነጋገር
ቅናት ደረጃ አለው በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረስን
ከመሰለን እና በራሳችን መንገድ ለመተው ሞክርን ካቃተን
ከባለሙያ ጋር በመነጋገር እና እገዛ በማግኘት
ወደተፈላጊው መንገድ መምጣት እንችላለን፡፡
====
@በሱፍቃድ ዜና የሰዎችን እድገት በሚያጠና የስነበሃሪ
ትምህርት ዘርፍ(Developmental psychology)
ሁለተኛ ዲግሪ(ማስተርስ) ያለው ሲሆን ባሁኑበልጆች
አስተዳደግ እና በትምህርት ዙሪያ ወላጆችን የሚያማክር
ድርጅት ከፍቶ በግሉ እየሰራ ያለ ወጣት ባለሙያ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ zbesufekad@gmail.com
ሐሙስ 5 ሜይ 2016
አዲስ ቻርጀር የኃይል ምንጭ በገቢያ ላይ ሊውል ነው
#በከተማችን በቅርብ ቀን መመረት የጀመረው የስልክ ቻርጀር የኃይል ምንጭ የሆነው በቅርብ ቀን ወደ ገቢያ እንደሚቀር እየተነገረለት ሲሆን ፈላጊዎቹም በመመዝገብ ላይ ናቸው እርሶም መመዝገብ ከፈለጉ ሜዲን አደዚች ብለው በስልክ ቁጥር 0000 ሻማ ብለው ያናግሩን።
ፍቺ
By besufkad zena@ DireTube
---------------------------------------
በባለፈው ጽሁፎቼ ላይ ትዳር በሁለት ሰዎች(በወንድ እና
በሴት) በጎ ፈቃድ የሚመሰረት ህጋዊና ማህበራዊ
ስምምነት እንደሆነ ጠቅሼ ነበር፡፡ሰዎች በትዳር ውስጥ
የሚኖሩት ተስማምተውና ተረዳድተው መኖር ሲችሉ ነው፡፡
ነገር ግን መስማማት ካቃታቸውና በመሀከላቸው
የሚኖረው ልዩነት እየሰፋ የሚመጣ ከሆነ ወደፍቺ
ያመራሉ፡፡ በምዕራባውያኑ አለም የሚፋቱ ሰዎች ቁጥር
በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል፡፡
----
በሀገራችንም ቢሆን እንደ ምዕራባውያኑ ባይሆንም
የተፋቺዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛ፡፡
በዛው በምዕራቡ አለም የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት
ፍቺ ሰዎችን ጭንቀት ውስጥ ከሚከቱ የህይወት
አጋጣሚዎች ሁሉ በአንደኝነት የተቀመጠ ነገር ነው፡፡
ግላዊነት በሚንጸባረቅበት የምእራቡ አለም ፍቺ እንደዚህ
አስጨናቂ ነገር ከሆነ ማህበራዊነት በሚንጸባረቅበት በእኛ
ባህል ፍቺ ምን ያክል ከባድ ተጽእኖ እንዳለው መገመት
አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ የእኛ መፋታት በዙሪያችን ያሉ ሰዎች
ላይ ሁሉ ከፍተኛ ተጽእኖ ይፈጥራል ስለዚህ በጣም
ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
------------
የፍቺ ደረጃዎች
ፍቺ በአንድ ለሊት የሚከናወን ነገር አይደለም፡፡ ቀስ በቀስ
ከአንድ ደረጃ ወደሌላ ደረጃ እየተሸጋገረ በስተመጨረሻ
ሰዎችን የሚያለያይ እና ቤተሰብን የሚያፈርስ ጉዳይ ነው፡፡
በትዳራችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን የሚመስሉ
ችግሮች ወድያውኑ መፍትሄ እየሰጠናቸው ካልሄድን
ጥቃቅን ብለን ያሰብናቸው ችግሮች ጥርቅም ትልቅ
ችግር ከመሆን አልፎ ለፍቺ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
የፍቺን ደረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እናያቸዋለን፡፡
-----
1. ሀይለስሜታዊ ፍቺ
ይህ ደረጃ የፍቺ የመጀመሪያ ደረጃ ሲሆን እዚህ ደረጃ
ላይ የደረሱ ባለትዳሮቹ አንድ ቤት ውስጥ የሚኖረው
አካላቸው ብቻ ነው፣ምንም አይነት የስሜት ቁርኝት
የላቸውም:: ከውጪ የሚመለከተው ሰው ብቻ ትዳር
ውስጥ እንዳሉ ይታየዋል፡፡
--------
2. ፍቺን ማጽደቅ
ይህ ደረጃ ተጋቢዎቹ ፍርድ ቤት ሄደው ትዳራቸውን
የሚያፈርሱበት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከውጪ ሆኖ ሲመለከት
ለነበረ ሰውም የትዳር መፍረስ የሚታወጅበት ነው፡፡
--------
3. የንብረት ክፍፍል
ይህ ደረጃ ባለትዳሮቹ አብረው ሲኖሩ ያፈሩትን ሀብት
በሚደርሳቸው መሰረት የሚከፋፈሉበት ነው፡፡
----
4. የቤተሰብ ክፍፍል
ይህ ደረጃ ባለትዳሮቹ አብረው ሲኖሩ ልጅ ወልደው ከሆነ
የልጆቻቸውን እጣ ፋንታ የሚወስኑበት ነው፡፡
------------
5. ስነልቦናዊ ፍቺ
በዚህ ደረጃ ላይ ፍቺ ይጠናቀቅና የተፋቱት ባልና ሚስቶች
እንዴት ሆነው መኖር እንዳለባቸው የሚያስቡበት
እንዲሁም አዲሱ ህይወታቸውን ለመላመድ የሚጥሩበት
ነው፡፡
------
የፍቺ አሉታዊ ተጽእኖ
ፍቺ እጅግ በጣም ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ ያለው፣ ትልቅ
ማህበራዊ ተቋምን የሚያፈርስ እና በሀገር ላይ ከፍተኛ
ቀውስን የሚያስከትል ሂደት ነው፡፡ ከተለያዩ የጥናት
ውጤቶች ላይ ያገኘኋቸውን የፍቺ አሉታዊ ተጽዕኖዎች
ከዚህ እንደሚከተለው አቀርብላችኋላው፡፡
----
1. በልጆች ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ
የጥናት ውጤቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ወላጆቻቸው በፍቺ
የተለያዩባቸው ልጆች ላይ ከፍተኛ ድብርት፣ የትምህርት
ውጤት መቀነስ፣ ከሰዎች ጋር መስማማት አለመቻል ፣
በሚያድጉበት ወቅትም ለትዳር አሉታዊ አመለካከት
ማሳየት….ወዘተ ይታይባቸዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት
ፍቺ ከሴት ልጅ ይልቅ ወንድ ልጅ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ
ያሳርፋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሀ ሀገራት ውስጥ ፍቺ
ልጆችን የጎዳና ተዳዳሪነት ድረስ ሲያደርስ ይታያል፡፡
----
2. በተፋቺዎቹ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ
የጥናት ውጤቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች በፍቺ ሲለያዩ
በራስ መተማመናቸው ይቀንሳል፣ በድብርት
ይጠቃሉ፣ከፍተኛ ለሆነ ጭንቀት ይዳረጋሉ፣የጤና መቃወስ
ያጋጥማቸዋል፣ ህይወትን ከዜሮ ለመጀመር
ይገደዳሉ………ወዘተ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ
ማህበረሰባዊነት በሚንጸባረቅበት አገሮች ውስጥ ደግሞ
ፍቺ ከተፋቺዎቹ አልፎ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችንም ማለትም
ቤተሰቦቻቸውን ፣ ጓደኞቻቸውን….ወዘተ ለከፍተኛ የስነ
ልቦና ጫና የሚዳርግ ነገር ነው፡፡ እንዲሁም የተፋቱት
ሰዎች ቶሎ ለማገገም ሲቸገሩም ይታያሉ፡፡
----
ፍቺ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ነገር ከሆነ ሰዎች ለምን
ይፋታሉ?
የፍቺ ምክንያቶች እጅግ በጣም ብዙ ሲሆኑ ከሰው ሰው
የሚለያዩ ናቸው፡፡ሁሉንም ምክንያቶች መዘርዘር ባይቻልም
ያስተምራሉ ብዬ ያመንኩባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች
ከዚህ በታች አቀርብላችኋለሁ፡፡
---
1. ትዳርን ፍጹም ደስታ እንደሚገኝበት አድርጎ ማሰብ
ትዳር ለሰው ልጆች ደስታ የሚሰጥ ነገር ነው፡፡ነገር ግን
ከፍተኛ ሀላፊነትን መቀበልንም ይጠይቃል፡፡የጥናት
ውጤቶች እንዲያሳዩት ከሆነ ከትዳር ደስታን ብቻ
ለማግኘት አስበው የሚጋቡ ሰዎች የመፋታት እድል
አላቸው፡፡እናትና አባቶቻችን በትዳር ውስጥ 40 እና 50
አመት የኖሩት ደስተኛ ሆነው ብቻ አይደለም
የሚያጋጥማቸውን ፈተና በጽናት እያለፉም ጭምር ነው፡፡
----
2. አሁን እየተተካ ላለው ትውልድ አርአያ የሚሆኑ ሰዎችን
በደንብ አጉልቶ አለማውጣት
ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከረኩት በአገራችን በትዳራቸው
ጸንተው ብዙ ችግሮችን አልፈው 40 እና 50 አመት መኖር
የቻሉ ብዙ አርአያዎች አሉን ነገር ግን የእነዚህን ሰዎች
ተሞክሮ ለቀጣዩ ትውልድ ከማድረስ አንጻር ብዙ
ተሰርቶበታል ብዬ አላምንም፡፡ እነዚህ ሰዎች ይህን ሁሉ
አመት የኖሩት ደስተኛ ሆነው ብቻ ነው ወይስ በትዳራቸው
ለመቆየት ቁርጠኛ ስለሆኑም ጭምር? ልናቀው የሚገባ
ነው፡፡
አንዳንድ ሚዲያዎች እነዚህ ነገሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ
የነቢዮነሴን የ3 ወር ትዳር ወይም የምራባውያንን የፍቺ
መጠን ማውራት ይቀናቸዋል፡፡በዚህ ላይ አለም አንድ
መንደር እየሆነች ባለችበት በዚህ ዘመን መረጃዎች
በቀላሉ ይገኛሉ በዚህ እና መሰል ምክንያቶች ማንን
አርአያ ማድረግ እንዳለበት ግራ የተጋባ ትውልድ
ይፈጠራል፡፡ከትዳር አንፃር የተሳሳተ አርአያ ያለቸው ሰዎች
ደግሞ ፍቺን አንድ የህይወት አማራጭ አርገው የማየት
እድል ይኖራቸዋል፡፡
---
3. ሌሎች ምክንያቶች
ለትዳር መፍረስ ምክንያቶች የሚሆኑ ብዙ ምክንያቶች አሉ
ለምሳሌ ታማኝ አለመሆን፣ መነጋገር አለመቻል፣ንብረትን
በጋራ አለማስተዳደር፣የትዳር አጋርን ስሜት አለመረዳት፣
ቅናት ፣የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት…………ወዘተን
መጥቀስ ይቻላል፡፡
---
ከላይ እነደማሳያ የጠቀስኩላችሁ የተወሰኑትን ምክንያቶች
ነው፡፡ በእናንተ አስተያየት ሰዎችን ለፍቺ እየዳረገ ያለው
ምክንያት ምንድን ነው? በትዳር ውስጥ ጸንቶ ለመቆየት
ምን ያስፈልጋል? ልንነጋገርበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ
ነው፡፡
--
በመጨረሻም በእውቁ የቤተ ክርስትያን አባት ዮሀንስ
አፈወርቅ አባባል ጽሁፌን ላጠናቅ
“ባልና ሚስት ልክ እንደ ዐይን እና እጅ ናቸው ዐይን
ሲያለቅስ
እጅ እንባውን ይጠርግለታል እጅ ሲታመም ዐይን
ያለቅሳል”፡፡
----=======================-----------------
@በሱፍቃድ ዜና የሰዎችን እድገት በሚያጠና የስነበሃሪ
ትምህርት ዘርፍ(Developmental psychology)
ሁለተኛ ዲግሪ(ማስተርስ) ያለው ሲሆን ባሁኑበልጆች
አስተዳደግ እና በትምህርት ዙሪያ ወላጆችን የሚያማክር
ድርጅት ከፍቶ በግሉ እየሰራ ያለ ወጣት ባለሙያ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ zbesufekad@gmail.com
ረቡዕ 4 ሜይ 2016
ትኩስ እና ወቅታዊ እንዲሁም ያልተሰሙ የክለቦቹን ዜናዎች የያዝን ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች እጅግ ተወዳጅ እየሆነ የመጣውም የቁጥራዊ መረጃዎች ዝግጅታችንም ሁሌም እንደተለመደው ባማረ አቀራረብ ለዛሬ ተሰናድቷል፡፡ የዝውውር ዜናዎችም ለምሽቱ አዘጋጅተናል፡፡
# ከሀገር_ውስጥ :- “ ቴክኒክ ኮሜቴው የተሰናበተው በእልህ ነው ” ፣ ፕሪሚየርሊጉ በጎል ድርቅ ተመቷል ፣ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አይቲ ባለሙያዋ ተሰናብታለች
መሉ የዜናዎቹን ዝርዝር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ፡- goo.gl/ulbUeZ
Mark Ogden Independent: Ryan Giggs has
a decision to make if Jose Mourinho takes
Manchester United job, but Zinedine
Zidane can sway him. Inside Football:
Zidane spent seven years waiting for the
Real Madrid job, so could Giggs serve
under Mourinho before fulfilling his destiny
as United manager?
Gigg
ማክሰኞ 3 ሜይ 2016
ዛሬ በተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታወች፦
ድሬዳዋ ከነማ 1-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሲዳማ ቡና 0-0 ሀዲያ ሆሳእና
ሀዋሳ 0-0 ወላይታ ዲቻ
ዳሽን ቢራ 0-0 ኢትዮ ንግድ ባንክ
አርባምንጭ 0-0 መከላከያ
ኢትዮጵያ ቡና 1–0 ኤልፓ)
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ 100% ለሲቲው ጨዋታ ብቁ ነው ሲል የማድሪዱ አለቃ ዚነዲን ዚዳን ተናገረ።ዚዳን አክሎም የቤንዜማና ካሴሜሮ ለዚ ጨዋታ መድረስ አጠራጣሪ ነው ብሏል።
የዩናይትዱ አሰልጣኝ ሉኢቫንሀል በቀጣይ ከዩናይትድ ጋር ዋንጫወችን ማግኘት እፈልጋለሁ ማለታቸው ሰውየው ከዩናይትድ ቤት እንደማይለቁ ያሳያል ተባለ።
የሌስተር ሲቲው አሰልጣኝ በክለባችን ደስተኛ የሆኑ ተጫዋቾች ብቻ አብረውን በቀጣይ አመት ይቆያሉ አሉ።
የሌስተር ሲቲው ወጣት የ19 አመት ተከላካይ ቤንቼዊል ሊቨርፑልን ተቀላቀለ።ተጫዋቹ የጊብስ ምትክ አንዲሆን በአርሰናል ይፈለግ ነበር።
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት “የሚሸነፍ ትግል የለም፤ የሚሸነፍ ሰው እንጂ”
ይገርምሃል ወንድሜ፤ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎች‘ኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ፤ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡
እነ እገሌ ካሉ፣ እነ እገሌ ቦታውን ከያዙ፣ እነ እገሌ እዚያ ላይ ከወጡ፣ በቃ አይሳካልኝም አትበል፡፡ ሌስተርን ያየ እንዲህ አይልም፡፡ ለወትሮው የእንግሊዝ እግር ኳስ ማንቸስተር ዮናይትድና ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሴናልና ቼልሲ በእግራቸው ርግጥ፣ በእጃቸው ጭብጥ አድርገው የሚዘውሩት ይመስል ነበር። መቼም ዋንጫውን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ እንጂ ሌላው ይቀምሰዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ‹ሙሴ በሩቁ ከነዓንን አያት እንጂ አልወረሳትም› እንደሚባለው ሌሎቹ ቡድኖች ዋንጫውን በሩቁ ከማየት አልፈው ይወርሱታል ብሎ ማን ያስብ ነበር፡፡
ወዳጄ በዚህ ዓለም ላይ የማይነጠቅ የተጨበጠ፣ የማይንሸራተት የተረገጠ የለም፡፡ nothing for granted ይሉ የለም ስታድየሙን ሞልተው የሚጨፍሩት እንግሊዞች፡፡ የጨበጥክበት እጅህ፣ የረገጥክበት እግርህ አንድ ቀን ይዝላል፡፡ የትናንት አይበገሬነትህ፣ የትናንት ጀግንነትህ፣ የትናንት ክብርህ፣ የትናንት አሸናፊነትህ፣ የትናንት ተፈሪነትህ በዛሬ ጥረት ካልታገዘ ታሪክና ቅርስ እንጂ ድልና ውጤት አይኖርህም፡፡ አታያቸውም እንዴ እነ ማንቸስተር ዩናይትድና እነ ማንቸስተር ሲቲ ከአራቱ ውስጥ ለመግባት መከራቸው ሲያዩ? አታያቸውም እንዴ እነ አርሴናል ከቀበሮ አምልጦ ዛፍ ላይ እንደወጣ ዶሮ ካሁን አሁን ከአራቱ ወረድን እያሉ ሲጨነቁ? አላየኸውም እንዴ ስንት ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የኖረው አስቶንቪላ ተሰናብቶ ከሊጉ ሲወርድ፡፡
ዓለም እንደዚህ ናት፡፡ ድል በታሪክ ቢሆን ኖሮ ከሊቨርፑል በላይ ማን ዋንጫ ይወስድ ነበር፡፡ ምን እዚያ ወሰደህ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ዋንጫ የጠነሰስን፣ የአፍሪካን እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንስ የመሠረትን አልነበርንምን? ከብዙዎቹ ቀድመን ኳስ ተጫውተን፣ ከብዙዎቹ ቀድመን ዋንጫ አልበላንምን? ከብዙዎቹስ በፊት የአፍሪካን የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አልመራንምን? ዛሬ ግን የት ነን? ትዝታ ሆነናል፡፡ ዋንጫ እንደ መንግሥተ ሰማያት፣ ድልም እንደ ሰማይ ርቆናል፡፡
ሊቃውንቱ ‹ድል ማለት ጥረትና ዕድል የሚገናኙባት አጋጣሚ ናት› ይላሉ፡፡ አንተ ትታገላለህ፣ ትጥራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትወጣለህ፣ ትወርዳለህ፤ እንዲህ ባለማቋረጥ ስትታገል አንድ ቀን የአንተ የጥረትህ መንገድ ከዕድል መንገድ ጋር ይገናኝና ታቋርጠዋለህ፡፡ ያኔ አይወድቅም የተባለው ወድቆ፣ አይሸነፍም የተባለው ተሸንፎ፣ አይነቀነቅም የተባለው ተነቅንቆ፣ አይፈርስም የተባለው ፈርሶ፣ አይነካም የተባለው ተነክቶ ቦታውን ሲለቅ ታየዋለህ፡፡
አንተ ካልጣርክና ካልታገልክ፣ ካልሠራህና ካልሞከርክ ግን በዕድል ብቻ የሚሆን ነገር የለም። ዛሬ አላሸነፍክም? ተስፋ አትቁረጥ፤ ቢያንስ የማሸነፍ ሞራልና የማሸነፍ ተስፋ አለህና፡፡ የሚሸነፍ ትግል የለም፡፡ የሚሸነፍ ሰው እንጂ፡፡ ትግል ትግልን ይወልዳል፣ ጥረት ጥረትን ይተካል፣ ሙከራ ሙከራን ያመጣል፡፡ ዛሬ አንድ አካፋ አፈር ከተራራው ላይ ስታነሣ ተራራውን አልናድከው ይሆናል፡፡ በርግጠኝነት ግን የተራራውን መልክ ቀይረኸዋል፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች፣ ወይም አንተ ራስህ እንኳን የተራራው መልክ መቀየሩን ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ተራራው ራሱ ግን ያውቀዋል፡፡ የመሬት መሸርሸር የሚባለው ግማሽ ተራራ ተሸርሽሮ አይደለም‘ኮ፡፡ ውኃ እያሳሳቀ አፈሩን በየጊዜው ሲወስደው ነው፡፡
ምናልባትም ምንም አታመጣም ብለው ሰዎች ይነግሩህ ይሆናል፡፡ ሌስተርን ተመልከቱ በላቸው። ሌስተር የት ነበረ፡፡ አምና ቼልሲ ዋንጫውን ሲወስድ፣ ማንቸስተር ሲቲ ሁለተኛ ሆኖ ሲጨርስ፣ አርሴናልና ማንቸስተር ዩናይትድ ሦስትና አራተኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ፣ ሌስተር የት ነበር? እስከ ሰባት፣ እስከ ዐሥር ደረጃ ብትፈልገው ታገኘዋለህን? ፈጽሞ፡፡ ሌስተር ከወራጅ ቀጠናው በአራት ደረጃ ርቆ፣ ከወራጁ ከሁልሲቲ በ7 ነጥብ ብቻ በልጦ 14ኛ ደረጃ ላይ ነበረልህ፡፡
ዘመን መሰላል ነው፡፡ የወጣው ሲወርድ፣ የወረደው ሲወጣ ይገናኙበታል፡፡ በአንድ ዓመት ልዩነት የቸልሲን ቦታ ሌስተር፣ የሌስተርንም ቦታ ቼልሲ ይዞ አየነው። እንዳያርግ ስንፈራው የነበረው ቼልሲ እንዳይወርድ ተሳቀቅንለት፡፡ ‹የናቁት ይወርሳል› እንደተባለው አራቱን ኃያላን ገፍቶ ሌስተር መጣና እንደ ሽሮ ቅቤ በአናት ተቀመጠ፡፡ ‹ይሞታል ያሉት ተርፎ፣ ይቀብራል ያሉት ሞተ› ሲባል አልሰማህም?
እናም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ግፋ፣ ጣር፣ ታገል፣ ሥራ፣ ሞክር፣ ድፈር፤ ድል ይጠራቀማል፡፡ አንድ ቀን ከላይ ያየሃቸው ኃያላን እንደ ቼልሲ ደክመው፣ እንደ አርሴናል አርጅተው፣ እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀልብ ርቋቸው፣ እንደ ሲቲ ነገር ዓለሙ ዞሮባቸው ታገኛቸዋለህ፡፡ ያኔ እንደሌስተር ገፋ ገፋ አድርገህ ከላይ ቁጢጥ ነው፡፡ ሰውን መናቅ እንጂ በሰው መናቅ አይጎዳም፡፡ ሰውን መናቅ ትዕቢትን ወልዶ ስንፍናን ያመጣል፡፡ በሰው መናቅ ግን እልህን ወልዶ ትግልን ይፈጥራል፡፡ እናም አሸናፊነትህ የሚወሰነው ሰዎች ባንተ ላይ ባላቸው አመለካከት አይደለም፤ አንተ በሌሎች ላይ ባለህ አመለካከት እንጂ፡፡ እንዴት ያዩኛል? ብለህ አትጨነቅ፡፡ እንዴት አያቸዋለሁ? ብለህ ግን አስብ፡፡ እያሸነፍክ ስትመጣ የማያዩህ ሁሉ ያኔ ያዩሃል፣ የጠሉህ ያኔ ይወዱሃል፣ የናቁህ ያኔ ያደንቁሃል፡፡ የበለጠ ወደ ማይክራፎኑ በተጠጋህ ቁጥር የበለጠ ድምጽህ ይሰማል፡፡
እንዲያውም ሲንቁህ መልካም ነው፡፡ ጫና አይበዛብህም፤ ጠላት አይበዛብህም፤ ተገዳዳሪ አይበዛብህም፤ ጉልበትህን ለሥራህና ለዓላማህ ብቻ እንድታውለው ጊዜ ታገኛለህ፡፡ ሰዎች ዓይናቸውን ቼልሲ ላይ ያርጉልህ፣ ማንቸስተር ላይ ይጣሉልህ፣ ሲቲ ላይ ያኑሩልህ፣ አርሴናል ላይ ያትኩሩልህ፡፡ አንተ ዝም ብለህ ሥራና እንደ ሌስተር እየገፋህ ና፡፡ መንደርህ ትንሽ ናት? ስምህን የሚያውቀው የለም? ገንዘብህ ጥቂት ነው? የተሰጠህ ግምት አነስተኛ ነው? ባንተ የሚተማመኑ የሉም ወይም ጥቂት ናቸው? እነዚህ ሁሉ ካልለወጡህ ልትለውጣቸው ትችላለህ፡፡
እንደ ንሥር ታድሰህ፣ እንደ እባብ አፈር ልሰህ፣ እንደ ከራድዮን ራስህን ለውጠህ እስካልመጣህ ድረስ እንደ ቼልሲ ትናንት ዋንጫ በልተህ ዛሬ መውረድህ የማይቀር ነው፡፡ ወደ ላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው፡፡ ጊዜ ይለወጣል፣ ሐሳብ ይለወጣል፣ ወዳጅ ይለወጣል፣ አሠራር ይለወጣል፣ እሴቶች ይለወጣሉ፡፡ አንተም ትናንት የሠራኸውን ብቻ እየዘፈንክ፣ የትናንቱንም ታሪክ ብቻ እየተረክህ፣ ‹ትናንት እንዲህ ያደረግኩት እኔ ነኝ› ብለህ እየፎከርክ መኖር አደገኛው አኗኗር ነው፡፡ ‹ሆ› ብለው ያወጡህ ‹ውይ› ብለው እንዳያወርዱህ፣ ‹ጀግና› ብለው የሰቀሉህ፣ ‹ፈሪ› ብለው እንዳይጥሉህ፤ ‹ጉሮ ወሸባዬ› የዘፈኑልህ፣ ‹ዋይ ዋይ የት ትሄዳለህ› እንዳይሉህ፣ ‹ያለ አንተ› ያሉህ ‹ካንተ በቀር› እንዳይሉህ፡፡ የኮሩብህ እንዳያፍሩብህ፣ ‹እዩኝ እዩኝ› ብለህ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› እንዳትል ከፈለግክ መንገዱ አንድ ብቻ ነው፡፡ የትናንቱን ለታሪክ ተወውና ለዛሬው የሚያስፈልግህንና የሚገባህን ሥራ ሥራ፡፡ ከታሪክ ተማር እንጂ ታሪክ ላይ አትተኛ፡፡
አታይም፤ እዚህ ሀገር እንኳን የሊቨርፑል ዘመን አልፏል፡፡ ዛሬ በሃምሳዎቹና በስድሳዎቹ ውስጥ ያሉ የኳስ አፍቃሪዎች በዘመናቸው የሊቨርፑል ደጋፊዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የእነርሱ ልጆች እንኳን ሊቨርፑልን አይደግፉም፡፡ ያማ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መጥቶ፡፡ ዘመን ተቀይሮ፤ ደጋፊም ተደጋፊም ተቀይሮ፡፡ አዲስ ጀግና መጥቶ፣ አዲስ ተከታይ አፍርቶ፡፡ ያም ዘመን አለፈ፡፡ የነማንቸስተርና የነአርሴናልም ዘመን መጣ፡፡ እርሱም ሊያልፍ ነው መሰል፣ ደግሞ የነ ሌስተርና የነ ቶተንሐም ዘመን መጣ፡፡
‹በቃ ጨርሻለሁ› ወይም ‹በቃ ተጨርሻለሁ› አትበል፡፡ ‹አለቀ›ም ‹አለቀልኝ›ም አትበል፡፡ ካንተ በፊት ሌሎች ነበሩ፡፡ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ። ‹ታግለን ጨርሰናል› ያሉ እንደ ቼልሲ ቦታ እየለቀቁ፣ ‹ገና ይቀረናል› የሚሉ ታጋዮች እንደ ሌስተር ቦታውን እየተረከቡ ይሄዳሉ፡፡ ሕይወት ሌስተርና ቼልሲ ናት፡፡