በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ወርሃዊ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ካለፈው ወር ሁለት ደረጃዎችን አሻሽላለች።
በኬንያ አስተናጋጅነት ለ39ኛ ጊዜ በተካሄደው የ2017 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ሴካፋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሩብ ፍፃሜ ላይ መሰናበቱ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ እና ግብፅ በአህጉሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ሲይዙ በዓለም ደግሞ 23ኛ፣ 27ኛ እና 31ኛ ላይ ይገኛሉ።
ጀርመን ያለፈው ወር ደረጃዋን በማስጠበቅ በቀዳሚነት እየመራች ሲሆን፥ ብራዚል፣ፖርቹጋል፣ አርጀንቲና እና ቤልጂየም ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ በቅደም ተከተል ይዘዋል።
በህዳር ወር በነበረው ወርሃዊው የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ የዓለም ቀዳሚ ደረጃዎችን ጀርመን በአንደኝነት ስትመራ ብራዚል እና ፖርቹጋል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው መከተላቸው ይታወሳል።
ሴኔጋል ከዓለም 23ኛ ደረጃ ስትይዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተቀምጣለች።
ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ሞሮኮ በአፍሪካ ከሁለት እስከ አምስት ያለውን የደረጃ ሰንጠረዥ ይዘዋል።
በአንፃሩም አንጉሊያ፣ ጂብራልታር፣ ባህማስ፣ ሶማሊያ፣ ቶንጋና ኤርትራ የመጨረሻው 206ኛ ደረጃ ላይ ናቸው።
በወሩ ቫኑዋቱ 28፣ ቬትናም 13 እና ሞንጎሊያ 12 ደረጃዎችን ያሻሻሉ ሀገራት ሆነዋል።
በአንፃሩ ከፍተኛ የደረጃ ማሽቆልቆል ያሳዩት ደግሞ ኒካራጓ 13፣ ሰሜን ኮሪያ 12 እንዲሁም ቻይና እና ሊቢያ 11 በተመሳሳይ ደረጃዎችን ዝቅ ያሉ ሀገራት ናቸው።
(ኤፍ ቢ ሲ)

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ