ዓርብ 29 ዲሴምበር 2017

በፍሎሪዳ የተደረገው የባህር ውስጥ ሰርግ ብዙዎችን አስደምሟል

ከአራት ዓመት በፊት በመምህር እና አስተማሪነት የተገናኙት ጥንዶች በፍሎሪዳ አካባቢ በባህር ውስጥ ያደረጉት ሰርግ የብዙዎችን ቀልብ መሳቡ ተነግሯል።
የብሪታንያ መከላከያ ሀይል አባል የሆነው የ31 ዓመቱ ቶማስ ሞልድ እና የአሜሪካ ዜግነት ያላት አስተማሪው ሳንድራ ሀይድ፥ ከአራት ዓመት በፊት የውሃ የመጥለቅ ስልጠና ነበር በፍቅር ያገናኛቸው። ጥንዶቹ አራት አመት የቆየው የፍቅር ቆይታ በትዳር እንዲጣመሩ ምክንያት መሆኑን ተነግሯል።
ስለሆነም በፍሎሪዳ ሞላሰስ በሚባል ትልቅ የባህር ጠረፍ አካባቢ በሚገኘው የተቀደሰ ስፍራ የሰርግ ስነ ሰርዓታቸውን በባህር ውስጥ አካሂደዋል።
እነዚህ ባልና ሚስት በባህር ውስጥ አበባ ሲቀባበሉ እና የሰርጋቸው ስነ ስርዓት ሲፈፅሙ ከመካከላቸው አንድ ሰው ብቻ ነው የነበረው።
በዚህም በሰርጋቸው የተነሱት ፎቶግራፍ በግዛቲቱ የቱሪዝም የፌስ ቡክ ገፅ እንዲለጠፍ መደረጉን ተነግሯል።

ምንጭ፦(ኤፍ.ቢ.ሲ) www.upi.com

ለ47 ዓመታት ያህል ያልተከፈተው የገና ስጦታ

ብዙዎቻቸን የተሰጠንን ስጦታ ከፍተን ውስጡ ያለውን ለማየት እጅግ ጉጉ ነን። ከወደ ካናዳ የተሰማው ግን ከዚህ ለየት ያለ መሆኑን ነው የተነገረው። ይህም አንድ ካናዳዊው ከ47 ዓመት በፊት ከሴት ጓደኛው ያገኘው የገና ስጦታ እስከ አሁን አልከፈተውም።
አድሪያን ፔርስ በአውሮፓውያን 1970 በ17 ዓመት እድሜው በቶሮንቶ ግዛት በሚገኘው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ነበር ጓደኛው የተለየችው። 
በዚያን ወቅት የነበረችው የመጀመሪያዋ የሴት ጓደኛው፥ በፖስታ መልክ በማሸግ የገና ስጦታ ካበረከተችለት በኋላ ግንኙነታቸውን ወድያውኑ ማቋረጡ ተነግሯል። 
በዚህም አድሪያን ፔርስ በጣም አዝኖ እንደነበር እና በመለያየታቸው ምክንያት ለ47 ዓመታት በብስጭት እንደነበረ ነው የተጠቆመው።
ስለሆነም ስጦታው በቀላሉ በገና ዛፍ ሥር ከጣለው በኋላ ያልተከፈተ መሆኑን የሚያስታውሰው በገና በዓል ቀን ብቻ ነበር።
ለቤተሰቦቹም ፈፅሞ እንደማይከፍተው በየጊዜው ይናገራቸው እንደነበር ተጠቁሟል።
በዚህም የገና ስጦታው ሳይከፈት 47 ዓመታት አልፎታል።

(ኤፍ ቢ ሲ)http://www.odditycentral.com

ሶማሊያ ከ27 ዓመታት በኋላ የአየር ክልሏን በራሷ መቆጣጠር ጀመረች

ሶማሊያ ከ27 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአየር ክልሏን በራሷ መቆጣጠር እና ማስተዳደር መጀመሯን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዶላሂ (ፋርማጆ) አስታውቀዋል።
የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር የአየር ክልል መቀመጫውን ኬንያ ናይሮቢ ባደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ቁጥጥር ስር ነበር ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ሲተዳደር የነበረው።
ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዶላሂ፥ በሞቃዲሾ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አስፈላጊው ቁሳቁስ የተሟላለትን የአየር ክልል መቆጣጠሪያ ቢሮ መርቀው ሲከፍቱ ነው ሶማሊያ የአየር ክልሏን በራሷ መቆጣጠር መጀመሯን ያበሰሩት።
“የአየር ክልላችን መልሰን በራሳችን አቅም መቆጣጠር መቻላችን በጣም ኩራት እንዲሰማን ያደርጋል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ቀኑንም ታሪካዊ ነው ብለዋል።
“ይህ በቀላሉ እና በእድል የመጣ አይደለም፤ የጠንካራ ስራ ውጤት እንጂ” ሲሉም ፕሬዚዳንት ሞሀመድ አብዶላሂ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ የሀገሪቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የሲቪል አቪዬሽን ሰራተኞች እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ የሶማሊያ አውሮፕላን ማረፊያን በማስተዳደር ላይ የሚገኘውን ዓለም አቀፉን የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አመስግነዋል።
ሶማሊያ ለበርካታ ዓመታት ከአሸባሪው አልሸባብ ጋር ጦርነት ውስጥ የነበረች ሲሆን፥ በጦርነቱም በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሞተው በሚሊየን የሚቆጡ ዜጎች ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

ምንጭ፦(ኤፍ.ቢ.ሲ) africa.cgtn.com

ረቡዕ 27 ዲሴምበር 2017

የጃፓኑ አልባሳት አምራች ዩኒቅሎ በኢትዮጵያ ፋብሪካውን ከፈተ

የጃፓኑ አልባሳት አምራች ኩባንያ ዩኒቅሎ በአፍሪካ የመጀመሪያውን አልባሳት ማምረቻ በኢትዮጵያ መክፈቱን አስታወቀ።
አልባሳት ማምረቻ ፋብሪካው የሙከራ ምርቱን በቅርብ ጊዜ ይጀምራል ተብሏል።
ፋብሪካው ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብም ከፋብሪካው ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
የፋብሪካው ምርቶች በዋናነት ለአሜሪካና አውሮፓ ገበያዎች ይቀርባሉም ነው የተባለው።
በኢትዮጵያ ያለው ርካሽ የሰራተኛ ጉልበትና በአሜሪካ ገበያዎች ለኢትዮጵያ ምርቶች የሚሰጠው ማበረታቻም ፋብሪካውን በኢትዮጵያ ለመትከል እንዳበቃውም ፋብሪካ ገልጿል።
ከዚህ ባለፈም ከሌሎች ሃገራት በተሻለ ኢትዮጵያ ለአውሮፓ ገበያዎች ቅርብ መሆኗ ተመራጭ እንዳደረጋትም ጠቅሷል።
አለም አቀፉ የጃፓን ኩባንያ ሹራብ፣ ሸሚዝ፣ ቲሸርት ሱሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ አልባሳትን ዲዛይን በማድረግ፣ በማምረትና በማዘጋጀት ይታወቃል።
ምርቶቹንም በዋናነት በእስያ፣ በአሜሪካና አውሮፓ ገበያዎች በመላክ ትርፋማ መሆኑም ይነገራል።

ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ) asia.nikkei.com

እሑድ 24 ዲሴምበር 2017

ከሁለት ወር በፊት ጠፍቶ የነበረ 1 ሚሊየን ዶላር የሚያሸልም ሎተሪ ድንገት ተገኘ

አሜሪካዊቷ እድለኛ ሴት 1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊ ያደረጋቸውን የሎተሪ እጣ ቁጥር የያዘ ትኬት ለሁለት ወራት ያህል የት እንዳስቀመጡት አላስታወሱትም ነበር።
በምዕራባዊ አሜሪካ አይኦዋ ግዛት ነዋሪ የሆኑት ካሬን ሀርጌር ለግዛቱ የሎተሪ ፅህፈት ቤት ባለስልጣናት እንደተናገሩት፥ የሎተሪ እጣ ቲኬቶች ለጥቂት ሳምንታት የማከማቸት ልምድ አላቸው።
በዚህም ከሁለት ወር በፊት የቆረጡትን የሎተሪ ትኬት የት እንዳስቀመጡት ባለማዎቃቸው እድለኛነታቸውን ሳያረጋግጡ ቆይተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት ግን ድንገት የሎተሪ ቲኬቱ በኮምፒውተር ውስጥ ተቀመጦ ያገኙት ሲሆን፥ ይህም የህዳር 4 የሎተሪ እጣ አሸናፊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። 
ሀርጌር “ የሎተሪ ቁጥሩን በኮምፒተር እንደገና ለማረጋገጥ ስለተቸገርኩ፥ ባለቤቴን ለማየት እንዲችል አደረግኩት" ብለዋል።
በዚህም በጣም ፈርተው እንደነበር የገለፁት ሀርጌር፥ የ1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አሸንፈናል ሲሉ ደስታቸው ገልፀዋል።
የሎተሪ ትኬቱን በድንገት እስኪያገኙት ድረስ ግለሰቧ የሎተሪ እጣ እንደደረሳቸው ምንም አያውቁም ነበር ነው የተባለው።
ከዚህ በፊት ከፖወርቦል የሎተሪ ትኬት ያገኙት ከፍተኛው የገንዘብ ሽልማት 10 የአሜሪካ ዶላር ብቻ እንደነበርም ነው ተናግረዋል።
የትኬቱ መገኘት ግለሰቧ የ1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሽልማታቸውን ከአይኦዋ ሎተሪ ፅህፈት ቤት ለመቀበል አስችሏቸዋል።
ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ) upi.com

የአውሮፓ ህብረት 10 ሺህ ስደተኞችን ከሊቢያ ሊቀበል ነው

 2010 የአውሮፓ ሀብረት በሊቢያ ካምፖች ውስጥ ታጉረው ከሚገኙ ስደተኞች ውስጥ 10 ሺህ ያክሉን ሊቀበል መሆኑን አስታውቋል።
ስደተኞቹ በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት 2018 ወደ በጣሊያን በኩል አውሮፓ ሀገራት እንዲገቡ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፥ ይህም በሊቢያ ካምፖች ውስጥ ኢ ሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀምባቸውን ስደተኞች የማዳን ተልእኮ እንዳለው ታውቋል።
የጣሊያን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማርኮ ሚኒቲ እንደተናገሩት፥ ስደተኞች ለህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች እንግልት ሳይጋለጡ እና በባህር ላይ ከሚደርስባቸው አደጋ በፀዳ መልኩ ወደ አውሮፓ የሚገቡበት መንገድ ይከፈታል ብለዋል።
“በአዲሱ የአውሮፓውያኑ 2018 እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሳይጥሉ በሚከፈተው መንገድ ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ይደረጋል” ሲሉም ተናግረዋል።
ማርኮ ሚኒቲ አያይዘውም የዓለም መንግስታት ባለስልጣናት እና የሊቢያ መንግስት በአውሮፓውያኑ 2018 ቁጥራቸው እስከ 30 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። 
በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ከ400 ሺህ እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሸጋገር በሚል ሊቢያ ውስጥ ታጎረው ይገኛሉ።
ምንጭ፦ (ኤፍ.ቢ.ሲ) www.presstv.com

የቂሊንጦ መድኃኒት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 75 በመቶ ተጠናቋል

የቂሊንጦ መድኃኒት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ 75 በመቶ መጠናቀቁን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ኩባንያዎችን በስፋት ለማሳተፍ በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እየገነባች መሆኑ ይታወቃል። 
ከነዚሁ ፓርኮች መካከል በ270 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ከ2009 ዓ.ም የካቲት ወር ጀምሮ በቻይናው ቲ ሴ ጁ ሲቪል እንጂነሪግ ግሩፕ እየተገነባ ያለው የቂሊንጦ መድኃኒት ማምረቻ ኢንዱስተሪ ፓርክ አንዱ ነው። 
ከ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቀው ይህ ፓርክ ከዓለም ባንክ በብድር በተገኘ ገንዘብ በመገንባት ላይ ሲሆን በመጭዎቹ ሶስት ወራት ግንባታው እንደሚጠናቀቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል። 
በኮርፖሬሽኑ የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፕሮጀክት ኢንጅነር የጌታሁን አገኘሁ ለኢዜአ እንዳሉት የግንባታው ዋና ዋና የሚባሉ ሥራዎች ተጠናቀዋል።
ግንባታውን በአንድ ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ የታቀደ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት የፓርኩ ግንባታ 75 በመቶ ተጠናቋል ብለዋል።
የስድስት ወኃ ጉድጓዶች ቁፋሮና 2 ትልልቅ የውሃ ማከማቻ ማማዎች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በፓርኩ ውስጥ የሚካሄደው የመንገድ ግንባታና አቋርጦ የሚያልፈውን ወኃ ማሸገሪያ ሶስት ድልድዮች ሥራዎችም መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። 
ለመድኃኒት ማምረቻ ሼዶች ግንባታ ቦታውን ምቹ ለማድረግ የሚከናወኑ የአፈር ቆረጣና መሙላት ስራዎችም በአብዛኛው መጠናቀቃቸውን የተናገሩት አቶ የጌታሁን እየተገነባ ባለው መንገድ ግራ እና ቀኝ ጎርፍ ማስወገጃ ቱቦዎች ስራም 95 በመቶ መከናወኑን አንስተዋል። 
የፓርኩ የአስተዳደር ህንጻ ግንባታ እተየገባደደ መሆኑን የጠቀሱት ኢንጅነር የጌታሁን የፓርኩ አጥር፣ ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር፣ የኤሌክትሮኒክስና ቴሎኮም መስመር ዝርጋታ ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። 
ከዲዛይንና ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ምክንያት ሥራው በሚጠበቀው ፍጥነት እንዳልተጓዘ ነው የተናገሩት።
እንደ ፕሮጀክት ኢንጅነሩ ገለፃ ''በአጋጠሙ ችግሮች ምክንያት የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ግንባታውን የሚያካሂደው ተቋራጭ ቀንና ማታ ከሁለት ሽፍት በላይ እየተሰራ ነው።'' 
የፓርኩ ግንባታ ሲጠናቀቅ 18 ኪሎ ሜትር የሚረዝም አስፋልት መንገድ፣ የውሃ አቅርቦት አገልግሎቶች፣ የሎጅስቲክ ሼዶች፣ የአረንጓዴ ቦታዎች፣ መጋዘኖች፣ መዝናኛ ማዕከላት፣ የቢዝነስ ማከላት፣ መኪና ማቆሚያ ቦታዎችን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ይሆናል። 
ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ከሚያስፈልጋት መድኃኒት 80 በመቶ ያህሉን ከውጭ አገራት በከፍተኛ ውጭ ምንዛሬ የምታስገባ ሲሆን፥ የቂሊንጦ መድኃኒት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፍላጎቱን በአገር ውስጥ ምርት ከመሸፈን ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል።
ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ) ኢዜአ

የንግድ ፍቃድ እድሳት ያደረጉ ነጋዴዎች ከሃምሳ በመቶ በታች መሆኑ ተገለጸ

 የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ2010 በጀት ዓመት የንግድ ሥራ ፍቃድ ዕድሳት ያደረጉ ነጋዴዎች ከሃምሳ በመቶ በታች መሆናቸውን አስታወቀ፡፡የንግዱ ማህበረሰብ እስከ ታኀሣሥ 30 ያለ ቅጣት እንዲያሳድስ ጥሪ አቀረበ። 
የቢሮው የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ተገኝ ትናንት እንዳስታወቁት፣ቢሮው ከሐምሌ አንድ እስከ ታኀሣሥ30/2010 ድረስ ለ276ሺ 688 ነጋዴዎች የፍቃድ ዕድሳት ለማድረግ አቅዶ እስከ ታኀሣሥ 12/2010ዓ.ም ዕድሳት ያደረገው ለ122ሺ752 ነጋዴዎች ብቻ ነው፡፡ይህም የዕቅዱ 47 በመቶ ነው።
እንደ አቶ ብርሃኑ ማብራሪያ ነጋዴዎች የፍቃድ ዕድሳት እንዳያደርጉ አንዱ ምክንያት ከቀን ገቢ ግመታ ጋር ተያይዞ ቅሬታ በማስገባታቸው ነው፡፡ ይሄም ቤት ለቤት ቅስቀሳ በሚደረግበት ወቅት ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት ቅሬታ ያስገቡ ነጋዴዎች ፍቃድ እንዲያድሱ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ቅሬታ ያላቸው የንግዱ ማህበረሰብ ቅሬታችን አልታየም በሚል በክሪላንስ እጦት ፍቃዳቸውን ሳያድሱ ለቅጣት እንዳይዳረጉ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጋር በመነጋገር ክሪላንሱ እንዲሰጣቸው አቅጣጫ መቀመጡን አብራርተዋል፡፡ ክሪላንስ ወስደው ፍቃዳቸውን ካደሱ በኋላ በየትኛውም ጊዜ ቅሬታቸው ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
አብዛኛው ነጋዴ በታኀሣሥ ወር ንግድ ፍቃዱን የማደስ ባህል እንዳለው የተናገሩት ዳይሬክተሩ፣ በቀረው ጊዜ ውስጥ ክሪላንስ ወስደው ማደስ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ነጋዴውን ለማስተናገድ ሠራተኞች ከሥራ ቀን በተጨማሪ ቅዳሜ እና እሁድን ጭምር እንደሚያገለግሉ አስታውቀዋል፡፡
‹‹የንግድ አዋጁ ነጋዴው ማህበረሰብ እስከ ታኀሣሥ 30 ብቻ ፍቃዱን እንዲያድስ ነው የሚያዘው ›› ያሉት አቶ ብርሃኑ የጥር ወር ከገባ በኋላ ግን ፍቃድ ለማደስ 2ሺ 500 ብር ቅጣት እንዳለውና ይሄም ጊዜው በጨመረ ቁጥር እያደገ የሚሄድ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡
 አዲስ ዘመን (ሰብስቤ ኃይሉ)

የሞባይል ስልክ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ ነው ► የብረት አቅርቦት ይሻሻላል

የሞባይል ኢንዱስትሪው ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የአርማታ ብረት ጥሬ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ እየገባ በመሆኑ የብረት አቅርቦት ሊሻሻል እንደሚችል ተገልጿል።
የኢንስቲትዩቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ በተለይ ለጋዜጣው ሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 12 የሞባይል ስልክ ማምረቻ ኩባንያዎች አሉ። በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙት እነዚህ ኩባንያዎች የአገር ውስጥ ገበያን አሟልተው ምርቶቻቸውን ወደውጭ ኤክስፖርት በማድረግ 14 ሚሊዮን488ሺ 775 ዶላር ገቢ አስገኝተዋል።
የኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፉ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ወቅት ላይ ማቆጥቆጥ ጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ዕድገት ማሳየቱንና አገራዊ ኢኮኖሚውን በመደገፍ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል። ባለፉት አምስት ወራት ብቻ ከኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ ዘርፉ 16ሚሊዮን 969ሺ 72 ዶላር የተገኘ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ ከፍተኛውን የኤክስፖርት ድርሻ የያዘው የሞባይል ስልክ ሽያጭ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሄ የሞባይል ስልክ ምርት ኤክስፖርት የሚደረገው በቴክኖሎጂ ከኢትዮጵያ ሻል ብለው በሚገኙ አገራት ጭምር መሆኑን የተናገሩት አቶ ፊጤ ፣ከነዚህም መካከል ናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ አገራት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ።
በኢንቨስትመንቱ ከተሰማሩ ከ12ቱ ኩባንያዎች መካከል አራቱ የአገር ውስጥ ሲሆኑ፣ አብዛኛቹ የውጭ ኩባንያዎችና በሽርክናም የሚሰሩ ናቸው።ኩባንያዎቹ በአገር ውስጥ እሴት ጨምሮ በመገጣጠም ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ። እንደ ኩባንያዎቹ አቅም የፈጠሩት የሥራ ዕድል የተለያየ ቢሆንም ከአንድ ሺ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።ተቀጣሪዎቹ ወጣቶች በመሆናቸው ደግሞ ከሥራ ዕድሉ በተጨማሪም ቴክኖሎጂውን በመቅዳት ለነገ እያስቀሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በተያያዘም በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ምክንያት ለዘጠኝ ወራት ተይዞ የነበረው የአርማታ ብረት የጥሬ ዕቃ ግዢ ችግር መፈታቱን አቶ ፊጤ አስታውቀዋል።ባለሀብቶቹ ጥሬ ዕቃ መግዛት ባለመቻላቸው በብረት ምርት አቅርቦት እና ዋጋ ላይ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ፈጥሮ እንደነበር ገልጸው ፣መንግሥት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ እና የውጭ ምንዛሪም በመገኘቱ ምክንያት አንዳንድ ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃውን ማስገባት መጀመራቸውን ተናግረዋል። የብዙዎቹ ደግሞ ወደብ ላይ ደርሷል። የጥሬ ዕቃ መግባት የብረት ምርት እንዲመረትና በገበያ ላይ ያለው እጥረትና የዋጋ ንረት እንዲሻሻል የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአገሪቱ የሚገኙ የብረት ኢንዱስትሪዎች በዓመት ከአምስት ሚሊዮን ቶን በላይ ብረት የማምረት አቅም እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል።
አዲስ ዘመን (አልማዝ አያሌው)

ዓርብ 22 ዲሴምበር 2017

sami dan


በአንድ የሙዚቃ ድግስ 53 ስልኮችን ከሰዎች ኪስ የሰረቀው ወጣት በ3 ዓመት እስር ተቀጣ

በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተዘጋጀ አንድ የሙዚቃ ድግስ ላይ የሴቶችን የመዋኛ ልብስ ተጠቅሞ በስፍራው ከነበሩ ሰዎች ሰዎች ኪስ በመበርበር 53 ስልኮችን የሰረቀው ግለሰብ በሶስት ዓመት እስር ተቀጥቷል።
ወጣቱ ሮማኒያዊ ሲሆን አሊን ማሪን ይባላል፤ የ22 ዓመት ወጣት ነው።
ማሪን በበርሚንግሃም በተዘጋጀ አንድ የሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቁር እና ሃምራዊ ቀለም ያለው ከሰውነት ጋር ጥብቅ የሚል እና ሲያስፈልግ የሚለጠጥ የሴቶች የመዋኛ ልብስ ከውስጥ እና ጥንድ ጂንስ ሱሪ ለብሶ ታድሟል።
የሴቶችን የመዋኛ ልብስ የለበሰውም የሰረቃቸውን ስልኮች በሙሉ ለመደበቅ እንዲያስችለው እና ሌሎች ተጨማሪ ስልኮችን እንዲሰርቅ ነው።
በዚህ መልኩ በሙዚቃ ድግሱ ሰዎች በጣም ተጠጋግተው በሚጨፍሩበት አካባቢ ይጠጋል።
ይህን ያደረገውም በርካታ ሰዎች እየተገፋፉ ስለሚጨፍሩ እና ከፍተኛ ድምፅ ስላለ ከታዳሚያኑ ኪስ እየገባ ለመስረቅ እንዲያመቸው ነው።
በዚህም መሰረት ስልኮችን ከሚጨፍሩት ሰዎች ኪስ ያምንም ስጋት እያወጣ ከውስጥ በለበሰው የሴቶች የመዋኛ ልብስ ማስቀመጥ ጀመረ።
በዚህ ጊዜ በአጠቃላይ በሰውነቱ ውስጥ 53 ስልኮችን የያዘ ሲሆን፥ ይህም ህይወት ያለው ሳጥን አስመስሎታል።
ዓላማውን ያሳካው ወጣቱ ማሪን ከሙዚቃ ድግሱ ለመውጣት ሲያስብ ድንገት በዙሪያው የነበሩ የደህንነት ሰዎች ዓይን ውስጥ ገባ።
በተጨናነቀው የህዝብ ብዛት ውስጥ የፀጥታ ስራን እየተከታተሉ የሚገኙት የደህንነት ሰዎች፥ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ዝርፊያ መከናወኑን መረጃው ስላላቸው በማሪን ላይ ክትትል ማድረግ ጀመሩ።
ማሪን በሙዚቃ ድግሱ በርካታ ሰዎች ከተጨናነቁበት ቦታ ለመራቅ ጥረት ሲያደርግ በደህንነት ሰዎች እጅ ገባ።
ስልኮችንም በመኪና ማቆሚያ አቅራቢያ ለማስቀመጥ ሲሞክር ነው የታየዘው።
የበርሚንግሃም ከተማ ፖሊስ መኮንን ጁሊያ ስላተር እንደተናገሩት፥ ማሪን ያካሄደው የኪስ ስርቆት በተጠና እና በታቀደ ሁኔታ የተፈፀመ ነው።
በርካታ ስልኮች በሙዚቃ ድግሱ ከታደሙ ሰዎች ንብረታቸውን በጥንቃቄ ያስቀምጥልናል ብለው ካሰቡት የፊት የጅንስ ኪስ ነው የተሰረቁት።
ሰዎቹ ስልካቸውን ማንም ሊነካው የማይችል ቦታ ላይ አስቀምጥናል ብለው በነፃነት በሚጨፍሩበት ጊዜ መዝናናቱ ሁሉን ነገር ስልሚያስረሳቸው ማሪን በቀላሉ ስልኩን ለመስረቅ አመች ሆኖለታል ይላሉ የፖሊስ መኮንኑ።
ስርቆቱ ከተፈፀመ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላም የበርሚንግሃም ንጉሳዊ ፍርድ ቤት የዙፋን ችሎት በያዝነው ሳምንት በማሪን ላይ የሶስት ዓመት የእስር ቅጣት በይኖበታል።
ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ)ኦዲቲ ሴንትራል

ሐሙስ 21 ዲሴምበር 2017

የአለማችን ቁጥር አንድ ተጠባቂ ጨዋታ ነገ ይካሄዳል ፡፡



የሁለቱ ክለቦች የበላይነት በነገሠበት የስፔን የክለቦች ፉክክር ውስጥ፤ባርሴሎናሪያል ማድሪድ የስፔን የላሊጋውን ማዕረግ ተቀዳጅተዋል። ኤልክላሲኮ ለመጀመሪያ ጊዜ በላሊጋ ጨዋታ የተከናወነው በየካቲት 17 1929 . .. በባርሴሎና ሜዳ ሲሆን ጨዋታውን ሪያል ማድሪድ 2-1ማሸነፍ ችሏል፡፡ በመጀመሪያው የኤልክላሲኮ ጨዋታ ለሎሳ ብላንካዎቹ የማሸነፊያ ጎሎችን ያስቆጠረዉ ሞሬራ የተባለዉ ተጫዋች 10 እና 55ኛዉ ደቂቃ ነዉ፡፡ ለካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሸንፈት ያልታደገችዉን ብቸኛ ጎል ማስቆጠር የቻለዉ ፔሬራ ነበር፡፡

የበርካታ የእግር ኳስ ከዋክብቶች መገኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሁለቱ ክለቦች በአለም እግር ኳስ ላይ የራሳቸውን አሻራ በማሳረፍ የስፖርት ቤተሰቡን ትኩረት ይስባሉ፡፡ ይህ የደርቢ ጨዋታ ዲያጎ ማራዶና፣ ዚነዲን ዚዳን፣ ሮናልዶ ሊዊስ ናዛሪዮ ዴሌማ፣ ጆሃን ክሩይፍ እና ሮናልዲንሆን ጨምሮ የዓለም ምርጥ ተጫዋቾችን ያፎካከረ ባለ ታሪክ ነው። በመላው ዓለም በሚያገኘው የቴሌቪዥን ተመልካች ብዛት፣ በገቢው ከፍተኛነት እና በውጤት የበላይነት የሚስተካከለው የሌለው የስፔኖቹ ሪያል ማድሪድ እና የባርሴሎና ፍልሚያ የዓለም ታላቁ የደርቢ ጨዋታ ነው፡፡ ኤል ክላሲኮ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ይህ የደርቢ ፍልሚያ በመላው ዓለም እስከ 500 ሚሊዮን የቲቪ ተመልካች የሚያገኝ፤ 200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የሚያመነጭም እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዓለም ላይ አሉ የሚባሉት ሁለት ምርጥ ተጫዋቾች ሊዮኔል ሜሲ እና ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እያፎካከረ ያለ የዓለማችን ታላቅ ደርቢ ነው።

በፊፋ ወርሃዊ ደረጃ ኢትዮጵያ 2 ደረጃዎችን አሻሻለች

 በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ወርሃዊ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ካለፈው ወር ሁለት ደረጃዎችን አሻሽላለች።
ይህን ተከትሎም በህዳር ወር ከዓለም 145ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው በታህሳስ ወር 143ኛ ደረጃን ይዛለች።
በኬንያ አስተናጋጅነት ለ39ኛ ጊዜ በተካሄደው የ2017 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ሴካፋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሩብ ፍፃሜ ላይ መሰናበቱ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ እና ግብፅ በአህጉሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ሲይዙ በዓለም ደግሞ 23ኛ፣ 27ኛ እና 31ኛ ላይ ይገኛሉ።
ጀርመን ያለፈው ወር ደረጃዋን በማስጠበቅ በቀዳሚነት እየመራች ሲሆን፥ ብራዚል፣ፖርቹጋል፣ አርጀንቲና እና ቤልጂየም ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ በቅደም ተከተል ይዘዋል። 
በህዳር ወር በነበረው ወርሃዊው የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ የዓለም ቀዳሚ ደረጃዎችን ጀርመን በአንደኝነት ስትመራ ብራዚል እና ፖርቹጋል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው መከተላቸው ይታወሳል። 
ሴኔጋል ከዓለም 23ኛ ደረጃ ስትይዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተቀምጣለች።
ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ሞሮኮ በአፍሪካ ከሁለት እስከ አምስት ያለውን የደረጃ ሰንጠረዥ ይዘዋል።
በአንፃሩም አንጉሊያ፣ ጂብራልታር፣ ባህማስ፣ ሶማሊያ፣ ቶንጋና ኤርትራ የመጨረሻው 206ኛ ደረጃ ላይ ናቸው።
በወሩ ቫኑዋቱ 28፣ ቬትናም 13 እና ሞንጎሊያ 12 ደረጃዎችን ያሻሻሉ ሀገራት ሆነዋል።
በአንፃሩ ከፍተኛ የደረጃ ማሽቆልቆል ያሳዩት ደግሞ ኒካራጓ 13፣ ሰሜን ኮሪያ 12 እንዲሁም ቻይና እና ሊቢያ 11 በተመሳሳይ ደረጃዎችን ዝቅ ያሉ ሀገራት ናቸው።
 (ኤፍ ቢ ሲ)

የለንደኑ ካፌ ደንበኞች ሚጠጡት ማኪያቶ ላይ ፎቶግራፋቸውን በመሳል ትኩረት ስቧል

 በእንግሊዝ ለንደን የሚገኝ አንድ ካፌ የባሪስታ ጥበብን ከፍ ወዳለ ደረጃ አድርሶታል እየተባለ ነው።
ቲ ትሬስ የተባለው ካፊቴሪያው ተጠቃሚዎች ወደ ካፌው ጎራ ሲሉ ባዘዙት ማኪያቶ አሊያም ካፑቺኖ ላይ የራሳቸውን ምስል መስራት በመቻሉ ነው ትኩረት የሳበው።
አዲሱ የካፌው አገልግሎት “ሰልፊቺኖ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ የደንበኞቹን ምስል በሚጠጡት ማኪያቶ አሊያም ካፑቺኖ ላይ በመሳል የሚያቀርብ የመጀመሪያ ካፌ ነው ተብሏል።
ምስላቸው በሚጠጡት ነገር ላይ እንዲሳልላቸው የሚፈልጉ ደንበኞች፤ በመጀመሪያ ስልካቸው ላይ የያዙትን ፎቶ ግራፋቸውን በመልእክት መላላኪያ መተግበሪያ አማካኝነት ለባሪስታው ይልኩለታል።
የተላከው ምስልም “ሲኖ” ወደ ተባለ ማሽን የሚላክ ሲሆን፥ ማሽኑም ምስሉን ስካን በማድረግ ከስሩ ተስተካክሎ በተቀመጠለት ትኩስ መጠጥ ላይ የምግብ ማቅለሚያዎችን በመጠቀም የተላከለትን ፎቶ ግራፍ ያትማል።
በዚህ መልኩ አንድ ምስልን አንድ ማኪያቶ ወይም ካፑቺኖ ላይ ለመስራት እስከ 4 ደቂቃ ይወስዳል የተባለ ሲሆን፥ አንድ ሰው ምስሉን በሚጠጣው ትኩስ ነገር ላይ ለማሳተም 7 የአሜሪካ ዶላር መክፈል አለበት።
ካፌው አገልግሎቱን ባሳለፍነው ቅዳሜ የጀመረ ሲሆን፥ እስካሁን ከ400 በላይ ፎቶ ግራፍ የተሳለበት ማኪያቶ እና ኩፑቺኖ መሸጡት ቲ ትሬስ ካፌ አስታውቋል።
“ሰልፊቺኖ” የተባለው ትኩስ መጠጥ በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች ላይም መነጋገሪያነቱ ጨምሯል ነው የተባለው።
ምንጭ፦ (ኤፍ.ቢ.ሲ) www.reuters.com

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ470 ሚሊየን ዶላር ብድር እና እርዳታ ሰጠ

 የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለእንሰሳትና አሳ ሀብት ምርት ማሻሻያ የሚውል የ470 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብድር እና እርዳታ ሰጠ።
የብድር ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ እና የዓለም ባንክ ተወካይ ካሮሊን ተርክ ናቸው።
ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ 300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩ በትምህርት መስክ በተለይ በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ የሚውል ነው።
ድጋፉ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በቂ የትምህርት አቅርቦት እንዲኖር እንደሚያስችልም ተነግሯል።
በተጨማሪም በእንሰሳት እና አሳ ሀብት ሀገሪቱ ያላትን አቅም በማሳደግ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚያግዝ ታምኖበታል።
 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤርሚያስ ፍቅሬ

በመዲናዋ የአሮጌ የውሃ መስመሮች በፕላስቲክ ቧንቧ የመቀየር ስራ 65 ኪሎ ሜትር ዝርጋታ ተከናወነ

 በመዲናዋ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም የተጀመረው የአሮጌ የውሃ መስመሮችን በፕላስቲክ ቧንቧ ቅየራ ስራ እስካሁን 65 ኪሎ ሜትር ዝርጋታ መከናወኑን የአዲሰ አበባ ከተማ የውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን አስታወቀ።
የመስመር ቅየራው በአሮጌ የብረት መስመሮች ምክንያት የሚስተዋለውን የውሃ ጥራትን ለማሻሻል እና ብክነትን ለመከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ዘለቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአዲስ አባባ መንገዶች ባለስልጣን የክረምት መንገድ ቁፋሮ ክልከላ እና በ42 የጥቃቅን ማህበራት ስልጠና ምክንያት ዘግይቶ ተጀምሯል።
በዚህም አሮጌ የብረት የውሃ መስመሮችን የመቀየር ስራ በአሁን ወቅት ከ100 ኪሎ ሜትር ውስጥ 65 ኪሎ ሜትር ተከናውኗል።
ቀሪው 35 ኪሎ ሜትር ዝርጋታ በቀጣይ አንድ ወር ይጠናቀቃል ብለዋል።
እንደ አቶ ፍቃዱ ገለጻም ባለስልጣኑ በቀጣይም በአጠቃላይ 263 ኪሎ ሜትር ቀሪ አሮጌ መስመሮችን በፕላስቲክ የመቀየር ስራ እንደሚያከናውን አመላክተዋል።።
በታሪክ አዱኛ

ረቡዕ 20 ዲሴምበር 2017

ስዋንሲ ሲቲ አሰልጣኝ ፖል ክሌመንትን አሰናበተ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ስዋንሲ ሲቲ አሰልጣኝ ፖል ክሌመንትን አሰናብቷል።
ክለቡ በዘንድሮ የውድድር ዘመን እስካሁን ከተደረጉ 18 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሶስቱን ብቻ ሲሆን ሶስት አቻ ተለያይቷል፤ በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ደግሞ ሽንፈትን አስተናግዷል።
በዚህም 12 ነጥቦችን ብቻ በመያዝ 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የ45 ዓመቱ ተሰናባቹ ፖል ክሌሜንት የስዋንሲ አሰልጣኝ የሆኑት ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ነበር።
ባለፈው የውድድር ዓመት ክለቡን እንደያዙ ከነበረበት የወራጅ ቀጠና አውጥተው 15ኛ ሆኖ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል።
የክለቡ ሊቀመንበር ሁው ጀንኪንስ፥ አሰልጣኙን መቀየር የፈለግነው ክለቡን ከወራጅ ቀጠና ለማውጣት ያለን የመጨረሻ አማራጭ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ስዋንሲ ምክትል አሰልጣኞቹ ኒጌል ጊብስ እና ካርል ሃላቢ ክለቡን መልቀቃቸውን አስታውቋል።
የዌልሱ ክለብ በ24 ሰዓት ውስጥ የአሰልጣኝ ክፍሉን እንደሚተካ ገልጿል።
አሰልጣኝ ክሌመንት ስዋንሲን ከመቀላቀላቸው በፊት በቼልሲ፣ በፓሪስ ሴንት ጀርሜይን እና በሪያል ማድርድ የካርሎ አንቼሎቲ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ሰርተዋል።
በድርቢ ካውንቲ የነበራቸው አጭር የአስልጣኝነት ቆይታ በ2016 በማብቃቱ ተመልሰው በባየር ሙኒክ የአንቼሎቲ ምክትል ለመሆን ተገደዋል።
ከዚያም የስዋንሲ አሰልጣኝ ሆነው የሁለት ዓመት ከግማሽ ውል ቢፈራረሙም አንድ ዓመት እንኳ ሳያገለግሉ ተሰናብተዋል።
ምንጭ፦ቢቢሲ

በእንግሊዝ የካራባኦ (ሊግ) ዋንጫ ማንቼስተር ዩናይትድ ሲሰናበት ቼልሲ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል

 በእንግሊዝ የካራባኦ (የቀድሞ ሊግ) ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሲሰናበት ቼልሲ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል።
ትናንት ምሽት ሁለት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተደርገዋል።
በዚህም ብሪስተል ሲቲን በአሽተን ጌት የገጠመው ማንቼስተር ዩናይትድ 2 ለ 1 ተሸንፎ ከውድድር ተሰናብቷል።
ብሪስተል ወደ ግማሽ ፍፃሜ እንዲያልፍ ያደረጉትን ሁለት ግቦች ኮሬይ ስሚዝ እና ጆ ብሪያን ሲያስቆጥሩ፥ የቀያዮቹን ፋይዳ ቢስ ግብ ደግሞ ዝላታን ኢብራሂሞቪች ከመረብ አዋህዷል።
ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ቦርንማውዝን አስተናግዶ 2 ለ 1 ረቷል።
ሰማያዊዎቹ በዊሊያን ግብ አብዛኛውን የጨዋታውን ክፍለ ጊዜ 1 ለ 0 እየመሩ ጨዋታውን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ተቃርበው ነበር።
ሆኖም በ90ኛው ደቂቃ የቦርንማውዙ ባን ጎስሊንግ አስቆጥሮ ሁለቱ ቡድኖች 1 ለ 1 ሆኑ።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በጭማሪ ሰዓት የአንቶኒዮ ኮንቴው ቡድን አጥቂ አልቫሮ ሞራታ የቼልሲን ድል ያረጋገጠች ግብ በ91ኛው ደቂቃ ከመረብ አዋሃደ።
ይህን ተከትሎም ሙሉ የጨዋታው ክፍለጊዜ በቼልሲ 2 ለ 1 አሸናፊነት በመጠናቀቁ ሰማያዊዎቹ ወደ ግማሸ ፍፃሜ አልፈዋል።
በግማሽ ፍፃሜው በፈረንጆቹ ጥር 9 ቀን 2018 የቻምፒየንሺፑ ቡድን ብሪስተል ሲቲ ከማንቼስተር ሲቲ ቼልሲ ደግሞ ከአርሴናል ጋር ይገናኛሉ።