አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካውያኑ ጥንዶች ከመጠን ባለፈ የሰውነት ውፍረት እና ክብደት ከሚሰቃዩ ሰዎች ሰዎች ውስጥ ይመደቡ ነበር።
ሁለቱ ጥንዶች እንደ አውሮታውያኑ አቆጣጠር በ2015 ነበር የሰውነታቸውን ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ክብደት ለመቀነስ መስራት የጀመሩት።
በወቅቱም ሌክሲ ሌድ የተባለቸው ሚሰት 220 ኪሎ ግራም ስትመዝን ባለቤቷ ዳኒ ሬድ ደግሞ 120 ኪሎ ግራም ይመዝን ነበር።
የሁለቱም ጥንዶች የሰውነት ክብደታቸው አንድ ጤነኛ ሰው ሊኖረው ከሚገባው የሰውነት ክብደት በእጅጉ የራቀ እንደነበረም ይናገራሉ።
አሁን ላይ ግን ጥንዶቹ ጠንክረው በመርሳታቸው በአሁኑ ወቅት ሚስት ሌክሲ ሬድ 82 ኪሎ ግራም እንዲሁም ባለቤቷ ዳኒ ሬድ ደግሞ 86 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ።
በጋራ በመሆን 180 ኪሎ ግራም መቀነስ የቻለሉት ጥንዶቹ በርካታ አድናቆተን እያገኙ መሆኑም ተነግሯል።
ጥንዶቹ እንደተናገሩት ለዚህ ስኬት ያበቃቸው በጋራ በመሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራታቸው እና ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ስርዓትን መከተላቸው ነው።
ያለ ምንም ተጨማሪ መድሃኒት እና ቀዶ ጥገና ህክምና ለዚህ ስኬት መብቃታቸውንም ነው ዳኒ እና ሌክሲ የተናገሩት።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ