ሰውነትን በቢላ ማሳጅ የማድረግ ህክምና ንቁና ጤነኛ እንደሚያደርግ ከወደ ታይዋን ተሰማ ።
ሰዎች ህመም ሲሰማቸው ሰውነታቸውን ዘና ማድረግ ሲፈልጉ የተለያዩ የህክምና አይነቶችን እና የተለያዮ የማሳጅ አይነቶችን ይጠቀማሉ፡፡
በተለይም የሩቅ ምሥራቅ አገራት በሌላው ዓለም ያልተለመዱ የህክምና አይነቶችን በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ የደረቅ መርፊ ህክምናን ማንሳት ይቻላል፡፡
ከወደ ታይዋን የተሰማው የህክምና አይነት አጀብ የሚያሰኝ ነው፡፡ በቢላ ሰውነትን አልያም ፊትን መምታት ህክምና ፍቱን መድሓኒት መሆኑን አስገራሚ ሆኗል ።
ይህ የህክምና አይነት በሰውነት ክፍል ላይ ለሚከሰቱ የህመም አይነቶች ፍቱን መድሓኒት ሲሆን ዘና ማለት ለሚፈልግ ሰውም ልክ እንደ ማሳጅ የሚጠቀሙበት ነው ተብሎለታል፡፡
ያለቅጥ ውፈረት ላስቸገራቸው፣ የነርቭ ችግር ላለባቸው፣ የደም መርጋት ፣ሰኳር፣ የራሰምታት ፣ እንዲሁም ጭንቀት ላሰቸገራቸው ሰዎች ፍቱን መድሓኒት ነው የቢላ ማሳጁ፡፡
ህክምናው ሲሰጥ የታካሚውን ሰውነት እንዲሁም ፊቱን በከፊል በመሽፈን በሁለት ትላልቅ ቢላዎች ሰውነቱን እና ፊቱን በሰለቱ በኩል ብልሀት በተሞላበት ሁኔታ በማሳረፍና መምታት የሚካሄድ ነው፡፡
ይህ ህክምና በማንኛውም ሰው የማይሰጥ ሲሆን ህክምናው የሚካሄድበት ቢላም ቢሆን ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀ እንጅ ለሽንኩርት መክተፊያ የሚያገለግለው አይደለም ።
ህክምናው ከዛሬ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አመት በፊት በቻይና ይሰጥ የነበረ እና በጥንታዊ ቻይናውያን ዘንድ ትልቅ ክብር የሚሰጠው ህክምና ነበር፡፡ ታዲያ ይህ ህክምና ለዘመናት ተዘንግቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን እንደ አዲስ እየተሰራበት ያለ የህክምና አይነት ነው፡፡
ይህንን የቢላ ህክምና ለ13 አመታት በታይዋን ሲሰጡ የነበሩት ባለሞያዎች እንደሚሉት ህክምናው ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ እና ሁሉም ሰው በበቂ ሁኔታ ማግኝት እንዲችል ጥበቡን ለማስተማር ትምህርት ቤት የመክፈት እቅድ እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡
ባለሞያዎቹ አንድ ሰው መቶ ህክምናውን ወሰዶ ከሄደ በኋላ ለበርካታ ሰዎች ሰለሚነግር በርካቶች ወደኛ ዘንድ ይመጣሉ ይህንን ደግሞ እኛ ማሰተናገድ አልቻልንም ለዚህም የህክምናውን ጥበብ አውቀው ሰውን ማገልገል ያለባቸው ሰዎች አሉ ብለን ሰላመንን ነው የህክምና ተቋሙን ለመክፈት ያሰብው ነው ብለዋል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ