
2010 የአውሮፓ ሀብረት በሊቢያ ካምፖች ውስጥ ታጉረው ከሚገኙ ስደተኞች ውስጥ 10 ሺህ ያክሉን ሊቀበል መሆኑን አስታውቋል።
ስደተኞቹ በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት 2018 ወደ በጣሊያን በኩል አውሮፓ ሀገራት እንዲገቡ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፥ ይህም በሊቢያ ካምፖች ውስጥ ኢ ሰብአዊ ድርጊት የሚፈፀምባቸውን ስደተኞች የማዳን ተልእኮ እንዳለው ታውቋል።
የጣሊያን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማርኮ ሚኒቲ እንደተናገሩት፥ ስደተኞች ለህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች እንግልት ሳይጋለጡ እና በባህር ላይ ከሚደርስባቸው አደጋ በፀዳ መልኩ ወደ አውሮፓ የሚገቡበት መንገድ ይከፈታል ብለዋል።
“በአዲሱ የአውሮፓውያኑ 2018 እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሳይጥሉ በሚከፈተው መንገድ ወደ አውሮፓ እንዲገቡ ይደረጋል” ሲሉም ተናግረዋል።
ማርኮ ሚኒቲ አያይዘውም የዓለም መንግስታት ባለስልጣናት እና የሊቢያ መንግስት በአውሮፓውያኑ 2018 ቁጥራቸው እስከ 30 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ከ400 ሺህ እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሸጋገር በሚል ሊቢያ ውስጥ ታጎረው ይገኛሉ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ