ቅዳሜ 1 ኦክቶበር 2016

★የክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ አቪየሮ የህይወት ታሪክ(በአጭሩ)★

ምንጭ፦Tribune sport
✔በፕላኔታችን ኳስን በላቀ ደረጃ ከሚጫወቱ ሁለት
ተጨዋቾች አንዱ ፤እንደ አጥቂም እንደ ክንፍ ተጨዋችም
ቢጫወት ጎል እንዳሻው የሚያገባ፤ኳስ ከፍጥነቱ ከፍጥነቱ
ሳይደናቀፍ የሚያንከባልል ጨራሽ የፍፁም ቅጣት ምት
ስፔሻሊስት፤አንድ ለአንድ ማንኛውንም ተከላካይ
የሚያሸብር .......
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ይህ የዛሬ ኮከብ የሴት ቅድመ አያቱ ኤልዛቤል ዳፒዳድ
በአፍሪካዊቷ ሀገር ኬፕ ቨርዴ የተወለዱ ናቸው፤ከአንድ
ወንድሙ እና ከሁለት እህቶቹ ጋር በአንዲት ክፍል ውስጥ
ኑሮን ለማሸነፍ እንደተጋ የልጅነት ታሪኩ ያስረዳል፤ታዲያ
በአንድ ወቅት ይህንን ህይወታቸውን በእግር ኳስ ብቻ
ለመቀየር ከእናቱ ጋር ይስማማል፤ለዚህም የሀገሩን ክለብ
ስፖርቲንግ ሊዝበን ይቀላቀላል በ15 አመቱ ግን እግር
ኳስን እንዲያቆም የሚያስገድድ የልብ ህመም እንዳለበት
ይታወቃል፤በእናቱ ስምምነት መሰረት ቀዶ ጥገና
ተደርጎለት ወደ እግር ኳስ ይመለሳል
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ስፖርቲንግ ሊዝበን እያለ በ2002 ከአርሰን ቬንገር ጋር
ተገናኝቷል ወደ ሊቨርፑል የመሄድ እድልም ነበር በመሀል
ግን ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና ዩናይትድ ትኩረት ውስጥ
ገባ፤በ2003 ስፖርቲንግ ሊዝበን ማንቼስተር ዩናይትድን
በወዳጅነት ጨዋታ 3ለ1 አሸነፈ፤ያኔ የማንቼስተር
ተጨዋቾች ወሬ ሁሉ ስለ ሮናልዶ ሆነ ወዲያውኑ ይሄ ልጅ
ወደ ማንቼስተር ዩናይትድ እንዲመጣ ሰር አሌክስ
ፈርጉሰንን መወትወት ጀመሩ
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በ2003-04 የውድድር ዘመን በ£12.4m ሮናልዶ
ቀያይ ሰይጣኖቹን ተቀላቀለ ፤እነ ጆርጅ ቤስት፣ብሪያን
ሮብሰን፣ኤሪክ ካንቶና ዴቪድ ቤካም የለበሱትን 7ቁጥር
መለያ ለበሰ፤ባለተሰጥኦ ተጨዋች የማንቼስተርን ውድ
ቁጥር ፈርጉሰን መረጡለት፤የክርስቲያኖ ሮናልዶ ተዐምር
ገና በመጀመሪያው ጨዋታ ከቦልተን ወንደረርስ ጋር
ታየ፤አዲስ የእግር ኳስ ሰው መወለዱ እውን ሆነ፤ከሁለት
የውድድር አመታት በኃላ ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልድ የኦልድ
ትራፎርድ ቁንጮ ተጨዋች ሆነ
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በ2006-07 የውድድር ዘመንማ ከ20 በላይ ጎሎችን
አስቆጠረ ፤በሊጉም በ2008 ከዩናይትድ ጋር ፕሪሚየር
ሊጉን እና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን አነሳ፤በዚህ
የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 42 ጎሎችን
በማስቆጠር ምርጥ ተጨዋችነቱን አስመሰከረ ፤በ2008
በዩናይትድ ባሳየው ምርጥ እንቅስቃሴ የተነሳ ክርስቲያኖ
ሮናልድ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን አገኘ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ያኔ ኮከብ የሚያሳድዱት ማድሪዶች የኦልድ ትራፎርድን
በር ማንኳኳት ጀመሩ፤ሮናልድ ከኦልድ ትራፎርድ ይለቃል
እየተባለም ግን ማን ዩናይትድ በዚህ ጥበበኛ ፖርቹጋላዊ
ጎል አምራችነት ለተከታታይ 3አመታት የፕሪሚየር ሊጉን
አነሳ(ከ2007-09)፡፡በ2009 ዩናይትድ እንደገና
ከባርሴሎና ጋር ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ፤ባርሰሎና
በዚህ ጨዋታ 2ለ0 አሸነፈ፤ያ ጨዋታ ሮናልዶ የዩናይትድን
ማሊያ የለበሰበት የመጨረሻው ትልቅ ጨዋታ ሆነ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ከሳምንታት በኃላ የዝውውር ሪከርድ በጥበበኛው ኮከብ
ተሰበረ ማድሪድ £80m ከፈለ፤ሮናልዶ የልጅነት ህልሜ
ወዳለው ሳንቲያጎ ቤርናቦ ተዘዋወረ፤አዲሱ ተፅዕኖ ፈጣሪ
ታታሪው ጋላክቲኮን ተቀላቀለ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በሳንቲያጎ ቤርናቦ በመጀመሪያው አመት ብቻ በ35
ጨዋታዎች 32ግቦችን አስቆጠረ ፤በ2010-11 የውድድር
ዘመን ደግሞ የላሊጋው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ
የፒቺቺው አሸናፊ ሆነ፤በ34 ጨዋታዎች 40ግቦችን
በማስቆጠር፤ሪያል ማድሪድ ባርሰሎና በኮፓ ዴል ሬይ
በዚህ ዘመን ሲያሸንፍ የማሸነፊያ ጎሏ የክርስቲያኖ ሮናልዶ
ሆነች
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በሪያል ማድሪድ ሮናልዶ መነሳቱን አላቆመም በየጊዜው
የሚጨምር የማይታመን ብቃት የሚያሳይ የጎል ማሽን
ሆነ፤በ2011-12 ላሊጋውን ከማድሪድ ጋር ወሰደ፤በ38
ጨዋታዎች 46 ጎል በማስቆጠር ኮከብ ሆነ በዚህ ወቅት
የፊፋ ባሎንዶርን ሌላ ልዩ ብቃት ባሳየው አርጀንቲናዊው
ሊዮኔል ሜሲ ተነጠቀ እንጂ ሮናልዶ መሸለም ነበረበት
ብለው የሚከራከሩት በርካታ ናቸው
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ከዚህ በኃላም ሁለት ባሎንዶሮችን ሁለት ሻምፒዮንስ
ሊጎችን እና ባሳለፍነው አመት ደግሞ የአውሮፓ ዋንጫን
ከሀገሩ ጋር አሳክቷል ፡፡
★★★★★★★★★

ማክሰኞ 13 ሴፕቴምበር 2016

★የክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ አቪየሮ የህይወት ታሪክ(በአጭሩ)★

ምንጭ፦Tribune sport
✔በፕላኔታችን ኳስን በላቀ ደረጃ ከሚጫወቱ ሁለት
ተጨዋቾች አንዱ ፤እንደ አጥቂም እንደ ክንፍ ተጨዋችም
ቢጫወት ጎል እንዳሻው የሚያገባ፤ኳስ ከፍጥነቱ ከፍጥነቱ
ሳይደናቀፍ የሚያንከባልል ጨራሽ የፍፁም ቅጣት ምት
ስፔሻሊስት፤አንድ ለአንድ ማንኛውንም ተከላካይ
የሚያሸብር .......
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ይህ የዛሬ ኮከብ የሴት ቅድመ አያቱ ኤልዛቤል ዳፒዳድ
በአፍሪካዊቷ ሀገር ኬፕ ቨርዴ የተወለዱ ናቸው፤ከአንድ
ወንድሙ እና ከሁለት እህቶቹ ጋር በአንዲት ክፍል ውስጥ
ኑሮን ለማሸነፍ እንደተጋ የልጅነት ታሪኩ ያስረዳል፤ታዲያ
በአንድ ወቅት ይህንን ህይወታቸውን በእግር ኳስ ብቻ
ለመቀየር ከእናቱ ጋር ይስማማል፤ለዚህም የሀገሩን ክለብ
ስፖርቲንግ ሊዝበን ይቀላቀላል በ15 አመቱ ግን እግር
ኳስን እንዲያቆም የሚያስገድድ የልብ ህመም እንዳለበት
ይታወቃል፤በእናቱ ስምምነት መሰረት ቀዶ ጥገና
ተደርጎለት ወደ እግር ኳስ ይመለሳል
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ስፖርቲንግ ሊዝበን እያለ በ2002 ከአርሰን ቬንገር ጋር
ተገናኝቷል ወደ ሊቨርፑል የመሄድ እድልም ነበር በመሀል
ግን ሰር አሌክስ ፈርጉሰን እና ዩናይትድ ትኩረት ውስጥ
ገባ፤በ2003 ስፖርቲንግ ሊዝበን ማንቼስተር ዩናይትድን
በወዳጅነት ጨዋታ 3ለ1 አሸነፈ፤ያኔ የማንቼስተር
ተጨዋቾች ወሬ ሁሉ ስለ ሮናልዶ ሆነ ወዲያውኑ ይሄ ልጅ
ወደ ማንቼስተር ዩናይትድ እንዲመጣ ሰር አሌክስ
ፈርጉሰንን መወትወት ጀመሩ
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በ2003-04 የውድድር ዘመን በ£12.4m ሮናልዶ
ቀያይ ሰይጣኖቹን ተቀላቀለ ፤እነ ጆርጅ ቤስት፣ብሪያን
ሮብሰን፣ኤሪክ ካንቶና ዴቪድ ቤካም የለበሱትን 7ቁጥር
መለያ ለበሰ፤ባለተሰጥኦ ተጨዋች የማንቼስተርን ውድ
ቁጥር ፈርጉሰን መረጡለት፤የክርስቲያኖ ሮናልዶ ተዐምር
ገና በመጀመሪያው ጨዋታ ከቦልተን ወንደረርስ ጋር
ታየ፤አዲስ የእግር ኳስ ሰው መወለዱ እውን ሆነ፤ከሁለት
የውድድር አመታት በኃላ ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልድ የኦልድ
ትራፎርድ ቁንጮ ተጨዋች ሆነ
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በ2006-07 የውድድር ዘመንማ ከ20 በላይ ጎሎችን
አስቆጠረ ፤በሊጉም በ2008 ከዩናይትድ ጋር ፕሪሚየር
ሊጉን እና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን አነሳ፤በዚህ
የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 42 ጎሎችን
በማስቆጠር ምርጥ ተጨዋችነቱን አስመሰከረ ፤በ2008
በዩናይትድ ባሳየው ምርጥ እንቅስቃሴ የተነሳ ክርስቲያኖ
ሮናልድ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን አገኘ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ያኔ ኮከብ የሚያሳድዱት ማድሪዶች የኦልድ ትራፎርድን
በር ማንኳኳት ጀመሩ፤ሮናልድ ከኦልድ ትራፎርድ ይለቃል
እየተባለም ግን ማን ዩናይትድ በዚህ ጥበበኛ ፖርቹጋላዊ
ጎል አምራችነት ለተከታታይ 3አመታት የፕሪሚየር ሊጉን
አነሳ(ከ2007-09)፡፡በ2009 ዩናይትድ እንደገና
ከባርሴሎና ጋር ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ደረሰ፤ባርሰሎና
በዚህ ጨዋታ 2ለ0 አሸነፈ፤ያ ጨዋታ ሮናልዶ የዩናይትድን
ማሊያ የለበሰበት የመጨረሻው ትልቅ ጨዋታ ሆነ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ከሳምንታት በኃላ የዝውውር ሪከርድ በጥበበኛው ኮከብ
ተሰበረ ማድሪድ £80m ከፈለ፤ሮናልዶ የልጅነት ህልሜ
ወዳለው ሳንቲያጎ ቤርናቦ ተዘዋወረ፤አዲሱ ተፅዕኖ ፈጣሪ
ታታሪው ጋላክቲኮን ተቀላቀለ፡፡
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በሳንቲያጎ ቤርናቦ በመጀመሪያው አመት ብቻ በ35
ጨዋታዎች 32ግቦችን አስቆጠረ ፤በ2010-11 የውድድር
ዘመን ደግሞ የላሊጋው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ
የፒቺቺው አሸናፊ ሆነ፤በ34 ጨዋታዎች 40ግቦችን
በማስቆጠር፤ሪያል ማድሪድ ባርሰሎና በኮፓ ዴል ሬይ
በዚህ ዘመን ሲያሸንፍ የማሸነፊያ ጎሏ የክርስቲያኖ ሮናልዶ
ሆነች
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔በሪያል ማድሪድ ሮናልዶ መነሳቱን አላቆመም በየጊዜው
የሚጨምር የማይታመን ብቃት የሚያሳይ የጎል ማሽን
ሆነ፤በ2011-12 ላሊጋውን ከማድሪድ ጋር ወሰደ፤በ38
ጨዋታዎች 46 ጎል በማስቆጠር ኮከብ ሆነ በዚህ ወቅት
የፊፋ ባሎንዶርን ሌላ ልዩ ብቃት ባሳየው አርጀንቲናዊው
ሊዮኔል ሜሲ ተነጠቀ እንጂ ሮናልዶ መሸለም ነበረበት
ብለው የሚከራከሩት በርካታ ናቸው
★★★★★★★★★★★★★★★★
✔ከዚህ በኃላም ሁለት ባሎንዶሮችን ሁለት ሻምፒዮንስ
ሊጎችን እና ባሳለፍነው አመት ደግሞ የአውሮፓ ዋንጫን
ከሀገሩ ጋር አሳክቷል ፡፡
★★★★★★★★★

ረቡዕ 6 ጁላይ 2016

ትንሽ በጥቂቱ ስለ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ )የማውቀውን

ይህ ሰው ሁሌም በመረጃ አሰባሰብ በዝግጅት አቀራረቡ
እና በሌሎች ነገሮቹ ድንቅ ከሚሉኝ ሰዎች ውስጥ አንድ
ነው።
ሁለገቡ ሰው ገነነ መኩሪያ( ሊብሮ) ።
ሊብሮ የምትለውን ስያሜ ያወጣለት በአብዛኛው
የእግርኳስ አፍቃሪ በአዝናኝነቱ በእግር ኳስ ወዳድነቱ
የሚታወቀው የኳስ ሜዳው ሰው ሀይሌ ካሴ ነው።
በወቅቱ ጊዮርጊስ ከሜታ አቦ በተጫወቱበት ጊዜ ነው
አምስት ተጫዎችን አልፎ ባስቆጠረበት ጊዜ ነበር
የተቀፅላው መነሻ ።
ሊብሮ የተወለደው ይርጋለም ከተማ ቢሆንም እድገቱ ግን
ሻሸመኔ ቀበሌ 09 ነው ።
በልጅነት ወቅትም እግርኳስ ይወድ የነበረው ገነነ
በጊዜው በየ15 ቀኑ አአ የሚመጡት የሆቴላቸው ሾፌር
አብሮቸው ያቀና ነበር በነበራቸው ቆይታም ካምቦሎጆ
ገብተው እግር ኳስ ተመልክተው ይመጡ ነበር በዛ
በአፋላነት ጊዜው መሆኑ ነው።
ሌላው የሚገርመው ገኔ ሻሸመኔ ውስጥ ላለ ቡድን ለ A
ም፣ለB፣ ለC ይጫወት ነበር በአንድ ቀን ውስጥ ።
የቀበሌ 09 ቡድንም በወቅቱ የአቶ ሙኩሪያ ቀበሌ ቡድን
ይባል ነበር ። በጊዜው እሱን ጨምሮ ስድስት ወንድሞቹ
እዛ ቡድኑ ውስጥ ይጫወቱ ነበሩ።እንደዚህ እያለ ነው
ወደ እግር ኳስ ተጫዎችነት ያመራው። ወደ ክለብ
ደረጃም መጀመሪያ የመጣው በ1975 አመተምህረት
አከባቢ በነበረ የትምህርትቤት ውደድሮች ላይ በመታየት
ከነ ታሪኩ መንጀታ፣አስቻለው ጋር በመሆን ነበር ወደ ሜታ
ቢራ የተቀላቀለው።
እዚህ ጋር በወቅቱ በአጨዋወትና በሌሎች ተዛማጅ
ነገሮች ከዛን ጊዜ ጀምሮ ከአሰልጣኞች ጋራ ሙግት
ይገጥም ነበር ።በጊዜው ሜታን ያሰለጥን ከነበረው ስዮም
ጋር ይጋጩ እንደነበር ይጠቀሳል።
በእግር ኳስ ተጫዎችንነት ወቅት እረፍት ሰአቱን በማንበብ
ማሰለፍ ይወድ እንደነበር አብሮት የተጫወቱት
ይመሰክራሉ ።
የሊብሮ ጋዜጣው መነሻ
ከዛ በፊት በበጎ ፍቃደኝነት በተለያዬ የህትመት እና
የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ይሰራ ነበር። ከሰራባቸው
የህትመት ሚዲያ ውስጥም መረሀ ስፖርት፣ የኢትዮጱያ
ራዲዮና ቴሌቪዥን ውስጥ ይጠቀሳል ።
በመቀጠል ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ማለትምአበበ ወልደ
ፃዲቅ ፣ሁሴን አብድልቀኒ ፣ጋር በመሆን ሻምኘዮን
የምትባል የስፖርት ጋዜጣ መስርተው ሰርተዋል።
በማስከተለም የራሱ የሆነችውን ሊብሮ ጋዜጣ አቋቋመ
።በዚህ አጋጣሚ የዚች ጋዜጣ አመሰራረት የሚገርም ነው
በተለይ በወቅቱ የነበሩቱ የቦሌ ማተሚያ ስራ አስኪያጂ
አሰፋ ከበደ ሊመሰገኑበት የሚገባ ድርጊት ነው ።በጊዜው
ገነነ የሚያሳትምበት ገንዘብ እጥረት ያጋጥመዋል ሁሉ
ነገር ጨርሶ ከሰራ በኋላ ነገር ግን እጅን አጣጥፈ ከሰማይ
መና አልጠበቅ ወደ ቦሌ ማተሚያ ቤት ሄዶ ስራ
አስኪያጅን ያለበትን ነገር ሁሉ አስረድቶ ጠይቆ በእሳቸው
ቀና ትብብር አማካኝነት ለህትመት ለመጀመሪያ ጊዜ በቃች
።በጊዜውም በጣም ተወዳጅ ጋዜጣ እንደነበረች በጊዜው
የነበሩ ሰዎች ያስታውሳሉ አብዛኛዋን ትኩረት
የምታደርገው የሀገር ውስጥ ዜናዎች ላይ ነበር ።ለነገሩ
አብዛኛዎ የዛን ዘመን ጋዜጦች ትኩረታቸው የሀገር ውስጥ
እንደነበር መመልከት ይቻላል።
በህትመት ግን ለ13 አመታት ከብዙ ችግሮች ጋር
እየተጋፈጠች ለህዝብ ተደራሽ መሆን ችላ ነበር ።
አብዛኛውን ስራ እራሱ ገነነ ነበር የሚሰራው ።የጋዜጣ ስራ
ምን ያህል አድጋሚና እርዳታ እንደሚያስፈልገው መሆኑ
የሚያውቀው ያውቀዋል።
ነገር ግን ጋዜጣዋ ከተቋረጠች በኋላ ለአጭር ጊዜ በድረ
ገፁ በኩል ጀምሮት ነበር ። ቢሆንም ግን ሊዘልቅ
አልቻለም ።ለሌሎች የምርመራና መፅሀፍ ለመፆሀፍ ፈልጉ
ሁሉ ነገር ገታ አድርጉ በመተው በመፅሀፋና ሌሎች
ተዛማጅ መስኮች ላይ በመስራት በተከታታይ በእግር ኳስ
ዙራያና ፖለቲካ የሚያጠነጥኑ መፅሀፎችን አበረከተለን
ለመጥቀስ ያክል
የአሸናፊ ግርማ የህይወት ታሪክ ከአሸዋ ሜዳ እስከ
አርጀንቲና
የእግር ኳስ ወጎች
ኢሀፖና ስፖርት 1 ና2 (አዚጋ በቅርብ ለእይታ የቀረበው
የነገን አልወልድም የታሪኩ መነሻ ከ ኢሀፖና ስፖርት 1
የተወሰደ ነው)
እና ሌሎች በህትመት ደረጃ ያልወጡ በሙዚቃና በሌሎች
ጉዳዮች ያተኮሩ መፅሀፍች እያሰናዳል ይገኛል ።
ሌላው በ90 ናዎቹ አጋማሽ ላይ በስፋት ይወራ
ስለነበረው የኢትዮጱያዊ ስልጠና ሀሳብ አመንጪ ሰው
ነው በተለምዶ Gk የሚባለውን የስልጠና ፍልስፍና በዋላ
በካሳዬ አራጌ ዳብሮ ለአጭር ጊዜ የተሞከረው
።በነገራችና ላይ በዚህ ዙሪያ ላይ 1994 ላይ ኢትዮጱያ
ስልጠና መፅሀፋ ማውጣቱ አይዘነጋም ።አስከ ጠቅላይ
ሚኒስተር ደረጃ ደብዳቤ ፅፎል በስልጠናው ዙሪያ ላይ ።
በአሁኑ ወቅት ገኔ በስፋት በብስራት fm ላይ እየሰራ
ይገኛል ።በትውስታ፣ በዘመን ተሻጋሪ ና በመሴ ሪዞርት ላይ
ማለት በተለይ የቀድሞ ጊዜ ትውስታዎች ላይ ያተኮሩ
ዝግጅቶቹ የማይጠገቡ መሆኑ ዝግጅቱን ማድመጥ ብቻ
በቂ ናቸው።በቃ ገነነ ማለት የመረጃ ቋት ነው። እዚጋ
ሀይሌ ካሴ ያላትን ነገር ላካፋላቹ። በተለይ በስልጠናው
ዙሪያ "ገነነ እና ካ ሳዬ ማለት ማሽን ናቸው
ልንጠቀምባቸው ይገባል የሌላ ሀገር ዜጉች ቢሆኑ ግን
እንቀበላቸው ነበር" እያለ በቁጭት ነግሩናል ሀይሌ ካሴ
በመጨረሻም እኛ በዚህ ዘመን ያለን የቀድሞን ጊዜ
ያልተመለከትን ሰዎች እንደአንተ አይነቱ ሰዎች ይብዙልን
ታሪኩን እና እድገቱን ለማወቅ ለሚፈልግ ትውልድ አንተ
አንዱ ተጠቃሽ ነክ ላንተ ክብር ይሆን ዘንድ ይህን
ከሰማሁትና ከማውቀው ስለአንተ ፃፍኩ።
*
*
*
እናመሰግናለን የአስቴር አየለ ባለቤት የናኦድና የኤሉም
አባት ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)።
# Dagim Tamiru

ረቡዕ 29 ጁን 2016

በአውሮፓ ዋንጫ 8ቱ ሀገራት ታውቀዋል፤እኛ ደግሞ ቀጣዩቹን ከምርጥም ምርጥ 4 የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ሀሙስ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም
*ፓላንድ 4፡00 ፓርቹጋል
አርብ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም
*ዌልስ 4፡00 ቤልጄም
ቅዳሜ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ.ም
*ጀርመን 4፡00 ጣሊያን
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008 ዓ.ም
*ፈረንሳይ 4፡00 አይስላንድ
source፦ኢትዮ አዲስ ስፖርት

ማክሰኞ 28 ጁን 2016

በ1ኛ እጣ 10 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የቶምቦላ ሎተሪ እጣ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለታላቁ ህዳሴ ግድቡ ግንባታ የሚውለውና በ1ኛ እጣ 10 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የቶምቦላ ሎተሪ እጣ ወጥቷል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ በወጣው እጣ “2913750” 10 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የእጣ ቁጥር ሆኖ ወጥቷል።
5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የሁለተኛ ዕጣ ቁጥር 0497398 ሲሆን፥ 2 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ አሸናፊ ቁጥርም 0207494 ሆኗል።
በተመሳሳይ 1 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የአራተኛ ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 2707403 በመሆን በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ወጥቷል።
በእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረሥላሴ፥ የግድቡ ግንባታ በጠንካራ ህዝባዊ ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀቀጠሉን ተናግረዋል።
ለግድቡ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያነት የተዘጋጀው ሎተሪው ከየካቲት 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ መዋሉና ከሽያጩም ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱም ይታወሳል።

አንድ ለትምህርት ቤቱ አዲስ የሆነ መምህር ክላስ ዉስጥ ገብቶ እራሱን ካስተዋወቀ በኃላ ። . አንድ ተማሪ ጋሸ ስለ ጠቅላላ እዉቀት ጥያቄ አለኝ ብሎ

By
Michael Negese
አንድ ለትምህርት ቤቱ አዲስ የሆነ መምህር ክላስ ዉስጥ ገብቶ እራሱን ካስተዋወቀ
በኃላ ። .
አንድ ተማሪ ጋሸ ስለ ጠቅላላ እዉቀት ጥያቄ አለኝ ብሎ
ተነሳ።።።።።።።።።።።።።
.
ተማሪ፦ ዝሆንን ፍሪጅ ዉስጥ ለማስገባት ብንፈልግ
እንዴት አድርገን እናስገበዋለን?
.
መምህር፦አላወኩም
.
ተማሪ፦ቀላል እኮነዉ ፤ፍሪጁን በመክፈት፥ ሌላም ጥያቄ
አለኝ።
.
መምህር፦እሽ ቀጥል
.
ተማሪ፦አህያንስ ፍሪጅ ዉስጥ ማስገባት ብንፈልግስ
እንዴት አድርገን ነዉ የምናስገባት?
.
መምህር፦ይችማ ቀላል አይደለች፣ ፍሪጅን በመክፈት
.
ተማሪ፦አይደለም ፤መጀመርያ ዝሆኑን ማዉጣት
.
መምህር፦ይገርማል
.
ተማሪ፦አሁንም ጥያቄ አለኝ
.
መምህር፦እሽ
.
ተማሪ፦ሁሉም እንስሳ የነብር ልደት ሁኖ ሂደዋል አንድ
እንስሳ ብቻ ቀረ ማነዉ እሱ?
.
መምህር፦አበሳ ምክንያቱም ሁሉንም እንስሳት
ስለሚበላቸዉ።
.
ተማሪ፦አይደለም፣አህያ ነች ምክንያቱም ከሰሀታት በፊት
ፍሪጅ ዉስጥ ስለነበረች።
..
መምህር፦እየቀለድክ ነዉ?
.
ተማሪ፦አሁን የመጨረሻ ጥያቄ ባህር ተሻግረህ ለማለፍ
ፈራህ ምክንያቱም አዞ አለ
ብለህ ስለምታስብ።እንዴት ብለህ መሻገር ትችላለህ?
.
መምህር፦በጀልባ ነዋ !
.
ተማሪ፦አይደለም ፣እየዋኘህ አዞ ለ ነብር ልደት ስለሄደ ።.

የኢትዮ ጵያ ፕሪሜርሊግ የመዘደጊያ ስነስርዓት በነገው እላት ይካሄዳል።

የኢትዮ ጵያ ፕሪሜርሊግ የመዘጊያ ስነስርዓት በነገው አለት የሚካሄድ  ሲሆን አሸናፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራም ዋንጫ ይረከባል ከዛበፊት የሚደረጉ ጨዋታዎች
ረቡዕ ሰኔ 22 ቀን 2008 ደደቢት ከ ሀድያ ሆሳዕና 8:30 (አ/አ ስታዲየም) ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዋሳ ከነማ 11:30 (አ/አ ስታዲየም)

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የሳምንቱ ምርጥ አባባል

ሰዎች ለዘላለም እንዳይረሱህ ከፈለክ ተበደራቸውና ሙት።

በመፋቀራችን… እግዚአብሔር ቅር አይለውም ፤ አላህ አይከፋውም ፡፡

በመፋቀራችን… እግዚአብሔር ቅር አይለውም ፤ አላህ አይከፋውም ፡፡ (መላኩ አላምረው) ========== ... መግቢያ፦ ከመካ ቀጥለን ከአፍሪካ ቀድመን በክርስቲያን አምባ መስጊዱን አቁመን እስላም ክርስቲያኑ በአንድ ላይ ከትመን በዓላችሁ በዓላችን በዓላችን በዓላችሁ ደስታችሁ ደስታችን ደስያችን ደስታችሁ ሆኖ የጠበቀን ከአበው የወረስነው ኢትዮጵያዊነት ! መለያችን ይህ ነው። .... ሀተታ፦ በእውነት ከሆነ... በእኛ የጥምቀት በዓል የእናንተ መንዙማ በአረፋ በመውሊድ... ያሬዳዊ ዜማ (ለአምልኮ ሳይሆን ለፍቅር ቢሰማ) እግዚአብሔር ቅር አይለውም አላህ አይከፋም ጽድቅ በክፋት እንጅ በፍቅር አይጠፋም። … የጽድቅን አኗኗር - አዛባነው እንጅ እያበዛን ጣጣ በሰው ልጆች ዓለም - ከፍቅር የሚሻል ጽድቅ ከየት ሊመጣ ? ... ‹‹ምንም ጽድቅ ያለ-እምነት ሊታሰብ ባይችልም ያለ-ፍቅርም እምነት ቅዠት ነው ከንቱ ህልም ።›› ... እኛም በእኛ እምነት እናንተም በእናንተ መንግሥቱን ለመውረስ ልባችን ከሻተ እምነታችን "በሩ" ቢሆንም ባይሆንም መንገዳችን ገነት ከቶ አያደርሰንም ፍቅር የሌለንን ፈጣሪ አያውቀንም ። ምክንያቱም... ዘላለም ሚገዛው ዓለማትን ፈጥሮ ፈጣሪ ፍቅር ነው ! ለፍቅር የፈጠረን በፍቅር ቀምሮ ። ... ‹‹ፍቅርን ያለ ፍቅር ለማግኘት ሙከራ ይህ ከንቱ ድካም ነው የሰነፎች ሥራ ።›› ... በእኛ መጽሐፍ ቅዱስ... ‹‹ሁሉም ነገር ባንተ በፍቅር ይሆን ዘንድ አይደለም ወዳጅህን ጠላትህ ውደድ›› የሚል ትዕዛዝ አለ... ትርጉሙም ምሥጢሩም "ፍቅርን" ያከለ የፍቅርን አስገኝ "እ ር ሱ ን" የመሰለ ። በእናንተ ቁርዓንም... ‹‹እንኳንስ ለሰው ልጅ ለፍጥረቱ ሁሉ ራርታችሁ ኑሩ እደሩ እንደ ቃሉ›› ተብሎ የተጻፈ የፍቅር ቃል አለ ክርስቶሳዊውን የእኛን የመሰለ ። ... መደምደሚያ፦ ፍቅር ከሆነ አምላክ ለሰው የተሰጠ ምንም ትዕዛዝ የለም ከፍቅር የበለጠ ... እኛ ስንዋደድ ዓይኑ ደም ሚለብስ ልባችን ሲፋቀር እግሩ የሚያነክስ ሰይጣናዊ ፍጡር ከሰው ልጅ ባይጠፋም በመፋቀራችን - እግዚአብሔር ቅር አይለውም - አላህ አይከፋም፤ ጽድቅ በክፋት እንጅ በፍቅር አይጠፋም ። ……… (©መለኛ ሐሳቦች)

መልካም ልደት ለአባባ ተስፋዬ

"ደህና ናችሁ ልጆች? የዛሬ ኣበባዎች የነገ ፍሬዎች
እንደምን ኣላችሁ ልጆች? ኣያችሁ ልጆች የኢትዮጲያ
ቴሌቭዥን የልጆች ግዜ ዝግጅት ክፍል እናንተን
ለማስደሰት ልክ በሰአቱ ይገኛል፥ እናንተስ ዝግጁ ናችሁ?
ኣዎዎ ኣባባ ሸንተረሩን ኣቋርጠው ዳገቱን ወጥተው
ቁልቁለቱን ወርደው በጓሮ በኩል ዲ ዲ ዲ ከተፍ ሲሉ
እናንተ ደሞ ቆማችኋል ኣይደል? በጣም ጥሩ ነው ልጆች፥
ኣንድ ኣባት ሲመጣ ብድግ ብሎ በኣክብሮት መቀበል
ኣስፈላጊ መሆኑን ሁልጊዜ እነግራችሁ የለም? ኣዎዎ በቃ
አሁን ተቀመጡ እንዳትጋፉ ታዲያ ትንንሾች ወደፊት
ትልልቆች ወደኋላ ኣዎዎ"
ሰኔ 20/1916 ዓ.ም በቀድሞዋ ባሌ ክፍለ ሃገር ከዶ
የተሰኘ አካባቢ ኣንድ ጀግና ፈለቀባት፥ ብላቴናው 14
ዓመት ሲሞላው ወደ ሸገር መጣ ከዚያም በኮከበ ፅባህ
ኣስኳላ ትምህርቱን መከታተል ጀመረ።
በኣንድ ወቅት የኣዲስ ኣበባ መስተዳደር ባህል እና ቲያትር
ኣዳራሽ ማስታወቂያ ሲወጣ በተዋናይነት ተመዝግቦ
ተቀጠረ፥ በወቅቱ ሴት ልጅ ወደ ማጀት እንጂ ኣደባባይ
ላይ መዋል ነውር ነበርና ለትወና የምትመጣ ሴት
ኣልነበረችም እናም ይህ ሰው የሴቶችንም ገጸባህሪ
ወክሎ በብቃት ይጫወት ጀመር። እንዲያውም ኣንድ
ወቅት ላይ ኣንድ ትያትር ሊያይ የገባ ሰው "ይህቺን ሴት
ወድጃለሁ" ብሎ ኣምባጓሮ እስኪፈጠር መስሎ ሳይሆን
ሆኖ የሚተውን እሳት ተዋናይ ነበር፥ ለዚህም
- ‘ሀ ሁ በስድስት ወር’
- ‘ኤዲፐስ ንጉስ’
- ‘አሉላ አባነጋ’
- ‘ዳዊትና ኦርዮን’
- ‘ኦቴሎ’
- ‘አስቀያሚዋ ልጃገረድ’
- ‘ስነ ስቅለት’
የተሰኙ እሱ የተጫወተባቸው ተውኔቶች ዉስጥ የሚጠቀሱ
ናቸው፥ ይህ ሰው ወደ ድርሰቱ ኣለም ገብቶም
- ‘ብጥልህሳ’
- ’ ነው ለካ’
- ‘ጠላ ሻጯ’
የተሰኙ ተውኔቶች ኣበርክቶ ግዙፍ ኣሻራውን ያሳረፈ ሲሆን
በተጨማሪም አራት የተረት መጻሕፍት ለልጆች ኣድርሷል።
በ1957 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲቋቋም ደግሞ
"የልጆች ግዜ" የተሰኝ ፕሮግራም እንዲኖር ሃሳቡን አቅርቦ
ሲፀድቅለት እስካሁንም ማንም ሊተካው ባልቻለና የእርሱ
ብቻ በሆነ የአቀራረብ መንገድ በመጠቀም ለመላው
የኢትዮጲያ ህዝብ ለ42 ዓመታት ያህል በኣባትነት ስሜት
ኣቅርቧል።
ለልጆች ብቻ ሳይሆን ለኣዋቂም የሚሆኑ ወዝ ያላቸው
ቁምነገር ኣዘል ተረቶችን፣ ጨዋታዎችን እና ኣስተማሪ
ዝግጅቶችን እያደረሰ መልካም ማንነትን የተላበሰ ትውልድ
ለመገንባት መተኪያ የሌለው ኣስተዋፅዖ እና ድርሻ
ኣበርክቶልናል።
ኣባባ ተስፋዬ እንኳን ለ93ኛ ዓመት የልደት በዓልዎ
ኣደረሰን፥ ውለታዎ ብዙ ነው ትውልዶች ሁሉ ሲያከብርዎት
ይኖራሉ እርስዎ በተለያየ ዘመን ውስጥ፥ በኣስቸጋሪውም
በጥሩውም የሀገር ሁናቴ በሚልየን ለሚቆጠሩ የኢትዮጲያ
ልጆች ስለ ሐገራቸው እንዲታስቡ መምህር የሆኑ
የትውልድ ኣባት ነዎትና እናከብርዎታለን፡፡ እንደ ትላንቱ
ሁሉ ሁሌም እርስዎን ስናስብ ከመቀመጫችን ብድግ
ብለን ልናከብርዎት የውዴታ ግዴታችን ነው። ከዛሬ ጀምሮ
የሚታሰብ ከእኔ እድሜ ተቆርጦ ለእርስዎ ለኣባቴ ቢሰጥ
እወዳለሁ
ልጅዎ

ምንጭ: Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

ዓርብ 3 ጁን 2016

#The Stone Roses could be poised to play

two secret gigs in Manchester, the M.E.N.
can reveal.
The band's management have refused to
confirm or deny reports that the band are
gearing up for a short run of hush-hush
gigs in an undisclosed city venue for a
small gathering of fans.
According to a Facebook post published
today, one person claims to have seen the
tickets, along with details of the gigs and
believes that tickets are to be released at
10am on Saturday (June 4).
The poster suggests Ian Brown and co will
play at a venue in Greater Manchester,
possibly somewhere between Manchester
and Oldham, as a warm up to their sold-
out stadium shows at the Etihad later this
month

ዳጉ፤ አስደናቂው የአፋሮች የመረጃ ልውውጥ እሴት፤=====================================

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ
ፍለጋው ወደ አፋር እየወሰደን ነው፡፡ የአፋርን አስደናቂ
መስህቦች ከመጎብኘታችን በፊት ስለ ዳጉ ማወቅ አለብን
ይላል፡፡ ዳጉ ካለን አፋርን እንዲህ እንጎበኘዋለን፡፡)
(ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ)
የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ፍለጋችንን ከዚህ በላይ
አንገፋበትም፡፡ ወደ አፋር ምድር ጉዞአችንን ቀጥለናል፡፡
ሱልጣኑ እንደአሉት እንኳን አፋሮች ግመሎቻቸው
የአንድነታችን መገለጫዋን ባንዲራችንን ያውቋታል፡፡
ወደዚህ ምድር እየሄድን ነው፡፡
አምስት ዞን 31 ወረዳና አንድ ልዩ ወረዳ የፈጠሩት
የአፋር ክልል 96,256 ስኩዬር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋትን
ይሸፍናል፡፡ በታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ
ውስጥ ያረፈው አፋር ምድር ከባህር ጠለል በታች እስከ
116 ሜትር የሰረጎዱ ሸለቆዎች የሚገኙበት ሲሆን ሙሳ
አሊ ከባህር ጠለል በላይ 2063 ሜትር የሚዘረዝመው
አፋር ትልቁ ተራራ ነው፡፡
አዋሽ ከተማ ቆመናል፡፡ አዋሽ ሰባት ኪሎ በሚለው
መጠሪያዋ ትታወቃለች፡፡ ከኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መቆም
ጋር ተያይዞ ደማቋ ከተማ ለዓመታት ፈዝዛ ኖራለች፡፡
አሁን አዋሽ ባቡሩ ጀመረ እንዴ የምታስብል ከተማ
እየሆነች ነው፡፡
መንገድ አንጀምርም፤ ከዚያ በፊት ዳጉ ያስፈልጋል፡፡ ዳጉ
የአፋሮች ቁልፍ እሴት ነው፡፡ አፋር ከዘመን ቀድሞ
የመረጃን ፋይዳ የተገነዘበ ህዝብ ነው፡፡ መረጃን በፍጥነት
የሚለዋወጡበት እሴት ዳጉ ይባላል፡፡ ያለ ዳጉ ህይወት
የለም፡፡ የአፋሮች ዳጉ ፈጣንና እውነተኛ ነው፡፡ ተአማኒነቱ
የተለየ መገለጫው ሲሆን በፍጥነትም ወደር የለውም፡፡
ቡሬሙዳይቱ የተከሰተው ሳይረፍድ ኤሊዳር ይሰማል፡፡
ማንዳ የተከወነው ሳይዘገይ አፍዴራ ይገባል፡፡ ሙሳ አሊ
የተወራው አዘሎ ሲደርስ ደከመኝ ብሎ መንገድ ሳያድር
ነው፡፡ ከበርሐሌ ዱብቲ፣ ከአሳኢታ ሚሌ ዳጉ ፈጥኖ
የሚደርስ የመረጃ መለዋወጫ ስልት ነው፡፡ ፍጥነቱ
የደወሉላቸው ደንበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ
ናቸው ከሚለው የስልካችን አገልግሎትም የሚፈጥንበት
ጊዜ አለ፡፡
የአፋሮች እንቅስቃሴ በዳጉ የተደገፈ ነው፡፡
ስለሚደርሱበት አካባቢ በቂ መረጃ በየደረሱበት
ይሰማሉ፡፡ ስለአለፉባቸው አካባቢዎች ደግሞ
ለደረሱባቸው ስፍራዎች አስተማማኝ መረጃ ይሰጣሉ፡፡
ይሄ ከማህበራዊ ትስስራቸው ባሻገር የኢትዮጵያን ድንበር
ሳትደፈር ተከብራ እንድትኖር በጽናት እንዲጠብቁ
ያስቻላቸውን ብቃት የፈጠረ እሴት ነው፡፡
አዋሽ ሰባት ቆመን ዳጉ እንሰበስባለን፡፡ ከዚያ ጉዞው
ይቀጥላል፡፡ የአዋሽ አርባን ሙቀት እንጋራዋለን፡፡ በመተካ
ፍል ውሐዎች እንጠበላለን፡፡ የአፋር ምድር አማካይ
የሙቀት መጠን ዝቅ ሲል 18 ከፍ ሲል 45 ዲግሪ
ሴንቲግሬድ ይደርሳል፡፡ እንደ ምድሩ እንለብሳለን፡፡
ጉዞአችን ወደ አፋሮች ምድር ነው፡፡

ዓርብ 27 ሜይ 2016

1.ይስጥሽ

---------*
እቴ
ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን ረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
.
.
... እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።
.
.
እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሽውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን
.
---//------
.
.
2. ክልክል ነው!!!
------------*
ማጨስ ክልክል ነው
ማፏጨት ክልክል ነው
መሽናት ክልክል ነው
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው"፤
የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡
-----//-------
.
.
3. አንሺና ጣይ
-------------*
ደመወዙን ቢጥል
አንስተው ጠጡበት
ባርኔጣውን ቢጥል
ወስደው ደመቁበት
ከዘራውን ቢጥል
ተመረኮዙበት
በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ
በጣለው ሲያጌጡ
በጣለው ሲያተርፉ
ራሱን ሲጥል ግን
አይተውት አለፉ
-----//----
.
.
4. ኢትዮጵያዊ ነኝ!
-------------------*
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደ አክሱም ግንብ እንደቦሃ አለት
የመከራ አለት ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
ከዋርካ ባጥር ከንቧይ ተልቄ
ከፀሃይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ከምድረ በዳ ውሃ አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በፍኝ ጠልቄ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
ልክ እንደ ቻይናው የትም ሳልረባ
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ
በመጠን ኖሬ አፈር ምገባ
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
ግትር ጠላቴን ባጭር አንካሴ
እራስ ምታቴን በዳማከሴ ነቅዬ ምጥል
አገር በነገር የማብጠለጥል
ነገር በነገር የማብጠረጥር
ኢትዮዺያዊ ነኝ
.
.
እንደ ማህረብ ቤቴን በኪሴ
እንደ ንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤው የምዞር ከቦታ ቦታ
በሰበብ ኬላ የማልረታ
ኢ..ት..ዮ..ጵ..ያ..ዊ.... ነኝ!
----//-------
© በዕውቀቱ ስዩም

ረቡዕ 11 ሜይ 2016

ዛሬ 03/09/08 በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ

ዛሬ 03/09/08 በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በቀበሌ 16 በሚገኝው በልማድ ፖሊስ ካምፕ በሚባለው ቦታ ለከተማችን ሁለተኛው ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ሙሉ በሙሉ ወጪው በዳሽን ቢራ አ.ማ የሚገነባው ሜዳ የመሰረት ድንጋይ በከንቲባችን በአቶ ተቀባ በዳሽን ቢራ አ.ማ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ መክብብ እንዲሁም የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች እንግሊዛዊው ማርቲን ሬይሞንድ ኬውን በተገኙበት የተቀመጠ ሲሆን በጎንደር መስቀል አደባባይ በተካሄደው ፐሮገራም ለአገሪቱ እግር ኳስ እድገት መሠረት የሆኑትን የታዳጊ የእግር ኳስ ተጫዋቾችንና አሰልጣኞችን ማበረታታት የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ ሲሆን ማሪቲን ኬውን በቆይታው በአዲስ አበባና በጎንደር የልማት ስራዎችን ይጎበኛል።ከዳሽን ቢራና ከፋሲል ከነማ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ተዋወቃል።
ከፕሮጀክት እግር ኳስ ተጫዋቾች ጋር ጨዋታ ያደረገ ሲሆን ፣ ኳሶችንና ፒፕስ በስጦታ የበረከተ ሲሆን ከሰአት ደግሞ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ለመጎብኝት ሂድዋል ኬውን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከሚሰለጥኑ ታዳጊ ወጣቶች ጋርም የእግር ኳስ ጨዋታ ያደርጋል።
እንዲሁም ከአሰልጣኞችና ከሌሎች የስፖርት ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ ያካሂዳል።
የአርባ ዘጠኝ ዓመቱ ማርቲን ኬውን በአርሰናል፣ በሬዲንግ፣ በኤቨርተን እና በአስቶን ቪላ ክለቦች ተጫውቷል።ተጫዋቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚጣው የእንግሊዙ የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ከዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር በእግር ኳስ ላይ በጋራ ለመስራት ባደረጉት ስምምነት መሠረት ነው። እንዲሁም ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ቤት ለተቃጠለባችወ ለችግረኞች ዳሽን ቢራ አ.ማ የ 600000 ብር ድጋፍ ለከንቲባው አበርክተዋል ፡፡ አንተነህ መሀሪ የዳሽን ቢራ ስፖርት ክለብ ህዝብ ግንኙነት

«ልብ ብለው ያንብቡ»

Enku TV

የዚህን ቻይናዊ ታሪክ ስሰማ ሁሌም እንደ አዲስ እደነቃለሁ።
ጃክ ማ (Jack Ma) ይባላል።
☞ለሶስት ጊዜ ያክል ኮሌጅ ውስጥ ውጤት አልመጣለትም
☞30 ግዜ ለስራ አመልክቶ አልተሳካልለትም
☞KFC ቻይና ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍት ከእሱ ጋር 24 ሰዎች ለስራ ተወዳድረው እሱ ብቻ እድሉን አጣ
☞ለፖሊስነት አመልክቶ እሱ ብቻ ተቀባይነት አጣ
☞አሜሪካ ለሚገኘው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ለመቀጠል ጠይቆ he was rejected በህይወቱ ውስጥ በጣም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዶዋል ግን ተስፋ ቆርጦ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም።
በ1994 ስለ ኢንተርኔት ሰማ። በ1995 ከትውልድ አገሩ ቻይና ወደ አሜሪካ ባጋጣሚ ያቀናል በዚህም ጊዜ በጓደኛው እርዳታ ስለ ኢንተርኔ ምንነት ማወቅ ቻለ።
ኢንተርኔትን እንዳወቀ መጀመርያ የፈለገው ቃል "beer" የሚል ነበር። በዚህም ስለ ቢራ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ አገሮች ያገኝ ቢሆንም ከአገሩ ቻይና ግን ምንም አይነት መረጃ ማግኝት አልቻለም።
በዚህም ተበሳጨና ስለ ቻይና አጠቃላይ መረጃ መፈለግ ተያያዘ አሁንም ውጤቱ 0 ነበር። በዚህም ቁጭት ከጓደኛው ጋር ሆኖ ሰለ ቻይና መረጃ የሚሰጥ ድህረ ገጽ ፈጠሩ፡፡
ድህረ ገጽ በተከፈተ በአምስት ሰዓት ውስጥ ከተለያዩ ቻይናዊያን የአብረን እንስራና እንተዋወቅ ጥያቄዎች ቀረቡለት።
በዚህም ኢንተርኔት አዋጭ ስራ እንደ ሆነ ተገነዘበ፡፡ እንደዚህ እያለ የአለማችንን ግዙፍ የe-commerce ተቋም የሆነውን ALIBABA GROUP ለማቋቋም በቃ፡፡
አሁን የ 23.6 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ተቀማጭ አለው። ማክ የአለማችን ቱጃር ከሚባሉት ባለሃብቶች ተርታ ስሙን አስመዝግቧል።
ወዳጄ በማንኛውም ሁኔታ በምንም ምክንያት ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ሌላ ብሩህ እና መልካም ቀን ነው። ወዳጄ አንድ ነገር ላይ ችክ አትበል አማራጮችን ተጠቀም አመራጮችን ተመልከት አማራጮችን ፍጠር፡፡ አንድ ነገር ፈልገኸው ወዳንተ ብቻ እስኪመጣ አትጠብቅ አንተም በምትችለው አቅም ተጠጋው፡፡ ምክር አይደለም ወዳጄ የምታውቀውን ነገር ላስታውስህ ብዬ ነው።
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»

ሰኞ 9 ሜይ 2016

ሕይወት- ሌስተርና ቼልሲ በዳንኤል ክብረት

ይገርምሃል ወንድሜ በሕይወትህ ድል አድርገህ ዋንጫ ወሰድክ ማለት እዚያው የልዕልና ማማ ላይ እንደተሰቀልክ ትቀራለህ ማለት አይደለም፡፡ አታየውም ቸልሲን መከራውን ሲቀበል፡፡ አምና እርሱ ዋንጫ ሲበላ ያየ ሰው ዘንድሮ መከራውን ይበላል ብሎ ማን ገመተ? ብዙዎችኮ ሲወጡ መውረድን ይረሱታል፡፡ ለሚወጣ ሰው ግን መውረድ የጥላውን ያህል ቅርብ ነው፡፡ ‹እኖራለሁ ብለህ ሥራ እሞታለሁ ብለህ ኑር› ሲባል አልሰማህም? መውረድን የረሳ ባለ ሥልጣን፣ ሕመምን የረሳ ጤነኛ፣ ድህነትን የረሳ ሀብታም፣ ሞትን የረሳ ነዋሪ፣ ድቀትን የረሳ ጻድቅ፣ ውርደትን የረሳ ክቡር፣ ወደረሳው ነገር ለመጓዝ እንዴት ይፈጥናል መሰለህ? ድቅድቁ ጨለማ ያለው ከሻማው ሥር ነው፡፡

እነ እገሌ ካሉ፣ እነ እገሌ ቦታውን ከያዙ፣ እነ እገሌ እዚያ ላይ ከወጡ፣ በቃ አይሳካልኝም አትበል፡፡ ሌስተርን ያየ እንዲህ አይልም፡፡ ለወትሮው የእንግሊዝ እግር ኳስ ማንቸስተር ዮናይትድና ማንቸስተር ሲቲ፣ አርሴናልና ቼልሲ በእግራቸው ርግጥ፣ በእጃቸው ጭብጥ አድርገው የሚዘውሩት ይመስል ነበር፡፡ መቼም ዋንጫውን ከእነዚህ ከአራቱ አንዱ እንጂ ሌላው ይቀምሰዋል ተብሎ አይታሰብም ነበር፡፡ ‹ሙሴ በሩቁ ከነዓንን አያት እንጂ አልወረሳትም› እንደሚባለው ሌሎቹ ቡድኖች ዋንጫውን በሩቁ ከማየት አልፈው ይወርሱታል ብሎ ማን ያስብ ነበር፡፡ 

ወዳጄ በዚህ ዓለም ላይ የማይነጠቅ የተጨበጠ፣ የማይንሸራተት የተረገጠ የለም፡፡ nothing for granted ይሉ የለም ስታድየሙን ሞልተው የሚጨፍሩት እንግሊዞች፡፡ የጨበጥክበት እጅህ፣ የረገጥክበት እግርህ አንድ ቀን ይዝላል፡፡ የትናንት አይበገሬነትህ፣ የትናንት ጀግንነትህ፣ የትናንት ክብርህ፣ የትናንት አሸናፊነትህ፣ የትናንት ተፈሪነትህ በዛሬ ጥረት ካልታገዘ ታሪክና ቅርስ እንጂ ድልና ውጤት አይኖርህም፡፡ አታያቸውም እንዴ እነ ማንቸስተር ዩናይትድና እነ ማንቸስተር ሲቲ ከአራቱ ውስጥ ለመግባት መከራቸው ሲያዩ? አታያቸውም እንዴ እነ አርሴናል ከቀበሮ አምልጦ ዛፍ ላይ እንደወጣ ዶሮ ካሁን አሁን ከአራቱ ወረድን እያሉ ሲጨነቁ? አላየኸውም እንዴ ስንት ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የኖረው አስቶንቪላ ተሰናብቶ ከሊጉ ሲወርድ፡፡

ዓለም እንደዚህ ናት፡፡ ድል በታሪክ ቢሆን ኖሮ ከሊቨርፑል በላይ ማን ዋንጫ ይወስድ ነበር፡፡ ምን እዚያ ወሰደህ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ዋንጫ የጠነሰስን፣ የአፍሪካን እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንስ የመሠረትን አልነበርንምን? ከብዙዎቹ ቀድመን ኳስ ተጫውተን፣ ከብዙዎቹ ቀድመን ዋንጫ አልበላንምን? ከብዙዎቹስ በፊት የአፍሪካን የእግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አልመራንምን? ዛሬ ግን የት ነን? ትዝታ ሆነናል፡፡ ዋንጫ እንደ መንግሥተ ሰማያት፣ ድልም እንደ ሰማይ ርቆናል፡፡

ሊቃውንቱ ‹ድል ማለት ጥረትና ዕድል የሚገናኙባት አጋጣሚ ናት› ይላሉ፡፡ አንተ ትታገላለህ፣ ትጥራለህ፣ ትለፋለህ፣ ትደክማለህ፣ ትወጣለህ፣ ትወርዳለህ፤ እንዲህ ባለማቋረጥ ስትታገል አንድ ቀን የአንተ የጥረትህ መንገድ ከዕድል መንገድ ጋር ይገናኝና ታቋርጠዋለህ፡፡ ያኔ አይወድቅም የተባለው ወድቆ፣ አይሸነፍም የተባለው ተሸንፎ፣ አይነቀነቅም የተባለው ተነቅንቆ፣ አይፈርስም የተባለው ፈርሶ፣ አይነካም የተባለው ተነክቶ ቦታውን ሲለቅ ታየዋለህ፡፡

አንተ ካልጣርክና ካልታገልክ፣ ካልሠራህና ካልሞከርክ ግን በዕድል ብቻ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ዛሬ አላሸነፍክም? ተስፋ አትቁረጥ ቢያንስ የማሸነፍ ሞራልና የማሸነፍ ተስፋ አለህና፡፡ የሚሸነፍ ትግል የለም፡፡ የሚሸነፍ ሰው እንጂ፡፡ ትግል ትግልን ይወልዳል፣ ጥረት ጥረትን ይተካል፣ ሙከራ ሙከራን ያመጣል፡፡ ዛሬ አንድ አካፋ አፈር ከተራራው ላይ ስታነሣ ተራራውን አልናድከው ይሆናል፡፡ በርግጠኝነት ግን የተራራውን መልክ ቀይረህዋል፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች፣ ወይም አንተ ራስህ እንኳን የተራራው መልክ መቀየሩን ላታውቀው ትችላለህ፡፡ ተራራው ራሱ ግን ያውቀዋል፡፡ የመሬት መሸርሸር የሚባለው ግማሽ ተራራ ተሸርሽሮ አይደለምኮ፡፡ ውኃ እያሳሳቀ አፈሩን በየጊዜው ሲወስደው ነው፡፡  

ምናልባትም ምንም አታመጣም ብለው ሰዎች ይነግሩህ ይሆናል፡፡ ሌስተርን ተመልከቱ በላቸው፡፡ ሌስተር የት ነበረ፡፡ አምና ቼልሲ ዋንጫውን ሲወስድ፣ ማንቸስተር ሲቲ ሁለተኛ ሆኖ ሲጨርስ አርሴናልና ማንቸስተር ዩናይትድ ሦስትና አራተኛ ሆነው ሲያጠናቅቁ፣ ሌስተር የት ነበር? እስከ ሰባት፣ እስከ ዐሥር  ደረጃ ብትፈልገው ታገኘዋለህን? ፈጽሞ፡፡ ሌስተር ከወራጅ ቀጠናው በአራት ደረጃ ርቆ፣ ከወራጁ ከሁልሲቲ በ7 ነጥብ ብቻ በልጦ 14ኛ ደረጃ ላይ ነበረልህ፡፡  

ዘመን መሰላል ነው፡፡ የወጣው ሲወርድ፣ የወረደው ሲወጣ ይገናኙበታል፡፡ በአንድ ዓመት ልዩነት የቸልሲን ቦታ ሌስተር፣ የሌስተርንም ቦታ ቼልሲ ይዞ አየነው፡፡ እንዳያርግ ስንፈራው የነበረው ቼልሲ እንዳይወርድ ተሳቀቅንለት፡፡ ‹የናቁት ይውርሳል› እንደተባለው አራቱን ኃያላን ገፍቶ ሌስተር መጣና እንደ ሽሮ ቅቤ በአናት ተቀመጠ፡፡ ‹ይሞታል ያሉት ተርፎ፣ ይቀብራል ያሉት ሞተ› ሲባል አልሰማህም?

እናም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ግፋ፣ ጣር፣ ታገል፣ ሥራ፣ ሞክር፣ ድፈር፤ ድል ይጠራቀማል፡፡ አንድ ቀን ከላይ ያየሃቸው ኃያላን እንደ ቼልሲ ደክመው፣ እንደ አርሴናል አርጅተው፣ እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀልብ ርቋቸው፣ እንደ ሲቲ ነገር ዓለሙ ዞሮባቸው ታገኛቸዋለህ፡፡ ያኔ እንደሌስተር ገፋ ገፋ አድርገህ ከላይ ቁጢጥ ነው፡፡ ሰውን መናቅ እንጂ በሰው መናቅ አይጎዳም፡፡ ሰውን መናቅ ትዕቢትን ወልዶ ስንፍናን ያመጣል፡፡ በሰው መናቅ ግን እልህን ወልዶ ትግልን ይፈጥራል፡፡ እናም አሸናፊነትህ የሚወሰነው ሰዎች ባንተ ላይ ባላቸው አመለካከት አይደለም፤ አንተ በሌሎች ላይ ባለህ አመለካከት እንጂ፡፡ እንዴት ያዩኛል? ብለህ አትጨነቅ፡፡ እንዴት አያቸዋለሁ? ብለህ ግን አስብ፡፡ እያሸነፍክ ስትመጣ የማያዩህ ሁሉ ያኔ ያዩሃል፣ የጠሉህ ያኔ ይወዱሃል፣ የናቁህ ያኔ ያደንቁሃል፡፡ የበለጠ ወደ ማይክራፎኑ በተጠጋህ ቁጥር የበለጠ ድምጽህ ይሰማል፡፡

እንዲያውም ሲንቁህ መልካም ነው፡፡ ጫና አይበዛብህም፤ ጠላት አይበዛብህም፤ ተገዳዳሪ አይበዛብህም፤ ጉልበትህን ለሥራህና ለዓላማህ ብቻ እንድታውለው ጊዜ ታገኛለህ፡፡ ሰዎች ዓይናቸውን ቼልሲ ላይ ያርጉልህ፣ ማንቸስተር ላይ ይጣሉልህ፣ ሲቲ ላይ ያኑሩልህ፣ አርሴናል ላይ ያትኩሩልህ፡፡ አንተ ዝም ብለህ ሥራና እንደ ሌስተር እየገፋህ ና፡፡ መንደርህ ትንሽ ናት? ስምህን የሚያውቀው የለም? ገንዘብህ ጥቂት ነው? የተሰጠህ ግምት አነስተኛ ነው? ባንተ የሚተማመኑ የሉም ወይም ጥቂት ናቸው? እነዚህ ሁሉ ካልለወጡህ ልትለውጣቸው ትችላለህ፡፡

እንደ ንሥር ታድሰህ፣ እንደ እባብ አፈር ልሰህ፣ እንደ ከራድዮን ራስህን ለውጠህ እስካልመጣህ ድረስ እንደ ቼልሲ ትናንት ዋንጫ በልተህ ዛሬ መውረድህ የማይቀር ነው፡፡ ወደላይ ከሚሄድ ሰው ይልቅ እላይ ያለ ሰው ለታቹ ቅርብ ነው፡፡ ጊዜ ይለወጣል፣ ሐሳብ ይለወጣል፣ ወዳጅ ይለወጣል፣ አሠራር ይለወጣል፣ እሴቶች ይለወጣሉ፡፡ አንተም ትናንት የሠራኸውን ብቻ እየዘፈንክ፣ የትናንቱንም ታሪክ ብቻ እየተረክህ፣ ‹ትናንት እንዲህ ያደረግኩት እኔ ነኝ› ብለህ እየፎከርክ መኖር አደገኛው አኗኗር ነው፡፡ ‹ሆ› ብለው ያወጡህ ‹ውይ› ብለው እንዳያወርዱህ፣ ‹ጀግና› ብለው የሰቀሉህ፣ ‹ፈሪ› ብለው እንዳይጥሉህ፤ ‹ጉሮ ወሸባዬ› የዘፈኑልህ፣ ‹ዋይ ዋይ የት ትሄዳለህ› እንዳይሉህ፣ ‹ያለ አንተ› ያሉህ ‹ካንተ በቀር› እንዳይሉህ፡፡ የኮሩብህ እንዳያፍሩብህ፣ ‹እዩኝ እዩኝ› ብለህ ‹ደብቁኝ ደብቁኝ› እንዳትል ከፈለግክ መንገዱ አንድ ብቻ ነው፡፡ የትናንቱን ለታሪክ ተወውና ለዛሬው የሚያስፈልግህንና የሚገባህን ሥራ ሥራ፡፡ ከታሪክ ተማር እንጂ ታሪክ ላይ አትተኛ፡፡

አታይም እዚህ ሀገር እንኳን የሊቨርፑል ዘመን አልፏል፡፡ ዛሬ በሃምሳዎቹና በስድሳዎቹ ውስጥ ያሉ የኳስ አፍቃሪዎች በዘመናቸው የሊቨርፑል ደጋፊዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የእነርሱ ልጆች እንኳን ሊቨርፑልን አይደግፉም፡፡ ያማ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መጥቶ፡፡ ዘመን ተቀይሮ፤ ደጋፊም ተደጋፊም ተቀይሮ፡፡ አዲስ ጀግና መጥቶ፣ አዲስ ተከታይ አፍርቶ፡፡ ያም ዘመን አለፈ፡፡ የነማንቸስተርና የነአርሴናልም ዘመን መጣ፡፡ እርሱም ሊያልፍ ነው መሰል፣ ደግሞ የነ ሌስተርና የነ ቶተንሐም ዘመን መጣ፡፡

‹በቃ ጨርሻለሁ› ወይም ‹በቃ ተጨርሻለሁ› አትበል፡፡ ‹አለቀ›ም ‹አለቀልኝ›ም አትበል፡፡ ካንተ በፊት ሌሎች ነበሩ፡፡ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፡፡ ‹ታግለን ጨርሰናል› ያሉ እንደ ቼልሲ ቦታ እየለቀቁ፣ ‹ገና ይቀረናል› የሚሉ ታጋዮች እንደ ሌስተር ቦታውን እየተረከቡ ይሄዳሉ፡፡ ሕይወት ሌስተርና ቼልሲ ናት፡፡  

ዳንኤል ክብረት