አሜሪካዊቷ እድለኛ ሴት 1 ሚሊየን ዶላር አሸናፊ ያደረጋቸውን የሎተሪ እጣ ቁጥር የያዘ ትኬት ለሁለት ወራት ያህል የት እንዳስቀመጡት አላስታወሱትም ነበር።
በምዕራባዊ አሜሪካ አይኦዋ ግዛት ነዋሪ የሆኑት ካሬን ሀርጌር ለግዛቱ የሎተሪ ፅህፈት ቤት ባለስልጣናት እንደተናገሩት፥ የሎተሪ እጣ ቲኬቶች ለጥቂት ሳምንታት የማከማቸት ልምድ አላቸው።
በዚህም ከሁለት ወር በፊት የቆረጡትን የሎተሪ ትኬት የት እንዳስቀመጡት ባለማዎቃቸው እድለኛነታቸውን ሳያረጋግጡ ቆይተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት ግን ድንገት የሎተሪ ቲኬቱ በኮምፒውተር ውስጥ ተቀመጦ ያገኙት ሲሆን፥ ይህም የህዳር 4 የሎተሪ እጣ አሸናፊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
ሀርጌር “ የሎተሪ ቁጥሩን በኮምፒተር እንደገና ለማረጋገጥ ስለተቸገርኩ፥ ባለቤቴን ለማየት እንዲችል አደረግኩት" ብለዋል።
በዚህም በጣም ፈርተው እንደነበር የገለፁት ሀርጌር፥ የ1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር አሸንፈናል ሲሉ ደስታቸው ገልፀዋል።
የሎተሪ ትኬቱን በድንገት እስኪያገኙት ድረስ ግለሰቧ የሎተሪ እጣ እንደደረሳቸው ምንም አያውቁም ነበር ነው የተባለው።
ከዚህ በፊት ከፖወርቦል የሎተሪ ትኬት ያገኙት ከፍተኛው የገንዘብ ሽልማት 10 የአሜሪካ ዶላር ብቻ እንደነበርም ነው ተናግረዋል።
የትኬቱ መገኘት ግለሰቧ የ1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሽልማታቸውን ከአይኦዋ ሎተሪ ፅህፈት ቤት ለመቀበል አስችሏቸዋል።
ምንጭ፦(ኤፍ ቢ ሲ) upi.com
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ