ረቡዕ 30 ማርች 2016

የደረጀ በላይነህ “የደመና ሳቆች” ለገበያ ሊቀርብ ነው

በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ሂሳዊ ጽሑፎችን በማቅረብ የሚታወቀው ደራሲና ገጣሚ ደረጀ በላይነህ የፃፈው “የደመና ሳቆች” የተሰኘ ረዥም ልብወለድ በመጪው ሳምንት ለገበያ ሊቀርብ ነው፡፡
የመፅሃፉ ጭብጥ በብላቴ አየር ወለድ ማሰልጠኛ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወታደራዊ ዘመቻ ላይና በወጣትነት የፍቅር ግጥምጥሞሽ ላይ ያጠነጥናል ተብሏል፡፡ መቼቱን ብላቴ፣ ተፈሪ ኬላ (ሲዳማ) እና ወላይታ ሶዶ ከተሞች ላይ ያደረገው ልብወለዱ፤በ230 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ58 ብር ለገበያ ይቀርባል፡፡ የመጽሃፉ አሳታሚና አከፋፋይም ጃፋር የመጻሕፍት መደብር መሆኑ ታውቋል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም በተለያዩ ዘውጎች 7 መፃህፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን ከእነዚህም መካከል “ብልጥ ጀንበር”፣ “የዕድሜ መንገድ”፣ “የአዳም ድንኳን” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ደረጀ በላይነህ በብስራት 101.1 ኤፍ ኤም ራዲዮ “አዲስ ምዕራፍ” የተሰኘና በናሁ ቴሌቪዥን “የኔታ” የሚል ፕሮግራም ከሙያ አጋሮቹ ጋር በማቅረብም ይታወቃል፡፡

ሃጢያት ከተደጋገመ ፅድቅ ይመስላል

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ አዕምሮውን ነካ ያደርገዋል የሚባል ሰው ቀን በጠራራ ፀሐይ ወደ አንድ የስልክ እንጨት (ምሰሶ) ይሄዳል፡፡ ከዚያም እንደ ስልከኛ ምሰሶው ላይ እግሩን አጠላልፎ መውጣት ይጀምራል፡፡
ሰው ምን ሊያደርግ ነው እያለ ዙሪያውን መክበብ ጀመረ፡፡ ዙሪያውን የከበበውን ሰው ያየ መንገደኛ ሁሉ ወደ ስብስቡ ተቀላቀለ፡፡ የሁሉም ሰው ጥያቄ፤
“ምን ሊያደርግ ይሆን?” የሚል ሆነ፡፡
ሰውየው መውጣቱን ቀጠለ፡፡ ህዝቡም መሰብሰቡን ቀጠለ፡፡
ከፊሉ - “ይሄ ሰውዬ ጫፍ ከደረሰ በኋላ ሊወረወር ነው፡፡ በጊዜ እናስወርደው” አለ፡፡
ከፊሉ - “ለማንኛውም ፖሊስ ብንጠራ ይሻላል”
ሌላው - “ፖሊስ ቢመጣ ምን ሊያደርግ ይችላል፡፡ በገመድ አይጠልፈው”
ሌላው - “ግዴላችሁም አንድ ሰው ተከትሎት ይውጣ”
“ተከትሎት ወጥቶ በእርግጫ ቢለውስ ዕብድ አይደለ እንዴ?”
“እባችሁ ምንም አይሆን፤ ዝም ብለን የሚያደርገውን እንይ”
“ለምን አንጠይቀውም?”
“ምን ብለን ልንጠይቀው ነው፤ እኛ ቴሌ ኮሙኒኬሽን አደለን”
“ለምን ለሚመለከተው መስሪያ ቤት አንነግርም”
“መሥሪያ ቤቱ ንብረቴ ነው ካለ እራሱ ይምጣ እንጂ እኛ ምን ቤት ነን?”
ዕብዱ ሰው መውጣቱን ቀጠለና ጫፍ ደረሰ፡፡
ቀጠለና ከኪሱ እስክሪቢቶና ወረቀት አወጣ፡፡
ታች ያለው ሰው ግምቱን አወጋ-
“ይሄዋ ኑዛዜውን እየፃፈ ነው”
“ዕብድ ደሞ ምን ኑዛዜ ይኖረዋል?”
“ምን ይታወቃል? ሰውኮ ሊሞት ሲል የሚናገረው ነገር ይበዛል”
“እባክህ፤ መንግሥትን ሊሳደብ ይሆናል”
“መንግሥት ለመሳደብ ምሰሶ ጫፍ ላይ መውጣት አለብህ እንዴ?”
ዕብዱ ሰው ጽሑፉን ጨረሰ፡፡ በፕላስተር ምሰሶው ጫፍ ላይ ለጠፈው፡፡
እየተንሸራተተ ወደ መሬት ወረደ፡፡
ታች ከተሰበሰበው ህዝብ አንዱ፤
“ምን ብለህ ጽፈህ ነው የለጠፍከው?” አለና ጠየቀው፡፡
ዕብዱ ሰውም
“ወጥቶ ማየት ነዋ!” ብሎ ሄደ፡፡
ከህዝቡ ማህል አንደኛው፤
“ወጥተን እንየው እንጂ” አለ፡፡
ሁሉም “አንድ ሰው ይውጣ” አለ፡፡
አንድ ጐበዝ ከማህል ወደ ስልክ እንጨቱ ሄደ፡፡
ሁሉ ሰው አበረታታው፡፡ “ጐበዝ ውጣ!” “ቀጥል ጀግናው!” “ይሄ ነው ወንድ!” “ግፋ!”
ሰውየው እግሩን እየሳበ ወጣ ወጣና ጫፍ ደረሰ፡፡ ወረቀቱ ላይ የተፃፈውን አየ፡፡
ታች የለው ህዝብ “አንብብልን!” ብሎ ጮኸ፡፡
ጐበዙ ሰው ጮክ ብሎ አንበበው፤
“የምሰሶው ጫፍ እዚህ ጋ ነው!”
*   *   *
ማንኛውም ሰው ህዝብን እንዳሻው ለመንዳት ከቻለ ሀገር ላይ ችግር አለ፡፡ ያ ሰው ዕብድ ከሆነ ደግሞ የባሰ ችግር አለ፡፡ አሳሳቢ ሆነ ማለት ነው፡፡ ጥርጣሬ ላይ የወደቀ ህዝብ ይዋልላል፡፡ በመንግሥት፣ በተቋማትና በማህበራት ላይ ዕምነት አይኖረውም፡፡ ዕምነት ያጣ ህዝብ ከመምራት ዕምነት የለው የልቡን የሚናገር ተቃዋሚ ህዝብ መምራት ይሻላል ይላሉ ፀሐፍት፡፡
ኢትዮጵያን በተለየ መንገድ ለማሳደግ ህዝብ በአጭበርባሪዎች እንዳይታለል ተቆጣጥሮ ህጋዊነትን ማስከበር ያሻል፡፡ ህዝብ ሙሉ ዕምነት ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡
ተቋማቱን አስተማማኝና እርግጠኛ ፍቃደ ልቡና ይለግሳቸው ዘንድ እንዳይመዘበር፣ እንዳይበዘበዝ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ለዚህም የአስተሳሰብ ብልጽግና፣ የግንዛቤ ጥራት፣ የልብ ለልብ መግባባትና የመቻቻል ምንነት በግልጽ የገባው ሊሆን ያሻል፡፡ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን የሚመርጥበት ምክንያት ከልምድ ከተማረው በተጨማሪ ወቅታዊ ንቃት እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡
ሙስናን ለመቋቋም እየሰጋን መሆን የለበትም፡፡ መታሠር ያለበት ህገ ወጥ ሰው ከሆነ የፍርድ ቤት ጉዳይ እንጂ የእከሌ ከእከሌ አማራጭ መፍጠር ወይም “አጥፊው ስለበዛ እንተወው” መፍትሔ አይሆንም፡፡ ሁሉም የየድርሻውን ማግኘቱ የፍትሕን መጉላትና መጠንከርን እንደሚያሳይ አለመዘንጋት ነው፡፡ በተለይ በህዝብ ላብ የሚቀልድ ማንም ይሁን ማን ሊተው አይገባም፡፡ በተለይም በልዩ መዋቅር ተሳስሮ ጀርባው ደንደን ያለውን መተው፣ ኮሳሳውን ማጥቃት ለፍትሕ ጐጂ ባህል ነወ፡፡ ይህን የሚያስከብሩ ተቋማት መጠንከር አለባቸው። ይህም ሲባል ተቋማቱ ግዑዝ አይደሉምና የሚመሯቸው ሰዎች በሚሠሩት አምነውና ጠንክረው ይጓዙ ማለታችን ነው፡፡
አበሻ አደባባይ ያምናል፡፡ ለአበሻ ሚዲያ መንግሥት ነው፡፡ ስለሆነም ለማናቸውም ሚዲያ ተጠቃሚ ተአማኒ ነው፡፡ ሚዲያ ላይ የቀረበ፤ አንድም መንግሥታዊ ነው፣ አንድም የታመነ ነው!  ቴሌቪዥን አይቶ፣ ሬዲዮ ሰምቶ የማያውቅ ሰው እንኳ ቢሆን በቴሌቪዥን ታየ፣ በሬዲዮ ተነገረ ካሉት የዕምነቱን ዣንጥላ ይዘረጋል፡፡ በአደባባይ የታየው፣ የተሰማው ነገር ህጋዊ ነው እንደማለት ነው! የዛሬ ዘመን የ “ቢዝነስ” ሁኔታ የደራሲ አቤ ጉበኛን “ጐብላንድ አጭበርባሪው ጦጣን” የሚያስታውሰን ነው፡፡ ለነገሩ የተመዘበረው ብር ብዛት ሲታይ እሰው እጅ ያለው ገንዘብ ኤሎሄ ያሰኛል፣ እንደ ልብ ደረቅ ቼክ መፃፍ፣ ባንክ ውስጥ በቂ ገንዘብ የለውም መባል፤ የወትሮ ነገር ሆኗል፡፡ ዲቪ የደረሰው ቀርቶ ያልደረሰው ይሄዳል በሚባልበት፣ ኮንዶምኒየም የደረሰው ቀርቶ ያልደረሰው ይኖርበታል በሚባልበት፣ ፖለቲካው ግራ ሲያጋባንና የምሁርነት ጥልቀት እያደር እንደ ውሃችን ቱቦ ሲደፈን
“እንተኛም ካላችሁ፣ እንገንደሰው
መኝታ እንደሆነ ቀርቷል ካንድ ሰው”
የሚል ዘፈን በምናቀነቅንበት ሀገር፤ ፖለቲካ ሁሉ የመሬት ጉዳይ ቢሆን ብዙ የሚያስደምም ሁኔታ አይሆንም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ለምሁራን ታዳሚዎች እንዳሉት፤ “እኛም እናንተም ችግር አለብን፡፡…ህብረተሰቡም እልከኛ ነው”…ይህንን የችግር ሶስት ማዕዘን (Triangular problem) መቼ እንደምንገላገለው ማሰብ ይጠበቅብናል፡፡
ችግሩ ባለቤት እንጂ ሁልቆ መሣፍርት የለውም፡፡ ዘርዝሮ ማየት እንጂ ችግር አለብን ብቻ መፍትሔ አይሆነንም፡፡ “የኤሊት ግሩፕ ቱጃር እየፈጠርን መጓዝ አንችልም” ያሉት ግን ሊሰመርበት የሚገባ ሀቅ ነው፡፡ “የመላዕክት ስብስብ አይደለንም” ያሉትም ሌላው ሀቅ ነው፡፡
በተደጋጋሚ የምናሰማው እሮሮ መጠነ ሰፊ ሆኗል፡፡ ሙስና አጠጠ፣ ት/ቤቶች ጥራት የላቸውም፡፡ መሠረተ - ጤና እንደምንፈልገው አልተስፋፋም፡፡ ተቋማት ይቋቋማሉ እንጂ አፈፃፀም የላቸውም፡፡ ባንኮች ንፅህናቸው አልተፈተሸም የከፍተኛ አመራሩ ችግር አለበት፡፡ ከፖለቲካ ልዩነት፤ ከሃይማኖት ልዩነት፣ ከዘር ልዩነት ነፃ ነን እንበል እንጂ ጣጣው አልለቀቀንም፡፡ “ሃጢያቱ ከተደጋጋመ ፅድቅ ይመስላል” ይሏልና፣ ቆም ብለን ተግባር ላይ እናተኩር!!
ምንጭ፡- አዲስ አድማስ ጋዜጣ ርዕስ አንቀፅ

ጋዜጠኝነት በሙስና የተዘፈቀ ነው ተባለ

90 በመቶ ጋዜጠኞች በሥራቸው እርካታ የላቸውም
   በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ በጥቅማ ጥቅም የታሠረና በሙስና የተዘፈቀ መሆኑን የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የቀረበ ጥናት አመለከተ፡፡
“በመገናኛ ብዙኃን መልዕክቶች ዙሪያ የሚታዩ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቻቸው” በሚል ርዕስ ከትናንት በስቲያ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህርና የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፤ ጋዜጠኞች ዘገባ ለማቅረብ ጉቦና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚቀበሉ ጠቁመዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ትንሹ ስራቸው በሚዲያዎች ተጋኖ እንዲቀርብላቸው ጋዜጠኞችን ለመደለያ በእቅዳቸው ውስጥ በጀት እስከ መያዝ ደርሰዋል ያሉት አጥኚው፤ በዚህ ምክንያት ጋዜጠኞች ህብረተሰባዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ተፅዕኖ ውስጥ ወድቀዋል ብለዋል፡፡
ችግሩ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም በስፋት እንደሚንፀባረቅ የጠቆሙት ጥናት አቅራቢው፤ በፖስታ ታሽጐ ከሚሠጥ ገንዘብ ጀምሮ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች፣ ከልብስና ጫማ ጀምሮ ውድ ስጦታዎች ድረስ እንዲሁም ለአንድ የዘገባ ስራ የትራንስፖርት፣ የማደሪያና የምግብ … የመሳሰሉ ወጪዎችን መሸፈን በኢትዮጵያም ይሁን በአህጉሪቱ የተለመደ መሆኑን በመግለፅ፣ ይሄም ከሙያው ስነምግባሮቹ ጋር የሚጋጭ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
በብርሃኑ ሌዳሞ ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያ የተሠራን ጥናት የጠቀሱት ጽሑፍ አቅራቢው፤ ስለ መደለያ ገንዘብና ሌሎች ስጦታዎችን ስለመቀበል ከተጠየቁ ጋዜጠኞች መካከል 83.3 በመቶ ያህሉ ለሚሰሩት ዘገባ ገንዘብ ወይም ሌሎች ጥቅማ ጥቅም እንዲሠጣቸው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ብለዋል፡፡
ጋዜጠኞች ገንዘብና ጥቅማ ጥቅም የሚገኝባቸውን “ቡጬ ያለው” በሚል እንደሚለዩ የጠቀሱት አጥኚው፤ ገንዘብም ሆነ ጥቅማ ጥቅም የሌላቸው ተቋማት “ደረቅ ጣቢያዎች” የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡ ገንዘብና ጥቅማ ጥቅም የማይቀበሉ ጋዜጠኞች፣ በተቀባዮቹ የተለያዩ ስያሜዎች እንደሚሠጣቸው ሲገልፁም፤ “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያና የኤርትራ መልዕክተኛ” ወይም “ወጋሚ” የሚሉ ስያሜዎች እንዳላቸው ጥናት አቅራቢው አብራርተዋል፡፡
በአሁን ወቅት ጥቅም የተገኘባቸው ዘገባዎችና ፕሮግራሞች በቀላሉ እየተለዩና እየታወቁ እንደመጡ ያመለከቱት አጥኚው፤ ጥቅም የተገኘባቸው ዘገባዎችና ፕሮግራሞች ሳቢና ማራኪ ተደርገው ሲቀርቡ ያልተገኘባቸው ደግሞ “እንደነገሩ” ይቀርባሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ለገንዘብና ጥቅማ ጥቅም ተገዢ እየሆኑ የመጡበት ምክንያት በዋናነት ከመስሪያ ቤታቸው የሚያገኙት ደሞዝና ጥቅማጥቅም ዝቅተኛ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡
በሀገሪቱ 89.6 በመቶ የሚሆኑት ጋዜጠኞች በስራቸው እርካታ እንደሌላቸው የጠቆመው ጥናቱ፤ ይሄም ለሚዲያ ባለሙያዎች ከሚከፈለው ደሞዝ ጋር የተገናኘ መሆኑን አመልክቷል፡፡
ጋዜጠኞች ከሙስና ፀድተው በሙያቸው እንዲሠሩ በቂ ስልጠና ማግኘት ይኖርባቸዋል ያሉት አጥኚው፤ በየተቋሞቻቸው የስነ ምግባር መመሪያ መዘጋጀት እንዳለበትና ደሞዛቸውም ከፍ ሊል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት፤ አለማቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሰሰች

የተከለከለ አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅማለች በሚል ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ ከውድድር እንድትታገድ የተወሰነባት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ኢቫን አቢይ ለገሰ  ውሳኔው የተላለፈብኝ ያለአግባብ ነው በሚል አለማቀፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኞች ማህበር መክሰሷን ሲኤንኤን ዘገበ፡፡
ለቱርክ የምትሮጠው አትሌቷ እ.ኤ.አ በ2005 እና 2007 በተከናወኑት የአለም ሻምፒዎናዎች በተደረጉላት የሽንት ምርመራዎች የተከለከለ ንጥረ ነገር መገኘቱን ተከትሎ፣ በቱርክ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከውድድር መታገዷን ያስታወሰው ዘገባው፣ በምርመራዎቹ ላይ የቴክኒክ ስህተቶች ተፈጽመዋል በሚል በሞናኮ የአስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቷን ጠቁሟል፡፡
የአትሌቷ ወኪል ኦንዴር ኦዝባይለን በበኩላቸው፤ በአለማቀፉ የጸረ አበረታች እጽ ተቋም እውቅና በተሰጠው አንድ የምርመራ ላቦራቶሪ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያ በጉዳዩ ዙሪያ የሰጧቸውን መረጃዎች መሰረት በማድረግ፣ ክሱን እንደመሰረቱና በምርመራው ወቅት ዘጠኝ ያህል የቴክኒክ ስህተቶች መፈጸማቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ለተባለ የዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ስህተቶቹ መፈጸማቸውን ካረጋገጠ፣ የአለማቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በአትሊቷ ላይ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ውድቅ እንደሚደረጉም ወኪሉ ገልጸዋል።
አትሌቷ ባለፈው አመት የተባለውን አበረታች ንጥረ ነገር አለመጠቀሟንና እንዲህ አይነት ህገወጥ ተግባር ለመፈጸም አስባ እንደማታውቅ መናገሯን የጠቆመው ዘገባው፣ ኦሳካ ላይ በተካሄደው የ2007 የአለም ሻምፒዮና በአስር ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ ማግኘቷንም አስታውሷል፡፡

ትኩስ መረጃዎችን ፣ድንቃድንቅ እና አዝናኝ ቪዲዮዎችን ፣ ጠቃሚ ትምህርቶችን ከማሲንቆ ኢንተርቴመንት ብቻ Like ስላደረጉ እናመሰግናለን


ትኩስ መረጃዎችን ፣ድንቃድንቅ እና አዝናኝ ቪዲዮዎችን ፣ ጠቃሚ ትምህርቶችን ከማሲንቆ ኢንተርቴመንት ብቻ Like ስላደረጉ እናመሰግናለን

ትኩስ መረጃዎችን ፣ድንቃድንቅ እና አዝናኝ ቪዲዮዎችን ፣ ጠቃሚ ትምህርቶችን ከማሲንቆ ኢንተርቴመንት ብቻ Like ስላደረጉ እናመሰግናለን

ዓርብ 25 ማርች 2016

#አዲስ አበባ ከተማና ከንቲባዎቾ


የዛሬዋ አዲስ አበባ ከተማ ከ1901ዓ.ም ጀምሮ ቁጥራቸው በዛ ያለከንቲባዎችን ማፈራረቋ የታሪክ መጽሐፍት መረጃውን ይጠቁማሉ ከተማዋ ከንቲባ መሾም ስትጀምር እንዳውኑ በአዲስ አበባ ምክር ቤት አልነበረም የከንቲባ ሹመት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት መነሻ ታሪክ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን በ1901 ዓ.ም ቢትወደድ ወልደ ጻዲቅ ጎሹ የመጀመሪያው ከንቲባ ሆነው ቢሾሙም የአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆኑ የጎንደር ከንቲባ ሆነው በመሾም እንዳገለገሉና የአገልግሎት ዘመናቸውም ከ1901 እስከ 1908 እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ ሆኖም በአንዳንድ መረጃዎች መሠረት ደግሞ የአገልግሎት ዘመናቸው ከ1892 ይጀምራል ይላል፡፡ ሲሾሙ ማዘጋጃ ቤት የሚባል ነገር አይታወቅም ሆኖም ቀደም ብሎ ግን ‹‹የከተማ ማህበር ቤት›› ይባል የነበረና የጠፉ ከብቶችንና በተከለከለ ቦታ የተገኙ የቤት እንስሶችን አፈላልጎ አስከፍሎ የሚሰጥ ቤት ነበር ታዲያ ይህ ቤት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የማዘጋጃ ቤት አሠራርን ያስጀመሩበት ነው ተብሎ ይገለፃል፡፡
በ1909 ዓ.ም ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ቢትወድ ኃይለ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ቆይታቸውም ለአንድ ዓመት ያህል የነበረ ሲሆን በቆይታቸውም ወቅት በተለይ የንግዱ ዘርፍ እንዲለማ ከፍተኛ ጥረት ያዳረጉ ሲሆን ለዚህም ደግሞ የንግድ ሚኒስተር ሆነው እንዲሾሙ አስተዋጾ አድርጎላቸዋል ይባላል፡፡  

ሐሙስ 24 ማርች 2016

ታዋቂነትና አዋቂነት…’

እንዴት ሰነበታችሁሳ!
ስሙኝማ…ሀሳብ አለን… ‘ታዋቂነት በአቢሲንያ’ የሚል መጽሐፍ ይጻፍልን፡፡ ግራ ገባና! አሀ…አለ አይደል…ታዋቂ ማለት
ሀ. ‘ባያውቅም የሚያውቅ፣’
ለ. ‘ባይጸልይም መባረክ የሚችል፣’
ሐ.‘ባያነብም መፃሕፍት መተቸት የሚችል’’…
ምናምን እየተባለ ይዘርዘርልንና እኛም ግራ ከመጋባት እንትረፍማ፡፡
ስሙኝማ…መቼም ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ…ጠቅላላ ሚዲያው ለምኑም ለምናምኑም ‘አርቲስት’ የሚባሉትን ብቻ የሚጠራው ግርም አይላችሁም! አሀ… አርቲስቶች… “አይ ሀቭ ኤ ድሪም…” ብለው ሚዲያውን ከሰፊው ህዝብ መዳፍ ፈልቅቀው ያወጡት ይመስላላ! ቂ…ቂ…ቂ…
የምር ግን…በተለይ በበዓላት ቀናት ከምናያቸው የአርቲስቶች ቃለ መጠይቆችና በተለይ ደግሞ  ‘ጨዋታዎች’’… አንዳንዶቹ አሸማቃቂ እየሆኑ ነው፡፡ ያውም ልጆች እንኳን ከዛ በስንት እጥፍ በሚያስቡበት ዘመን!
እናላችሁ…ምን ችግር አለ መሰላችሁ…አርቲስቶች ወይም ‘ታዋቂ ሰዎች’ በየምክንያቱ ለቃለ መጠይቅ ሲቀርቡ… አለ አይደል… ከ‘ኪሎ በላይ’ የሆነ ጥያቄ እየተጠየቁ እኛንም ክው ያደርጉናል፡፡ አንድ ጊዜ አንዲት የፊልም ሰው በቴሌቪዥን እየተጠየቀች ነበር፡፡ እናላችሁ… በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ያለው የፊልም ኢንደስትሪ ከእኛ የተሻለ ስለመሆኑ አይነት ነገር ትጠየቃለች፡፡ እናላችሁ… እሷዬዋ ምን ብላ ብትመልስ ጥሩ ነው…
“ምን እነሱ የሚያሳዩት ዶሮ ምናምን ነው…”
ምን ታድርግ…ከሁለትና ወይም ሦስት ፊልም ጋር ስለተነካካች ከ‘ኪሎ በላይ’ ስለ አፍሪካ የፊልም ኢንደስትሪ ተጠየቀቻ! ችግሩ ምን መሰላችሁ…የጥያቄ ቅደም ተከተሉ ልክ አይደለማ! መጀመሪያ መጠየቅ የነበረባት…
“አፍሪካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለተመልካቾቻችን ብትገልጪልን?” ተብሎ ነበር፡፡ እናማ…ጋዜጠኛው ዘሎ የፕሬሚየር ሊግ ጥያቄ ሲጠይቃት ምን ታድርግ!
እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ብሔራዊ ዲቪዥን እንኳን ገና ሳይገባ የፕሬሚየር ሊግ ጥያቄ ሲቀርብ… “አይ ስለዚህ እንኳን ብዙም መረጃው የለኝም…”
“ይገርምሀል ይህንን እንኳን እኔም ማወቅ የምፈልገው ነው፣” ምናምን ማለት ማንን ገደለ! ይቅርታ ማንን ከ‘ታዋቂነት ዙፋን’ አወረደ!
እናማ…‘ጋዜጠኞች’… አለ አይደል… ‘ከኪሎ በላይ’ የሆኑ ጥያቄዎች እየጠየቅን ‘ታዋቂዎች’ን ‘ሄደውበት በማያውቁት’ መንገድ አንውሰዳቸውማ፡፡
ከ‘ኪሎ በላይ’ የሆነ ነገር አሪፍ አይደለም፡፡
በነገራችን ላይ ታዋቂ ስለሆኑ ብቻ ‘ሁሉንም ነገር አውቃለሁ’ አይነት ነገር እኛ ዘንድ ብቻ አይደለም፡፡ እነኚህ ምናቸውንም፣ ምናምናቸውንም እየኮረጅን (‘እየነጠቅን’ ማለትም ይቻላል፣) ‘ባዶአቸውን ሊቀሩ’ ጫፍ ላይ ያሉት ‘ፈረንጆች’ ቀላል ይዘባርቃሉ እንዴ!
አሽተን ኩቸር አሪፍ ተዋናይ ነው፡፡ እናላችሁ…. አንድ ጊዜ ምን አለ መሰላችሁ…
“ግንባርህ ላይ ያሉት መስመሮች ብዛት ምን ያህል ህይወቶች እንደኖርክ ይናገራሉ፡፡” አሁን ኩቸርን ፊልም ላይ ስታዩት ዘብረቅ ያደርጋል ብለን እንጠብቃለን? እናማ…‘ታዋቂ’ መሆን ሌላ፣ ‘አዋቂ’ መሆን ሌላ! (ይቺን መፈክር ለማድረግ የፈለገ ‘ፍሪ ዳውንሎድ’ ፈቅጃለሁ፡፡)
እናላችሁ…እኛ ዘንድ አንዳንድ ጊዜ የግንባር መስመር ቆጠራ ድረስ ባይደርሱም…ከዚህ አይነቱ የማይሻል አስተያየት የሚሰጡ የእኛው ‘ታዋቂዎች’ አሉ፡፡
ሻኪል ኦኔል ምርጥ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነው፡፡ በዛ ሰውነቱ ቅርጫት ኳስ ሜዳው ላይ ሲነግሥበት ስታዩት…አለ አይደል…አንዲትም የተዛባች ነገር ከአንደበቱ የምትወጣ አይመስላችሁም፡፡  (እውቅናና እውቀት ተቀላቀሉብና!)
ታዲያላችሁ…አንድ ጊዜ ግሪክን ጎብኝቶ አገሩ ይመለሳል፡፡ ግሪክን መጎብኘት ማለት ደግሞ በአብዛኛው እነኛን ጥንታዊ የስነ ህንጻ ጥበቦች ማየት ነው፡፡ እናማ…ጋዜጠኞቹ እነኚህን ጥንታዊ የግንባታ ጥበቦች መቼም ሳያይ አይመጣም ብለው “በጉብኝትህ ወቅት ፓርቴኖንን አይተኸዋል?” ብለው ይጠይቁታል፡፡ ምን ብሎ መለሰ መሰላችሁ…
“እንደ እውነቱ የሄድኩባቸውን የምሽት ክበቦች ሁሉ ስማቸውን ማስታወስ አልችልም፡፡” ቂ…ቂ…ቂ… ይሄኔ ዘመዶቹ ‘ትከሻ ብቻ’ ሳይሉት አይቀሩም፡፡
ከ‘ኪሎ በላይ’ የሆነ ነገር አሪፍ አይደለም፡፡
አሁን፣ አሁንማ…አለ አይደል… ‘አዋቂ አላዋቂውም፣’ ‘አላዋቂ አዋቂውም፣’…ብቻ ምን አለፋችሁ… ሁሉ ነገር እንደ ‘ማህበራዊ ምግብ’ አይነት ሆነና ግራ ተጋብተናል፡፡ እናላችሁ…የቱ “በትክክል ተመልሷል…” የቱ “ለዛሬው አልተሳካልህም…” እንደሚባል ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ የምር…አለ አይደል…ኤፍ ኤሞች ላይ የሚሰሙ የ‘መረጃ’ ስህተቶች መአት ናቸው፡ ብዙዎቹ ስሀተቶች ደግሞ ከኢንተርኔት የሚገኙ መረጃዎች ሲተረጉሙ የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ እናማ…ብዙ ሰው በሚዲያ የሚሰማቸውን ነገሮች ሁሉ እንደ ‘እውነተኛ መረጃዎች’ ስለሚወስዳቸው አስቸጋሪ ነው፡፡
ዓይኔን ሰው አማረው
ዓይኔን ሰው አማረው
የሰው ያለሀ የሰው
የምትለዋ ስንኝ የምርም ዘመን ተሻጋሪ ነችሳ!
አንድ ጊዜ ደግሞ የሆነ አቀንቃኝ (አይደል የሚባለው!) ስለ ሙዚቃ በቴሌቪዥን እየተጠየቀ ነበር፡፡ እናላችሁ…ስለ ዓለም ሙዚቃ አስተያየቱን ይጠየቃል፡፡ እናማ…ምን ብሎ ቢመልስ ጥሩ ነው…
“ምን ሙዚቃ አለ፣ ራፕ ብቻ ነው፡፡” ቂ…ቂ…ቂ…
ከ‘ኪሎ በላይ’ የሆነ ነገር አሪፍ አይደለም፡፡
እናላችሁ…ይሄ ታዋቂነትና አዋቂነትን የመቀላቀል ነገር የት ይደርሳሉ የሚባሉ ልጆችን መንገድ ላይ እንዳያስቀራቸው ፍሩልኝማ፡፡
የካን ፊልም ፌስቲቫል በየዓመቱ ካን ውስጥ ይካሄዳል፡፡ (አራት ነጥብ፡፡) ክሪስቲና አጉሌራ የተባለችው ድምጻዊት ምን ብላ ጠየቀች አሉ መሰላችሁ…
“የዘንድሮ የካን ፊልም ፌስቲቫል በዚህ ዓመት የት ነው የሚካሄደው?”
“የዘንድሮ የጃን ሜዳ አገር አቋራጭ የት ነው የሚካሄደው?” ለማለት ያሰባችሁ፣ ድምፃዊቷ ትምህርት ትሁናችሁ፡፡ ቂ…ቂ..ቂ…
አሁን ዴቪድ ቤካም ቀሺም ነገር የሚናገር ይመስላል! አንድ ጊዜ ምን አለ አሉ መሰላችሁ…የልጁን ክርስትና መነሳት እንደሚፈለግ ከተናገረ በኋላ ምን ቢል ጥሩ ነው… “ግን በየትኛው ኃይማኖት እንደሆነ ገና አላውቅም፡፡” የምር…ቤካም ራሱ ነው እንዲህ ያለው፡፡
ደግሞላችሁ… ነገር የሚገንባት የምትባለው ብሪቲኒ ስፒርስ አንድ ጊዜ ምን አለች አሉ መሰላችሁ…
“እንደ እውነቱ ጃፓን ለመሄድ ፈልጌ አላውቅም፡፡ ምክንያቱም አሳ መብላት አልወድም፡፡ እዛ አፍሪካ ውስጥ ደግሞ አሳ በጣም የሚወደድ መሆኑን አውቃለሁ፡፡”  ቂ…ቂ…ቂ… (ጆርጅ ቡሽ እንኳን አፍሪካ ‘አገር’ አለመሆኗን ያወቁት ዘግይቶ ነው ይባል የለ!)
ብሩክ ሺልድስ በጊዜዋ የታወቀች ተዋናይት ነበረች፡፡ እናላችሁ… በአንድ ወቅት የፀረ—ማጨስ ዘመቻ ቃል አቀባይ ሆና ነበር፤ አንድ ጊዜ መግለጫ ስትሰጥ ምን አለች መሰላችሁ…
“ማጨስ ሊገድልህ ይችላል፡፡ ከሞትክ ደግሞ ከህይወትህ እጅግ ዋና ክፍል አጥተሀል ማለት ነው፡፡” ቂ…ቂ…ቂ… የፀረ—ምናምን ዘመቻ ውስጥ ቃል አቀባይም ሆነ ‘ቃል ተቀባይም’ የምትሆኑ… ይቺን ነገሬ በሉልኝማ፡፡
“ከልክ በላይ ከበላህ ከልክ በላይ ትወፍራለህ፣ ከልክ በላይ ወፈርክ ማለት ደግሞ ክብደትህ ጨመረ ማለት ነው፣” አይነት ነገር… አለ አይደል…ብዙ እርፍና የሚጠይቅ አይመስልም፡፡
ታዋቂዎች አዋቂ የሆኑ ሲመስላቸውና አጉል ሲራቀቁ ምን እንደሚፈጠር ማሪያ ኬሪ በአንድ  ወቅት አለች የተባለችውን ስሙኝማ…
“ቴሌቪዥን ላይ እነኛን ድሀ፣ የተራቡ ህጻናት ባየሁ ቁጥር አለቅሳለሁ፡፡ ማለቴ፣ እንደ እነሱ ብቀጥን ደስ ይለኛል፣ ግን ያለ ዝንቦቹና ሞት ሳይኖር ማለት ነው፡፡” አያስደነግጥም!
እናማ…ታዋቂዎቻችን ከ‘ኪሎ በላይ’ የሆነ ነገር ሲገጥም…አለ አይደል…“አይ ስለዚህ እንኳን የማውቀው ነገር የለም…” ማለት ከ‘ታዋቂነት’ መዝገብ አያስፍቅም፡፡
ደህና ሰንብቱልኝማ!
 Written by  ኤፍሬም እንዳለ

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚነት ለድብርት ያጋልጣል - ጥናት

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚነት ለድብርት ያጋልጣል - ጥናት

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች በዚህ ዘመን እጅግ ተፈላጊና ተዘውታሪዎች ናቸው።
በተለያየ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን በማቀራረብና መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚረዳው የማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ደግሞ በወጣቶች ዘንድ በስፋት ይዘወተራል።

ይህ መሆኑ ሃሳብና መረጃዎችን በመለዋወጥ ከሰዎች ጋር የሚኖርን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከዚህ ባለፈ ግን ሲበዛና ከመጠን በላይ ሲሆን ጉዳት እንደሚያስከትልም ነው የሚናገሩት።

ባለፉት ሁለት አመታት አደረግነው ባሉት ጥናት አብዝቶ መጠቀም፥ ከጭንቅላት ጋር ተያያዝ ለሆኑ ችገሮች ያጋልጣል ይላሉ።

ከፍተኛ ጭንቀት እና ድብርት እንዲሁም ለእንቅልፍ እጦት እንደሚዳርግ መረጃዎችን አስደግፈው ይገልጻሉ።

ከሰሞኑ ባወጡት አዲስ መረጃ ደግሞ የማህበራዊ ሚዲያ አብዝተው የሚጠቀሙ ሰዎች ለድብርት እንደሚጋለጡ ነው የገለጹት።

ጥናቱ በአሜሪካ ፔንሲልቫኒያ ፒትስበርግ በሚገኘው የህክምና ትምህርት ክፍል የሚገኙ ባለሙያዎች የተካሄደ ነው።

ይህ ጥናት በአሜሪካ ብሄራዊ የጤና ተቋም የተደገፈ ሲሆን፦ ከ19 እስከ 32 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን ያካተተ ነው።

በጥናቱ 1787 ሰዎችን በማሳተፍ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ዙሪያ አጠቃላይ መረጃን በመሰብሰብ የተደረገ ነው።

ከዚህ ባለፈም አዲሱ ጥናት ከቀደሙት በተለየ ከ10 በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ያሳተፈና ሰፋ ያለም ነበር ነው የተባለው።

በዚህ ጥናታቸው አብዛኛዎቹ በቀን በአማካኝ 61 ደቂቃዎችን እንዲሁም በሳምንት የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸውን ለ30 ያክል ጊዜ ከፍተው የሚጠቀሙ ሆነው አግኝተዋቸዋል።

በዚህ መልኩ የሚጠቀሙት ከማይጠቀሙት በ2 ነጥብ 7 በበለጠ መልኩ ለድብርትና አለመረጋጋት የተጋለጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን አንስተዋል።

ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ መሆን ከማይጠቀሙት በ1 ነጥብ 7 በበለጠ ሁኔታ ለዚህ ችግር እንደሚያጋልጥም ነው ያስረዱት።

እናም የማህበራዊ ሚዲያ አብዝተው የሚጠቀሙት ከማይጠቀሙት ይልቅ፥ ለከፍተኛ ድብርት፣ አለመረጋጋት እና ትኩረት ማጣት የተጋለጡ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።

ይህ ደግሞ ሙሉ ትኩረታቸው የያዙት ነገር ላይ ስለሚሆንና ከሌላው መነጠል ደግሞ ለዚህ መንሰኤ ነው ሲሉም ነው ባለሙያዎቹ ማጠቃለያቸውን ያስቀመጡት።

ምንጭ፦ medicalnewstoday
- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/%E1%8C%A4%E1%8A%90%E1%8A%9B-%E1%8A%91%E1%88%AE/item/14745-%E1%8B%A8%E1%88%9B%E1%88%85%E1%89%A0%E1%88%AB%E1%8B%8A-%E1%88%9A%E1%8B%B2%E1%8B%AB-%E1%89%B0%E1%8C%A0%E1%89%83%E1%88%9A%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%88%E1%8B%B5%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8B%AB%E1%8C%8B%E1%88%8D%E1%8C%A3%E1%88%8D-%E1%8C%A5%E1%8A%93%E1%89%B5.html#sthash.gWpHayNZ.dpuf

ረቡዕ 16 ማርች 2016

ስጋዬን ቀመስሁት


ደርቆ ከበሰለዉ  ከተንጠለጠለዉ፣
የስጋ  ደረቆት‹‹ ቁዋንጣ›› ከሚባለዉ፤
አየሁት ስጋዬን  ለየሁት በሩቁ፣
ቀመስኩት፣ በላሁት ጣፈጠኝ  መረቁ፣
ወጥ  ሆኖም  አየሁት  በድስቱ ሲማሰል፣
ሲጎመድ፣ ሲጎረድ ፣ ሲከተፍ ሲቀቀል፣
በነፈረ ዉሃ ተነፍሮ  ሲበሰል፣
ቀመስኩት በእንጀራ የእኔዉም አይመስል፡፡
ደሞ  አልጫ ሆኖ  በቀለም ኮስምኖ፣
በቅመማት ዋይታ ሁለመናዉ ቀጥኖ፣
አየሁት ስጋዬን ራሱን ለዉጦ፣
በሱፋ፣ በቅባኑግ፣ በቅባቶች ቀልጦ፡፡
በማንም ወጥ ቀቃይ፣ በሰላ ቢላዋ፣
ሲከፈት አየሁት ሲደቅ እንዳሸዋ፡፡
ክትፎዉን  ቀመስኩት በጣሙን  ይጥማል፣
የእጄ ጣም ራሱ እጅ ያስቆረጥማል፡፡
ምንጭ ካነበብ ነው
(አበራ አዳሙ ውዳሴ ሞት የግጥም መድበል

ሰኞ 14 ማርች 2016

አማርኛ በጉግል

ጉግል የአማርኛ ቋንቋን ከሌሎች 13 ተጨማሪ ቋንቋዎች ጋር በይፋ መተርጎም መጀመሩን ከገጠ ዛሬ ሁለት ሣምንታትን አስቆጠረ። የካቲት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው የጉግል የትርጉም ሥራ የመጀመሪያ ከመኾኑ አኳያ ስህተቶች ቢታዩበትም በጥንቃቄ የተተረጎሙ ቃላት እና ሐረጎችንም መመልከት ይቻላል።

አማርኛ ትርጉም በጉግል

በኢንተርኔቱ ዓለም ግዙፍ የሆነው ጉግል ከዚህ በፊት የትርጉም አገልግሎት ከሚሰጥባቸው 90 ቋንቋዎች በተጨማሪ 13 ቋንቋዎችን መተርጎም ጀምሯል። ከሣምንታት በፊት አዲስ መተርጎም ከጀመሩት ቋንቋዎች ውስጥ የአማርኛ ቋንቋም ይገኝበታል። ጉግል የአማርኛ ቋንቋ ትርጉም አገልግሎት የሚሰጠው እንዴት ነው? የአገልግሎቱ ፋይዳስ ምንድን ነው?

ጉግል ከዛሬ ዐሥር ዓመት በፊት ማሽንን መሠረት ያደረገ የትርጉም ሥራ የጀመረው በአራት የዓለም ቋንቋዎች ነበር። እንግሊዝ፣ ዐረብ፣ ቻይና እንዲሁም ሩስያ ላይ ትኩረት አድርጎ የተጀመረው የጉግል የትርጉም ስራ ዛሬ አማርኛን ጨምሮ በብዛት 103 ቋንቋዎችን የሚያካትት ኾኗል። ለመሆኑ ጉግል የትርጉም ሥራውን እንዴት ነው የሚያካትተው። የመጀመሪያ እና ድኅረ ምረቃ ዲግሪያቸውን በኮምፒውተር ሣይንስ የያዙት የሶፍትዌር ዴቨሎፐር ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ አየለ።

አማርኛ ቋንቋ በጉግል የትርጉም ሥራ አገልግሎት ውስጥ መግባቱ ለቋንቋው እድገት የሚኖረው አስተዋጽዖ ላቅ ያለ ነው። የትርጉም ሥራው መጀመር የሣይንስ እና ስነ-ቴክኒክን ጨምሮ፣ የፍልስፍና እና ሌሎች ቃላት ከሌሎች ቋንቋዎች ወደ አማርኛ እንዲመለሱ ከአማርኛም ወደ ሌሎች ቋንቋዎች እንዲተረጎሙ የሚኖረው ድጋፍ ከፍተኛ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ የትርጉም አገልግሎት የመስጠት ሙያ ላይ የተሰማሩ አቶ አብርሀም ሞሼ መዝገበ-ቃላት የቆዩ በመኾናቸው አዳዲስ ቃላትን ለመተርጎም ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው ብለዋል። በእርግጥ የሚሻሻል ነገር ቢኖረውም እንደጅማሬ ጥሩ መኾኑን ጠቅሰዋል።
Amharisch Google-Übersetzer auf Handy


አንድ ቋንቋ በጉግል የትርጉም ሥራ አገልግሎት ለማግኘት ጉግል በመሠረታዊነት ያስቀመጠው መሥፈርት ቋንቋው በጽሑፍ የሚገኝ መኾኑ ነው። ከዚያም ባሻገር በቋንቋው በርካታ ጽሑፎች የኢንተርኔቱ ዓለም ላይ ወይንም ድር ውስጥ መገኘታቸው ትኩረት እንደሚሰጠውም ጉግል በአምደመረቡ አስፍሯል። ጉግል በዋናነት ለትርጉም የሚጠቀመው በቋት ውስጥ ያከማቻቸውን ቃላት በመውሰድ ነው።

አማርኛ ከአረብኛ ቀጥሎ ዓለም ላይ በስፋት ከሚነገሩ የሴሜቲክ ቋንቋዎች ሁለተኛው ነው። በጉግል የትርጉም ስነ-ቴክኒክ ዘርፍ የሚወጡ ማናቸውንም ይፋዊ መረጃዎች የሚቆጣጠረው ጎግል መተርጎሚያ በአምደመረቡ ይኽንኑ አስፍሯል። ጉግል የትርጉም አገልግሎት ሲሰጥ ከኢንተርኔቱ ዓለም በመረጃ ቋቱ አሰባስቦ ካከማቻቸው የአማርኛ ቃላት እና ጽሑፎች በቀጥታ ይጠቀማል። የባለቤትነት መብት ያላቸው አቅርቦቶችንም አገልግሎት ላይ ያውላል። ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትርጉም ለማከናወን ጉግል ወርድ ኔት የተባለውን በባለቤትነት የተያዘ የትርጉም ቋት ይጠቀማል። ከዚያም ባሻገር ማንኛውም የጉግል የኢሜል አድራሻ ያለው ሰው በአድራሻው ገብቶ መተርጎም እና የተተረጎሙትንም ማረም ይችላል።

ጥራት ያላቸው ትርጉሞች እየተበራከቱ በሄዱ ቁጥር የጉግል የአማርኛ ትርጉም አገልግሎት ጠቀሜታው እየጎለበተ ሊሄድ ይችላል። በእርግጥ የአማርኛ ሰዋሰው ከእንግሊዝኛ፣ አለያም ከጀርመንኛ አለያም ከሌሎች ቋንቋዎች የተለየ መኾኑ የትርጉም ሥራው ላይ ተግዳሮት መፍጠሩ አልቀረም።
ካለፉት ሁለት ሣምንታት አንስቶ በጉግል መተርጎም መጀመራቸው በይፋ የተነገረላቸው 13ቱ ቋንቋዎች አማርኛ፣ ቆሳ፣ ሾና፣ ኮርዲካ፣ ፍሪዚያ፣ ኪርጊዝ፣ ሃዋዪ፣ ኩርድ፣ ሉግዘምቡርግ፣ ሳሞዋ፣ የስኮት ጋዬሊክ፣ ሲንዲ እና ፓሽቱ ናቸው። ጉግል የአማርኛ ቋንቋን በጽሑፍ ከመተርጎሙ ባሻገርም ወደፊት በድምጽም እየተናገሩ በመቅዳት ቋንቋውን በኢንተርኔቱ ዓለም በስፋት ለመጠቀም እንዳሰበ የሶፍትዌር ዴቨሎፐር ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ አየለ ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ በጉግል የትርጉም አገልግሎት ለሚሰጡት 103 ቋንቋዎች በዓለም ዙሪያ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስተዋጽዖ አድርገዋል። ወደ 200 ሚሊዮን ገደማ የሚጠጉ ቃላትም በተለያዩ የዓለማችን ቋንቋዎች እንደተተረጎሙ ጉጉል በገጹ አስነብቧል። አማርኛ ቋንቋ በጉግል የትርጉም አገልግሎት መጀመሩ ለቋንቋው ታላቅ እመርታ ነው። አሁን የሚታዩ የትርጉም ስህተቶቹን ለመቀነስ ግን አቅሙ ያላቸው ሰዎች የጉግል ማኅበረሰብ ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት አስተዋጽዖ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ

ዓርብ 11 ማርች 2016

#አዲስ አበባ ከተማና ከንቲባዎቾ


ብዞዎቻችን ይህን ቃል በተለያዩ ሚዳዎች ሲጠራ እንሰማል ሆኖም ምንያህላችን ስለዚህ ቃል ትርጉም አውርተን እናቅ ይሆን ካለወቅንም ጠይቀን እናውቃለን ባይገርማችሁ እኔ ጥያቄ የመጣልኝ ስለ አዲስ አበባ ክንቲባዎች ስራዎች ለመፃፍ ሳስብ ከንቲባ ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ አህምሮዬ አነሳ  ስለዚህ መልስ ለማግኘት መፅሐፍ ስፈልግ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ባለፈውና በመጪው ሚሌኒየም ›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ እሰተዳደር ሚሊኒም ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሳነብ ያገኘውት ላካፍላች እንሆ ብለናል፡፡
 ከንቲባ (ላንተ ይግባ) ማዕረጉ ከሊጋባ በታች የኾነ ዋና የራስ ከተማ ሹምና ዳኛ ፣ የከተማው ቀረጥና የዳኝነቱ ገንዘብ (ይበእ ኀቤክ) አንተ ዘንድ ይግባ ማለት ነው፡፡ይህ ስም በዘመን ብዛት ለባለሃብቶችና ለታላላቅ ሀገር ገዢዎች ስለተሰጠ እስከ ዛሬ ድረስ የሀሳብ ባላባት ከንቲባ ይባላል፡፡ (ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት 62)
ከባህር ወለል በላይ የሶስት ሺህ ሜትር ከፍታ ካለው እንጦጦ ታራራ ላይ ተቆርቁራ ቁልቁል ወደ ፍል ውሃ ከዚያም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ተንሰራፍታ የ126ኛው ዓመት በማስቆጠር የከተመችው አዲስ አበባን በተለያዩ ዘማናት ያስተዳድሮት የነበሩ ከንቲባዎች ቀደም ባለው አገላለጽ ‹‹የመገናኛና የዋና ከተማ ገዥዎችና አስተዳዳሪዎችን›› የቆይታ ጊዜና ለየት ያለ ተግባርና እንቅስቃሴ በማሲንቆ ኢንትርቴመንት ለማቅረብ ዝግጅታችን አጠናቀን ከታሪክ ማዕድ እንሆ ብለናል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ከተቆረቆረች ጀምሮ ሲመሯት የነበሩ ከንቲባዎች በቅደምተከተል በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ።

#አዲስ አበባ ከተማና ከንቲባዎቾ


ብዞዎቻችን ይህን ቃል በተለያዩ ሚዳዎች ሲጠራ እንሰማል ሆኖም ምንያህላችን ስለዚህ ቃል ትርጉም አውርተን እናቅ ይሆን ካለወቅንም ጠይቀን እናውቃለን ባይገርማችሁ እኔ ጥያቄ የመጣልኝ ስለ አዲስ አበባ ክንቲባዎች ስራዎች ለመፃፍ ሳስብ ከንቲባ ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ አህምሮዬ አነሳ  ስለዚህ መልስ ለማግኘት መፅሐፍ ስፈልግ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ባለፈውና በመጪው ሚሌኒየም ›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ እሰተዳደር ሚሊኒም ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሳነብ ያገኘውት ላካፍላች እንሆ ብለናል፡፡
 ከንቲባ (ላንተ ይግባ) ማዕረጉ ከሊጋባ በታች የኾነ ዋና የራስ ከተማ ሹምና ዳኛ ፣ የከተማው ቀረጥና የዳኝነቱ ገንዘብ (ይበእ ኀቤክ) አንተ ዘንድ ይግባ ማለት ነው፡፡ይህ ስም በዘመን ብዛት ለባለሃብቶችና ለታላላቅ ሀገር ገዢዎች ስለተሰጠ እስከ ዛሬ ድረስ የሀሳብ ባላባት ከንቲባ ይባላል፡፡ (ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት 62)
ከባህር ወለል በላይ የሶስት ሺህ ሜትር ከፍታ ካለው እንጦጦ ታራራ ላይ ተቆርቁራ ቁልቁል ወደ ፍል ውሃ ከዚያም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ተንሰራፍታ የ126ኛው ዓመት በማስቆጠር የከተመችው አዲስ አበባን በተለያዩ ዘማናት ያስተዳድሮት የነበሩ ከንቲባዎች ቀደም ባለው አገላለጽ ‹‹የመገናኛና የዋና ከተማ ገዥዎችና አስተዳዳሪዎችን›› የቆይታ ጊዜና ለየት ያለ ተግባርና እንቅስቃሴ በማሲንቆ ኢንትርቴመንት ለማቅረብ ዝግጅታችን አጠናቀን ከታሪክ ማዕድ እንሆ ብለናል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ከተቆረቆረች ጀምሮ ሲመሯት የነበሩ ከንቲባዎች በቅደምተከተል በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ።

#አዲስ አበባ ከተማና ከንቲባዎቾ


ብዞዎቻችን ይህን ቃል በተለያዩ ሚዳዎች ሲጠራ እንሰማል ሆኖም ምንያህላችን ስለዚህ ቃል ትርጉም አውርተን እናቅ ይሆን ካለወቅንም ጠይቀን እናውቃለን ባይገርማችሁ እኔ ጥያቄ የመጣልኝ ስለ አዲስ አበባ ክንቲባዎች ስራዎች ለመፃፍ ሳስብ ከንቲባ ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ አህምሮዬ አነሳ  ስለዚህ መልስ ለማግኘት መፅሐፍ ስፈልግ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ ባለፈውና በመጪው ሚሌኒየም ›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ የአዲስ አበባ ከተማ እሰተዳደር ሚሊኒም ጽ/ቤት የተዘጋጀ ሳነብ ያገኘውት ላካፍላች እንሆ ብለናል፡፡
 ከንቲባ (ላንተ ይግባ) ማዕረጉ ከሊጋባ በታች የኾነ ዋና የራስ ከተማ ሹምና ዳኛ ፣ የከተማው ቀረጥና የዳኝነቱ ገንዘብ (ይበእ ኀቤክ) አንተ ዘንድ ይግባ ማለት ነው፡፡ይህ ስም በዘመን ብዛት ለባለሃብቶችና ለታላላቅ ሀገር ገዢዎች ስለተሰጠ እስከ ዛሬ ድረስ የሀሳብ ባላባት ከንቲባ ይባላል፡፡ (ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት 62)
ከባህር ወለል በላይ የሶስት ሺህ ሜትር ከፍታ ካለው እንጦጦ ታራራ ላይ ተቆርቁራ ቁልቁል ወደ ፍል ውሃ ከዚያም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ተንሰራፍታ የ126ኛው ዓመት በማስቆጠር የከተመችው አዲስ አበባን በተለያዩ ዘማናት ያስተዳድሮት የነበሩ ከንቲባዎች ቀደም ባለው አገላለጽ ‹‹የመገናኛና የዋና ከተማ ገዥዎችና አስተዳዳሪዎችን›› የቆይታ ጊዜና ለየት ያለ ተግባርና እንቅስቃሴ በማሲንቆ ኢንትርቴመንት ለማቅረብ ዝግጅታችን አጠናቀን ከታሪክ ማዕድ እንሆ ብለናል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ከተቆረቆረች ጀምሮ ሲመሯት የነበሩ ከንቲባዎች በቅደምተከተል በተከታታይ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ።