By Bersufkad Zena@DireTube
---------------------------------------
ቅናት የምንፈልገውን ሰው አጣዋለሁ ብሎ ከመስጋት
የሚመነጭ ስሜት ነው፡፡ቅናት ነገሮችን ከራስ አንጻር ብቻ
በማየት የሚከሰት ነገርም ነው፡፡ ቅናት ደረጃዎች ያሉት
ሲሆን በአለባበስና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ አስተያየት
ከመሥጠት ጀመሮ የአጋራችንን ሁለንተናዊ ነገር
ለመቆጣጠር እስከመሄድ የሚደርስ ነው፡፡ የጥናት
ውጤቶች እንደሚያሳዩት ቅናት ሀይለ ስሜታዊ፣አካላዊ
፣ስነባህሪያዊ እነዲሁም ማህበራዊ አሉታዊ ተጽእኖዎችን
በሰዎች ላይ ያሳድራል፡፡
--
የቅናት ምክንያቶች
ሰዎችን ለቅናት የሚዳርጉ ብዙ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን
እነዚህ ምክንያቶች ካስተዳደግና ከምንኖርበት
ማህበረሰብ ባህል ጋር ቀጥተኛ ወይም ቀጥተኛ ያልሆነ
ግንኙነት አላቸው፡፡ከተለያዩ የጥናት ውጤቶች
ያገኘኋቸውን እና በእኛ ሐገር ነባራዊ ሁኔታ ያስኬዳሉ
ያልኳቸውን የቅናት ምክንያቶች ከዚህ እንደሚከተለው
አቀርብላችኋለው::
---
1.አጋርን የማጣት ስጋት እና ከመጠን ያለፈ ፍራቻ
የመጣንበት መንገድ ወይንም ከሰዎች ልምድ በመነሳት
እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡
እንዲሁም ለራሳችን የምንሰጠው ቦታ የወረደ ከሆነ ሌላ
ሰው ትልቅ ቦታ ይሰጠናል ብለን ለማሰብ እንቸገራለን
በዚህም ቅናት ውስጥ የመግባት እድል ይኖረናል፡፡የጥናት
ውጤቶች እንደሚያሳዩት የትዳር አጋራችንን ልናጣ
እንደምንችል በመጠኑ መፍራት ፍቅርን የማጠናከር አቅም
አለው ፡፡ነገር ግን ከመጠን ያለፈ ፍራቻ ለቅናት ይዳርጋል
እንዲሁም የምንወደውን ሰው ሊያሳጣንም ይችላል፡፡
---
2.ሰዎችን እንደቁስ መቁጠር
ሰዎች አስበውና ወደውን እንደመረጡን የማይሰማን ከሆነ
እንዲሁም በየትኛውም ጊዜ የሆነ ሰው ተነስቶ ሊቀማን
ይችላል ብለን የምናስብ ከሆነ የመቅናት እድል ይኖረናል፡:
---
3.ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ጥገኛ መሆን
ጥገኝነት በብዙ መንገድ ሊገለጽ ይችላል የግዴታ ቁሳዊ
ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡አነድ ሰውን ያጣን ጊዜ የኛ መኖር
እንደሚቆም የምናስብ ከሆነ ያንን ሰው ላለማጣት
እንጥራለን ሁሉም ሰው እሱን የሚቀማን ይመስለናል
በዚህም በቀላሉ በቅናት እንጠቃለን፡፡
----
4.ከአስተዳደጋችን እና ከምንኖርበት ማህበረሰብ ባህል
ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምክንያቶች
እነዚህ ምክንያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በወላጅ እና
በአሳዳጊ መሀከል ጥሩ ያልሆነ ግኝኙነት ከነበር፣
ከህጻንነታችን ጀምሮ ምንም ነገር የመስራት ችሎታ
እየተነገረን ካዳግን…..ወዘተ
----
ቅናትን ለመቀነስ ምን ማድረግ እንችላለን?
ቅናት ሰዎችን ለበሽታ ፣ለጭንቀት እንዲሁም ለተለያዩ
ማህበራዊ ቀውስ የሚዳርግ ነገር ነው፡፡ቅናትን ሙሉ
ለሙሉ ማጥፋት ባይቻልም ቢያንስ ለመቀነስ የሚረዱ
ዘዴዎች አሉ፡፡ ቅናት ለበትን ሰው ከዚህ ስሜት እነዲላቀቅ
ወይም ቅናትን ለመቀነስ የሚረዱ እና ከተለያዩ የጥናት
ውጤቶች ላይ ያገኘኋቸውን ዘዴዎች ከዚህ በታች
እናያቸዋለን እቀርባለሁ
--
1.ቅናት ችግር መሆኑን ማመን
አንዳንድ ሰዎች ቅናትን ጥሩ እንደሆነና ሰውን ከመውደድ
አንጻር የሚደረጉት እንደሆነ ያስባሉ በዚህም ለተለያዩ
ችግሮች ይዳረጋሉ፡፡ ከዚህ ይልቅ ቅናት ትልቅ ችግር
መሆኑን በመረዳት መፍትሄ መፈለግ ጠቃሚ ነው፡፡
--
2.እራሳችንን እና የፍቅር ሂይወታችንን መገምገም
በጣም የተረጋጋና ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ውስጥ
እየኖርን የቅናት ስሜት የሚሰማን ከሆነ እራሳችንን
መገምገም እና ከባለሞያ ጋር መመካከር ያስፈልጋል፡፡
--
3.በሰከነ መንገድ ለመነጋገር መሞከር
ያልተፈጠረ ነገርን ተፈጥሯል ብለን እራሳችንን ከመጉዳት
በፊት በተረጋጋ ሁኔታ አስበንበት ግልጽ የሆነ ውይይት
የማድረግ ባህልን ብናዳብረ ቢያንስ በቅናት ምክንያት
ሊደርስብን የሚችለውን አደጋ መቀነስ እንችላለን፡፡
---
4.እራሳችን ላይ መስራት
ቅናት በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል ለምሳሌ ለራሳችን
ዝቅተኛ ቦታ መስጠት አንዱ የቅናት ምክንያት ነው፡፡
እንደዚህ እይነት ምክንያቶችን በመለየት እና እራሳችን ላይ
በመስራት በራስ መተማመናችንን በመጨመር ፣ ለራሳችን
ከፍተኛ ግምት በመስጠት ………ወዘተ ቅናትን መቀነስ
እንችላለን፡፡
---
5.ለሚቀናበት ሰው
አጋራችን እነደሚቀናብን ካወቅን አጋራችንን መርዳት
ይጠበቅብናል፡፡ ለአጋራችን ሁሌም ከጎናቸው እንደሆንን
እና ፍቅራችንን የምንገልጽ ከሆነ የአጋራችንን ቅናት
የመቀነስ አቅም ይኖረናል፡፡የጥናት ውጤቶች
እንደሚያሳዩት እንደዚህ የሚያደረጉ ሰዎች የተረጋጋ
የፍቅር ህይወት ይኖራቸዋል፡፡
---
6.ከባለሞያ ጋር መነጋገር
ቅናት ደረጃ አለው በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረስን
ከመሰለን እና በራሳችን መንገድ ለመተው ሞክርን ካቃተን
ከባለሙያ ጋር በመነጋገር እና እገዛ በማግኘት
ወደተፈላጊው መንገድ መምጣት እንችላለን፡፡
====
@በሱፍቃድ ዜና የሰዎችን እድገት በሚያጠና የስነበሃሪ
ትምህርት ዘርፍ(Developmental psychology)
ሁለተኛ ዲግሪ(ማስተርስ) ያለው ሲሆን ባሁኑበልጆች
አስተዳደግ እና በትምህርት ዙሪያ ወላጆችን የሚያማክር
ድርጅት ከፍቶ በግሉ እየሰራ ያለ ወጣት ባለሙያ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ zbesufekad@gmail.com
ዓርብ 6 ሜይ 2016
ቅናት
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ