ግብፃዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ በፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የ2017-18 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡
የ25 ዓመቱ ሞሃመድ ሳላህ ተፎካካሪዎቹን ኬቨን ዴብሩየን፤ ሊሮይ ሳኔ፤ ዲቬዲ ሲልቫ፤ ሃሪ ኬንን እና ዲቬድ ድሂሃን በመብለጥ ነው አሸናፊነቱን ያረጋገጠው፡፡
“በቼልሲ ክለብ እያለሁ ያለኝን ችሎታ ማሳየት አልቻልኩም ነበር፤ በተጫዎቾች መመረጤ ክብር ተሰምቶል በጣም ደስተኛ ነኝ” በማለት ሳላህ አስተያቱን ሰጥቷል፡፡
የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በበኩላቸው የሳላህ አሰልጠኝ በመሆናቸው እጅጉን ደስተኛ እንደሆኑና ይህን ሽልማት ማሸነፉ የማይታመን ክብር ነው በማለት ለሳላህ ያላቸውን አድናቆት ተናግረዋል፡፡
ሳላ ፕሪምየር ሊግ በ31 ጨዋታዎች 33 ግቦች በማስቆጠር የፕሪሚየር ሊጉን የምን ጊዜውም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰኑን ከአላን ሼረር ፣ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሉዊስ ሱዋሬዝ ጋር ክብረወሰኑን ተጋርቷል፡፡
የማንችስተር የሲቲው ሊሮይ ሳኔ ደግሞ የፕሪምየር ሊግ ወጣት ተጫዋች በመባል የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በሴቶቹ ደግሞ የቼልሲዋ ፍራንክ ኪርቢ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብላ የተሸለመች ሲሆ የብሪስቶል ሲቲዋ ላውረን ሄምፕም እንዲሁ በሴቶች ወጣት ተጫዋችን ሽልማት አግኝታለች፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲ

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ