በአዲስ አበባ የሚገኙ 13 የግል ትምህርት ቤቶች ያልተገባ ክፍያን ከተማሪ ወላጆችን ከማስከፈል ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው።
ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው የትምህርት ተቋማት ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ያሉ መሆናቸውን በአዲስ አበባ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት እና አግባብነት ሬጉላቶሪ ኤጀንሲ አሳውቋል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ብሩክነሽ አርጋው እንዳሉት ተቋማቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ በሚል ተጨማሪ ክፍያ ከወላጆች በመውሰዳቸው ነው።
በተደረገ ክትትል እና ፍተሻም ተቋማቱ ለመማሪያ ቁሳቁስ በሚል ከወላጆች የተቀበሉትን ገንዘብ እና ተጨማሪ የመማሪያ ቁሳቁሶችም ለወላጆች እንዲመለሱ መደረጉን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
ሌሎች ተቋማት ላይም ይህን መሰል ድርጊት እንዳይፈፅሙ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።
እነዚህ ተቋማትም በድጋሚ ይህን ተግባር የሚደግሙት ከሆነ እርምጃ የሚወሰድባቸው እንደሚሆንም ኤጀንሲው ገልጿል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ተቋማት የውጭ ፍተሻ ስራ ትናንት በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፥ የፍተሻ ስራው ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ ባሉ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ነው የሚሰጠው።
ኤጀንሲው እስካሁን ከመማር ማስተማር ሂደቱ ጋር ተያይዞ ችግር አለባቸው ለተባሉ 99 የመንግስትና 5 የግል የትምህርት ተቋማት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
እነዚህ ተቋማት ከነበሩበት ደረጃ የማይሻሻሉና ያሉባቸውን ችግሮች የማይቀርፉ ከሆነም እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በዙፋን ካሳሁን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2010
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ