ማክሰኞ 3 ሜይ 2016

ዝንብና ንብ

አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ
ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
.
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ ለምንስ
ነው የሚጸየፉኝ ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
.
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ
ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል
.
አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ
ይንከባከቡሻል ደግሞም
መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው
ለምንድነው?
.
ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ
አለቻት
.
"ውሎሽ የት ነው?"
.
እንግዲህ እናስታውስ ሰው ጠላን፣ገፋን፣ናቀን እያልን እንደ
ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ
መቼም ማንም በጤፍ ማሳ ላይ ስንዴን አይጠበቅም።
.
ስለዚህ ምንጊዜም ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን
ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ
ምክንያቱም
ሀሳባችን ስራችንን
ስራችን ውጤታችንን
ውጤታችን እኛነታችንን
ይገልጽልናል!
.
ውሏችን የት ነው?
ምንጭ # eyohaa.com እዮሃ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ