ረቡዕ 22 ሜይ 2019

አሳሙዋ ጂያን ከጋና ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ራሱን አገለለ

በጋና እግር ኳስ ታሪክ በ51 ግቦች የምንጊዜም ኮከብ ግብ አስቆጣነቱን የያዘው አሳሙዋ ጂያን ከጋና ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡
ተጫዋቹ በአሁኑ ሰዓት በቱርክ ለየሲሪሰፖር ክለብ እየተጫወተ ይገኛል፡፡
ሀገሩ ጋና ከአንድ ወር በኋላ በግብፅ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2019ኙ 32ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አምበልነቱን ለሌላ ተጫዋች እንደሚሰጥ አሰልጣኝ ኩዋሲ አፒያ መገለፁን ተከትሎ ነው ራሱን ከብሄራዊ ቡድኑ ያገለለው፡፡
አሰልጣኝ ኩዋሲ አፒያ የጋና ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድኑ አባል ሆኜ አንበልነቱን ለሌላ ተጫዋች የሚሰጡ ከሆነ በገዛ ፍቃዴ ረሴን ከብሄራዊ ቡድኑ አግያለው ብሏል ጊያን፡፡
አሰልጣኝ ኩዋሲ አፒያ ለግብፁ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ 29 ተጫዋቾችን ይፋ ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡
ምንጭ፡ - ቢቢሲ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ