ዩጋንዳ ከፍተኛ የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ከሚከሰትባቸው አገራት አንዷ ስትሆን በየቀኑ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ የ15 እናቶች ህይወት ያልፋል፡፡
በአብዛኛው የዩጋንዳ ገጠራማ አከባቢዎች የሚገኙ መንዶች ለመደበኛ አምቡላንሶች አመቺ ስላልሆኑ በቀላሉ ወደ ገጠር መግባት የሚችሉ ልዩ ተሸከርካሪዎችን መስራት የግድ ሆነ፡፡
እናቶች የምጥ ስሜት ወይም የህመም ስሜት ሲሰማቸው አገልግሎቱን ለሚሰጡ ሰዎች በመደወል በብስክሌት አምቡላንስ ወደ ጤና ተቋም በቀላሉ በመድረስ መታከም ይችላሉ፡፡
በተለይም በአገሪቱ ከሚገኙ 121 አካባቢዎች 77ቱ የአምቡላንስ አገልግሎት ስለማያገኙ ችግሩን አባብሶት ቆይቷል፡፡
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዩጋንዳውያን ታዲያ የዘየዱት ስልት የበርካታ ነብሰ-ጡርና ተማሚ እናቶችን ህይወት መታደግ ችሏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2018 በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የብስክሌት አምቡላንስና የመረጃ ተቋም ወይም ማህበር መሰረቱ፡፡
በአብዛኛው የዩጋንዳ ገጠራማ አከባቢዎች የሚገኙ መንዶች ለመደበኛ አምቡላንሶች አመቺ ስላልሆኑ በቀላሉ ወደ ገጠር መግባት የሚችሉ ልዩ ተሸከርካሪዎችን መስራት የግድ ሆነ፡፡
ይህንንም ለማሳካት የብስክሌት አምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ተሸከርካሪዎችን መስራት ተቻለ፡፡
የብስክሌት አምቡላንሶቹ የተሰሩት በአካባቢው ሰዎች በአካባቢው ከሚገኙ ቁሳቁስ ሲሆን መለዋወጫዎቻቸው በየሰፈሩ በቀላሉ ይገኛሉ፡፡
እናቶች የምጥ ስሜት ወይም የህመም ስሜት ሲሰማቸው አገልግሎቱን ለሚሰጡ ሰዎች በመደወል በብስክሌት አምቡላንስ ወደ ጤና ተቋም በቀላሉ በመድረስ መታከም ይችላሉ፡፡
ብስክሌቶቹ ይዘውት የመጡት መፍትሄ የነብሰ-ጡር እናቶችን ህይወት ከመታደግ በተጨማሪ በአካባቢ ላይ ብክለትን የማያስከትል በመሆኑ ተመራጭ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡
የማህበሩ የመስክ ኦፊሰር ጀሬሚያህ ብራያን ንኩቱ እንደሚለው የመሬቱ ወጣ ገባ መሆን የአምቡላንስ ብስክሌቶቹን እንደልብ ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ቢያደርገውም ፈጠራው ለአፍሪካዊው ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ለማበጀት የቻለ ነው ብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ