ዓርብ 25 ማርች 2016

#አዲስ አበባ ከተማና ከንቲባዎቾ


የዛሬዋ አዲስ አበባ ከተማ ከ1901ዓ.ም ጀምሮ ቁጥራቸው በዛ ያለከንቲባዎችን ማፈራረቋ የታሪክ መጽሐፍት መረጃውን ይጠቁማሉ ከተማዋ ከንቲባ መሾም ስትጀምር እንዳውኑ በአዲስ አበባ ምክር ቤት አልነበረም የከንቲባ ሹመት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት መነሻ ታሪክ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ነገር ግን በ1901 ዓ.ም ቢትወደድ ወልደ ጻዲቅ ጎሹ የመጀመሪያው ከንቲባ ሆነው ቢሾሙም የአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆኑ የጎንደር ከንቲባ ሆነው በመሾም እንዳገለገሉና የአገልግሎት ዘመናቸውም ከ1901 እስከ 1908 እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ ሆኖም በአንዳንድ መረጃዎች መሠረት ደግሞ የአገልግሎት ዘመናቸው ከ1892 ይጀምራል ይላል፡፡ ሲሾሙ ማዘጋጃ ቤት የሚባል ነገር አይታወቅም ሆኖም ቀደም ብሎ ግን ‹‹የከተማ ማህበር ቤት›› ይባል የነበረና የጠፉ ከብቶችንና በተከለከለ ቦታ የተገኙ የቤት እንስሶችን አፈላልጎ አስከፍሎ የሚሰጥ ቤት ነበር ታዲያ ይህ ቤት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የማዘጋጃ ቤት አሠራርን ያስጀመሩበት ነው ተብሎ ይገለፃል፡፡
በ1909 ዓ.ም ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ቢትወድ ኃይለ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ቆይታቸውም ለአንድ ዓመት ያህል የነበረ ሲሆን በቆይታቸውም ወቅት በተለይ የንግዱ ዘርፍ እንዲለማ ከፍተኛ ጥረት ያዳረጉ ሲሆን ለዚህም ደግሞ የንግድ ሚኒስተር ሆነው እንዲሾሙ አስተዋጾ አድርጎላቸዋል ይባላል፡፡  

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ