ደርቆ ከበሰለዉ ከተንጠለጠለዉ፣
የስጋ ደረቆት‹‹ ቁዋንጣ›› ከሚባለዉ፤
አየሁት ስጋዬን ለየሁት በሩቁ፣
ቀመስኩት፣ በላሁት ጣፈጠኝ መረቁ፣
ወጥ ሆኖም አየሁት በድስቱ ሲማሰል፣
ሲጎመድ፣ ሲጎረድ ፣ ሲከተፍ ሲቀቀል፣
በነፈረ ዉሃ ተነፍሮ ሲበሰል፣
ቀመስኩት በእንጀራ የእኔዉም አይመስል፡፡
ደሞ አልጫ ሆኖ በቀለም ኮስምኖ፣
በቅመማት ዋይታ ሁለመናዉ ቀጥኖ፣
አየሁት ስጋዬን ራሱን ለዉጦ፣
በሱፋ፣ በቅባኑግ፣ በቅባቶች ቀልጦ፡፡
በማንም ወጥ ቀቃይ፣ በሰላ ቢላዋ፣
ሲከፈት አየሁት ሲደቅ እንዳሸዋ፡፡
ክትፎዉን ቀመስኩት በጣሙን ይጥማል፣
የእጄ ጣም ራሱ እጅ ያስቆረጥማል፡፡
ምንጭ ካነበብ ነው
(አበራ አዳሙ ውዳሴ ሞት የግጥም መድበል
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ