ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።
ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።
በማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማንና ለጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ጠቅሰዋል።
በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ነርሶችና ዶክተሮች ሥልጠና ተሰጥቷል።
በዚህ መሰረት የማዕከሉ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ ህሙማንን መቀበል መጀመሩን ነው ዶክተር እስማኤል መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ