የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ሽንትን ለረጅም ጊዜ መቋጠር ለሰው ልጅ ጤና ከፍተኛ ችግር ያስከትላል።
ታዲያ
እንዲህ አይነቱ ልማድ ለጤና እክል ሊዳርገን ይችላል የሚሉን የጤና ባለሙያዎች፥ እንዲህ ከማድረግ መቆጠብ መልካም ነው ሲሉም ምክር አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሽንትን ለረጅም ጊዜ መቋጠር የሚያስከትላቸው እክሎች…
ምቾት ማጣት እና ከፍተኛ የህመም ስሜት፦ ለረጅም
ሰዓት
ሽንታቸውን የሚይዙ ሰዎች ምቾት የማጣት እና ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት እንደሚያጋጥማቸው ተነግሯል።
ትኩረት ማጣት፦ ሽንትን
ለረጅም ሰዓት መቋጠር በምናከናውናቸው ተግባራት ላይ ትኩረት እንድናጣ ያደርጋል።
ትኩረት ማጣት ደግሞ ከፍተኛ አደጋ እንደሚያስከትል ይታወቃል፤ በተለይም ሽንትን ለረጅም ሰዓት በመቋጠር ማሽከርከር ጠጥቶ ከማሽከርከር እንደማይተናነስ በጉዳዩ ላይ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።
ምክንያቱም ትኩረትን በመቀነስ ለትራፊክ አደጋ ሊዳርግ እንደሚችል በመግለጽ።
የፊኛ ያለመቆጣጠር ችግር፦ ከላይ ከዘረዘርናቸው
በተጨማሪም ሽንት ሳንሸና ለረጅም ጊዜ በመቋጠር ማቆየት ለበርካታ የጤና እክሎች ይዳርጋል።
ከእነዚህም ውስጥ የሽንት ፊኛ አለመቆጣጠር ችግር ዋነኛው መሆኑ ይነገራል።
ሽንትን ለረጅም ሰዓት በምንቋጥርበት ወቅት በሽንት ፊኛ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና እንዲፈጠር በማድረግ ፊኛችን ከቁጥጥር ውጪ እንዲሆን ያደርጋልም ተብሏል።
የኩላሊት ህመም፦ ሽንትን
ለረጅም ጊዜ የምንቋጥር ወይም የምንይዝ ከሆነ ለኩላሊት ህመም ሊዳርገን እንደሚችልም ተጠቅሷል እና ጥንቃቄ ማድረጉ መልካም ነው።
እንዲሁም በቀላሉ ሽንታችንን ያለመሽናት ችግር እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን እንደሚያስከትልም ተገልጿል።
ስለዚህ ሽንት በሚይዘን ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መጸዳጃ ቤት ወዳለበት በመሄድ መሽናት ይኖርብናል።
ምንጭ፦ http://hosbeg.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ