#በ45ኛው ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና መክፈቻ በሴቶች የ10ሺህ ሩጫ ውድድር ሹሬ ደምሴ አሸነፈች።
ትናንት ምሽት ላይ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ውድድር ሹሬ ደምሴ ከኦሮሚያ ፖሊስ 33 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ከ47 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው።
የኔነሽ ጥላሁን ከፌዴራል ፖሊስ፣ አያንቱ ኢዶሳ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሹሬን ተከትለው ውድድራቸውን በማጠናቀቅ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
በወንዶች በተደረገው የስሉስ ዝላይ አዲር ጉር ከመከላከያ ቀዳሚ ሲሆን፣ ሰለሞን ፈቃዱ ከኦሮሚያ ክልልና ጌቱ ደቀባ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
በተመሳሳይ በወንዶች በተካሄደው የጦር ውርወራ ኡቱ ኡቤሎ ከመከላከያ ክለብ 67 ነጥብ 27 ሜትር በመወርወር አሸናፊ ሆኗል፡፡
አቡ ጉዮ 58 ነጥብ 86ና ሽፈራው ሾዋካ 58 ነጥብ 73 ሜትር በማስመዝገብ ከኦሮሚያ ክልልና ከሲዳማ ቡና ክለብ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃዎችን ይዘው ውድድሮቻቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶች የአሎሎ ውርወራ አመለ ይበልጣል 13 ነጥብ 53 ሜትር በመወርወር አዲስ ክብረወሰን አስመዝግባለች።
አመለ ባለፈው ዓመት 12 ነጥብ 06 ሜትር ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በ1 ነጥብ 47 ሜትር አሻሽላለች።
ዙርጋ ኡስማን ከሲዳማ ቡና ሁለተኛ እንዲሁም መሰረት ከበደ ከመከላከያ ክለብ ሶሰተኛ በመሆን ውድድሩን ፈጽመዋል።
በሴቶች ከፍታ ዝላይ አርያት ዲቦ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስታሸንፍ፣ ኩት ኡቻንና አጀዳ አመድ ከመከላከያ እስከ ሦስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ተቆናጠዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ በሻምፒዮናው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ እንደተናገሩት ሻምፒዮናው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡ አትሌቶች ለብሔራዊ ቡድን ይመረጡበታል።
በተጨማሪም ተተኪ አትሌቶች የሚፈሩበት፣ ክለቦች አቅማቸውን የሚለኩበት ከመሆን ባለፈ፤ ለአሸናፊዎች ልዩ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
ከመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ቀደም ብሎ የ100፣ የ400፣የ800ና የ400 ሜትር የመሰናክል የማጣሪያና የግማሽ ፍጻሜ ሩጫ ውድድሮች ተካሂደዋል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ክለብ የአጭር ርቀት ሯጭ ወጋየሁ በሉ በሰጠው አስተያየት በማጣሪያ ውድድሮች አትሌቶች የሚያሳዩት ፉክክር መልካም መሆኑን ገልጾ፤ ይሁን እንጂ የወቅቱ ዝናብ ለጉዳት እንዳይዳርጋቸው ስጋቱን ተናግሯል።
በቀጣይም ብዙ አዳዲስ ክብረወሰኖች ሊመዘገቡ እንደሚችሉ ያለውን እምነት ገልጿል።
ሻምፒዮናው ዛሬም በመቀጠል የወንዶች የ10ሺህ ሜትር፣የ100 ሜትር፣የዲስከስ ውርወራ፣ የርዝመት ዝላይ፣ ምርኩዝ ዝላይ እንዲሁም የማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።
እስከ ፊታችን እሁድ በሚዘልቀው የሻምፒዮናው ውድድር ከክለቦችና ክልሎች የተውጣጡ ጨምሮ 551 ሴቶችና 756 ወንዶች በድምሩ 1ሺህ 307 ተወዳዳሪዎች ተካፋይ ሆነዋል።

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ